1አሌፍ።ወርቁ፡እንዴት፡ደበሰ! ጥሩው፡ወርቅ፡እንዴት፡ተለወጠ! የመቅደሱ፡ድንጋዮች፡በጐዳና፡ዅሉ፡ ራስ፡ተበተኑ።
2ቤት።ጥሩ፡ወርቅ፡የሚመስሉ፡የከበሩ፡የጽዮን፡ልጆች፥የሸክላ፡ሠሪ፡እጅ፡እንደ፡ሠራው፡እንደ፡ሸክላ፡ ዕቃ፡እንዴት፡ተቈጠሩ!
3ጋሜል።ቀበሮዎች፡እንኳ፡ጡቶታቸውን፡ገልጠው፡ግልገሎቻቸውን፡አጠቡ፤የወገኔ፡ልጅ፡ግን፡እንደ፡ ምድረ፡በዳ፡ሰጐን፡ጨካኝ፡ኾነች።
4ዳሌጥ።ጡት፡የሚጠባው፡የሕፃን፡ምላስ፡ከጥም፡የተነሣ፡ወደ፡ትናጋው፡ተጣበቀ፤ሕፃናት፡እንጀራ፡ ለመኑ፥የሚቈርስላቸውም፡የለም።
5ሄ።የጣፈጠ፡ነገር፡ይበሉ፡የነበሩ፡በመንገድ፡ጠፉ፤በቀይ፡ግምጃ፡ያድጉ፡የነበሩ፡የፍግ፡ክምር፡ዐቀፉ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
6ዋው።የማንም፡እጅ፡ሳይወድቅባት፡ድንገት፡ከተገለበጠች፡ከሰዶም፡ኀጢአት፡ይልቅ፡የወገኔ፡ሴት፡ልጅ፡ ኀጢአት፡በዛች።
7ዛይ።አለቃዎቿ፡ከበረዶ፡ይልቅ፡ጥሩ፥ከወተት፡ይልቅ፡ነጭ፡ነበሩ፤ገላቸው፡ከቀይ፡ዕንቍ፡ይልቅ፡ቀይ፡ ነበረ፥መልካቸውም፡እንደ፡ሰንፔር፡ነበረ።
8ሔት።ፊታቸው፡ከጥቀርሻ፡ይልቅ፡ጠቍሯል፥በመንገድም፡አልታወቁም፤ቍርበታቸው፡ወደ፡ዐጥንታቸው፡ ተጣብቋል፤ደርቋል፤እንደ፡ዕንጨት፡ኾኗል።
9ጤት።በሰይፍ፡የሞቱ፡በራብ፡ከሞቱት፡ይሻላሉ፤እነዚህ፡የምድርን፡ፍሬ፡ዐጥተው፡ተወግተውም፡ ቀጥነዋል።
10ዮድ።የርኅሩኆች፡ሴቶች፡እጆች፡ልጆቻቸውን፡ቀቅለዋል፤የወገኔ፡ሴት፡ልጅ፡በመቀጥቀጧ፡መብል፡ ኾኗቸው።
11ካፍ።እግዚአብሔር፡መዓቱን፡ፈጽሟል፥ጽኑ፡ቍጣውን፡አፍስሷል፤እሳትን፡በጽዮን፡ውስጥ፡ አቃጠለ፥መሠረቷንም፡በላች።
12ላሜድ።የምድር፡ነገሥታት፡በዓለምም፡የሚኖሩ፡ዅሉ፡አስጨናቂና፡ጠላት፡በኢየሩሳሌም፡በር፡እንዲገባ፡ አላመኑም።
13ሜም።የጻድቃንን፡ደም፡በውስጧ፡ስላፈሰሱ፡ስለነቢያቷ፡ኀጢአትና፡ስለካህናት፡በደል፡ነው።
14ኖን።ታውረው፡በመንገድ፡ላይ፡ተቅበዘበዙ፤ልብሳቸው፡እንዳይዳሰስ፡በደም፡ረክሰዋል።
15ሳምኬት።እናንተ፡ርኩሳን፥ራቁ፥ርቃችኹም፡ኺዱ፥አትንኩ፡ብለው፡ጮኹባቸው።በሸሹና፡በተቅበዘበዙ፡ ጊዜ፥በአሕዛብ፡መካከል።በዚህ፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡አይኖሩም፡ተባለ።
16ዔ።የእግዚአብሔር፡ፊት፡በተናቸው፡ርሱም፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡አይመለከታቸውም፤የካህናቱን፡ፊት፡ አላፈሩም፥ሽማግሌዎቹንም፡አላከበሩም።
17ፌ።ዐይናችን፡ወደ፡ከንቱ፡ረዳታችን፡ገና፡ሲመለከት፡ጠፍቷል፤በመቈየታችን፡ማዳን፡የማይቻለውን፡ ሕዝብ፡ጠብቀናል።
18ጻዴ።በአደባባያችን፡እንዳንኼድ፡ፍለጋችንን፡ተከተሉ፤ፍጻሜያችን፡ቀርቧል፥ዕድሜያችን፡ አልቋል፥ፍጻሜያችን፡ደርሷል።
19ቆፍ።አሳዳጆቻችን፡ከሰማይ፡ንስር፡ይልቅ፡ፈጣኖች፡ኾኑ፤በተራራዎች፡ላይ፡አሳደዱን፥በምድረ፡በዳ፡ ሸመቁብን።
20ሬስ።ስለ፡ርሱ፦በአሕዛብ፡መካከል፡በጥላው፡በሕይወት፡እንኖራለን፡ያልነው፡በእግዚአብሔር፡ የተቀባ፥የሕይወታችን፡እስትንፋስ፥በጕድጓዳቸው፡ተያዘ።
21ሳን።በዖፅ፡ምድር፡የምትኖሪ፡የኤዶምያስ፡ልጅ፡ሆይ፥ደስ፡ይበልሽ፡ሐሤትም፡አድርጊ፤ጽዋው፡ደግሞ፡ ወደ፡አንቺ፡ያልፋል፥አንቺም፡ትሰክሪያለሽ፡ትራቈቻለሽም።
22ታው።የጽዮን፡ልጅ፡ሆይ፥የበደልሽ፡ቅጣት፡ተፈጸመ፤ከእንግዲህ፡ወዲህ፡አያስማርክሽም።የኤዶምያስ፡ ልጅ፡ሆይ፥በደልሽን፡ይቀጣል፤ኀጢአትሽን፡ይገልጣል።