Skip to content
← Lamentations

Chapter 3 · Amharic

Lamentations

1አሌፍ።በቍጣው፡በትር፡መከራ፡ያየ፡ሰው፡እኔ፡ነኝ።

2ብርሃን፡ወደሌለበት፡ወደ፡ጨለማ፡መርቶ፡ወሰደኝ።

3ዘወትር፡ቀኑን፡ዅሉ፡እጁን፡በላዬ፡መለሰ።

4ቤት።ሥጋዬንና፡ቍርበቴን፡አስረጀ፥ዐጥንቴን፡ሰበረ።

5ቅጥር፡ሠራብኝ፡በሐሞትና፡በድካምም፡ከበበኝ።

6ቀድሞ፡ሞተው፡እንደ፡ነበሩ፡በጨለማ፡አኖረኝ።

7ጋሜል።እንዳልወጣ፡በዙሪያዬ፡ቅጥር፡ሠራብኝ፤ሰንሰለቴን፡አከበደ።

8በጠራኹና፡በጮኽኹ፡ጊዜ፡ጸሎቴን፡ከለከለ።

9መንገዴን፡በተጠረበ፡ድንጋይ፡ዘጋ፥ጐዳናዬንም፡አጣመመ።

10ዳሌጥ።እንደሚሸምቅ፡ድብ፡እንደ፡ተሸሸገም፡አንበሳ፡ኾነብኝ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

11መንገዴን፡ለወጠ፥ገነጣጠለኝም፤ባድማ፡አደረገኝ።

12ቀስቱን፡ገተረ፡ለፍላጻውም፡እንደ፡ጊጤ፡አደረገኝ።

13ሄ።የሰገባውን፡ፍላጻዎች፡በኵላሊቴ፡ውስጥ፡ተከለ።

14ለወገኔ፡ዅሉ፡ማላገጫ፡ቀኑንም፡ዅሉ፡መሳለቂያ፡ኾንኹ።

15ምሬት፡ሞላብኝ፡በሬትም፡አጠገበኝ።

16ዋው።ጥርሴን፡በጭንጫ፡ሰበረ፥በዐመድም፡ከደነኝ።

17ነፍሴን፡ከሰላም፡አራቅኽ፤በጎ፡ነገርን፡ረሳኹ።

18እኔም፦ኀይሌ፡ከእግዚአብሔርም፡ዘንድ፡ያለው፡ተስፋዬ፡ጠፋ፡አልኹ።

19ዛይ።መከራዬንና፡ችግሬን፡ሬትንና፡ሐሞትን፡ዐስብ።

20ነፍሴ፡እያሰበችው፡በውስጤ፡ፈዘዘች።

21ይህችን፡በልቤ፡አኖራለኹ፥ስለዚህ፡እታገሣለኹ።

22ሔት።ያልጠፋነው፡ከእግዚአብሔር፡ምሕረት፡የተነሣ፡ነው፤ርኅራኄው፡አያልቅምና።

23ማለዳ፡ማለዳ፡ዐዲስ፡ነው፤ታማኝነትኽ፡ብዙ፡ነው።

24ነፍሴ፦እግዚአብሔር፡ዕድል፡ፈንታዬ፡ነው፤ስለዚህ፥ተስፋ፡አደርገዋለኹ፡አለች።

25ጤት።እግዚአብሔር፡በተስፋ፡ለሚጠብቁት፡ለምትሻውም፡ነፍስ፡መልካም፡ነው።

26ሰው፡ዝም፡ብሎ፡የእግዚአብሔርን፡ማዳን፡ተስፋ፡ቢያደርግ፡መልካም፡ነው።

27ሰው፡በታናሽነቱ፡ቀንበር፡ቢሸከም፡መልካም፡ነው።

28ዮድ።ርሱ፡አሸክሞታልና፥ዝም፡ብሎ፡ለብቻው፡ይቀመጥ።

29ተስፋ፡የኾነው፡እንደ፡ኾነ፡አፉን፡በዐፈር፡ውስጥ፡ያኑር።

30ጕንጩን፡ለሚመታው፡ይስጥ፥ስድብንም፡ይጥገብ።

31ካፍ።ጌታ፡ለዘለዓለም፡አይጥልምና፤

32ቢያሳዝንም፡እንደ፡ምሕረቱ፡ብዛት፡ይራራልና፤

33የሰውን፡ልጆች፡ከልቡ፡አያስጨንቅም፥አያሳዝንምም።

34ላሜድ።በምድር፡የተጋዙትን፡ዅሉ፡ከእግሩ፡በታች፡ይረግጣቸው፡ዘንድ፥

35የሰውን፡ፍርድ፡በልዑል፡ፊት፡ይመልስ፡ዘንድ፥

36የሰውን፡ፍርድ፡ያጣምም፡ዘንድ፡ጌታ፡ዕሺ፡አይልም።

37ሜም።ጌታ፡ያላዘዘውን፡የሚልና፡የሚፈጽም፡ማን፡ነው፧

38ከልዑል፡አፍ፡ክፉና፡መልካም፡ነገር፡አይወጣምን፧

39ሕያው፡ሰው፡የሚያጕረመርም፥ሰው፡ስለኀጢአቱ፡ቅጣት፡የሚያጕረመርም፡ስለ፡ምንድር፡ነው፧

40ኖን።መንገዳችንን፡እንመርምርና፡እንፈትን፥ወደ፡እግዚአብሔርም፡እንመለስ።

41ልባችንን፡ከእጃችን፡ጋራ፡በሰማይ፡ወዳለው፡ወደ፡እግዚአብሔር፡እናንሣ።

42በድለናል፡ዐምፀናልም፥አንተም፡ይቅር፡አላልኽም።

43ሳምኬት።በቍጣ፡ከደንኸን፡አሳደድኸንም፤ገደልኸን፥አልራራኽም። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

44ጸሎት፡እንዳያልፍ፡ራስኽን፡በደመና፡ከደንኽ።

45በአሕዛብ፡መካከል፡ጕድፍና፡ውዳቂ፡አደረግኸን።

46ዔ።ጠላቶቻችን፡ዅሉ፡አፋቸውን፡አላቀቁብን።

47ድንጋጤና፡ቍጣ፥ጥፋትና፡ቅጥቃጤ፡ኾነብን።

48ስለወገኔ፡ሴት፡ልጅ፡ቅጥቃጤ፡ዐይኔ፡የውሃ፡ፈሳሽ፡አፈሰሰች።

50ፌ።እግዚአብሔር፡ከሰማይ፡እስኪጐበኝና፡እስኪመለከት፡ድረስ፡ዐይኔ፡ሳታቋርጥ፡ዝም፡ሳትል፡ እንባ፡ታፈሳ፟ለች።

51ስለከተማዬ፡ቈነዣዥት፡ዅሉ፡ዐይኔ፡ነፍሴን፡አሳዘነች።

52ጻዴ።በከንቱ፡ነገር፡ጠላቶች፡የኾኑኝ፡እንደ፡ወፍ፡ማደንን፡አደኑኝ።

53ሕይወቴን፡በጕድጓድ፡አጠፉ፥በላዬም፡ድንጋይ፡ጣሉ።

54በራሴ፡ላይ፡ውሃዎች፡ተከነበሉ፤እኔም፦ጠፋኹ፡ብዬ፡ነበር።

55ቆፍ።አቤቱ፥በጠለቀ፡ጕድጓድ፡ውስጥ፡ኾኜ፡ስምኽን፡ጠራኹ።

56ድምፄን፡ሰማኽ፤ዦሮኽን፡ከልመናዬ፡አትመልስ።

57በጠራኹኽ፡ቀን፡ቀርበኽ፦አትፍራ፡አልኽ።

58ሬስ።ጌታ፡ሆይ፥ስለ፡ነፍሴ፡ተሟግተኽ፡ሕይወቴን፡ተቤዠኽ።

59አቤቱ፥ጭንቀቴን፡አይተኻል፥ፍርዴን፡ፍረድልኝ።

60በቀላቸውን፡ዅሉና፡በእኔ፡ላይ፡ያለውን፡ዐሳባቸውን፡ዅሉ፡አየኽ።

61ሳን።አቤቱ፥ስድባቸውንና፡በእኔ፡ላይ፡ያለውን፡ዐሳባቸውን፡ዅሉ፥

62የተነሡብኝን፡ሰዎች፡ከንፈሮች፡ቀኑንም፡ዅሉ፡ያሰቡብኝን፡ዐሳባቸውን፡ሰማኽ።

63መቀመጣቸውንና፡መነሣታቸውን፡ተመልከት፤እኔ፡መሳለቂያቸው፡ነኝ።

64ታው።አቤቱ፥እንደ፡እጃቸው፡ሥራ፡ፍዳቸውን፡ትከፍላቸዋለኽ።

65የልብ፡ዕውርነትንና፡ርግማንኽን፡ትሰጣቸዋለኽ።

66አቤቱ፥በቍጣ፡ታሳድዳቸዋለኽ፡ከሰማይም፡በታች፡ታጠፋቸዋለኽ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source