1አቤቱ፥የኾነብንን፡ዐስብ፤ተመልከት፡ስድባችንንም፡እይ።
2ርስታችን፡ለእንግዳዎች፥ቤቶቻችን፡ለሌላዎች፡ኾኑ።
3ድኻ፡አደጎችና፡አባት፡የሌለን፡ኾነናል፤እናቶቻችን፡እንደ፡መበለቶች፡ኾነዋል። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
4ውሃችንን፡በብር፡ጠጣን፡ዕንጨታችንን፡በዋጋ፡ገዛን።
5አሳዳጆቻችን፡በዐንገታችን፡ላይ፡ናቸው፤እኛ፡ደክመናል፡ዕረፍትም፡የለንም።
6ለግብጻውያንና፡ለአሶራውያን፡እንጀራ፡እንጠግብ፡ዘንድ፡እጅ፡ሰጠን።
7አባቶቻችን፡ኀጢአትን፡ሠሩ፡ዛሬም፡የሉም፤እኛም፡በደላቸውን፡ተሸከምን።
8ባሪያዎች፡ሠልጥነውብናል፤ከእጃቸው፡የሚታደገን፡የለም።
9ከምድረ፡በዳ፡ሰይፍ፡የተነሣ፡በሕይወታችን፡እንጀራችንን፡እናመጣለን።
10ከሚያቃጥል፡ከራብ፡ትኵሳት፡የተነሣ፡ቍርበታችን፡እንደ፡ምድጃ፡ጠቈረ።
11በጽዮን፡ሴቶችን፥በይሁዳም፡ከተማዎች፡ደናግልን፡አጐሰቈሉ።
12አለቃዎች፡በእጃቸው፡ተሰቀሉ፤የሽማግሌዎች፡ፊት፡አልታፈረም።
13ጕልማሳዎች፡ወፍጮን፡ተሸከሙ፥ልጆችም፡ከዕንጨት፡በታች፡ተሰናከሉ።
14ሽማግሌዎች፡ከአደባባይ፥ጕልማሳዎች፡ከበገናቸው፡ተሻሩ።
15የልባችን፡ደስታ፡ቀርቷል፤ዘፈናችን፡ወደ፡ልቅሶ፡ተለውጧል።
16አክሊል፡ከራሳችን፡ወድቋል፤ኀጢአት፡ሠርተናልና፥ወዮልን!
17ስለዚህ፥ልባችን፡ታሟ፟ል፤ስለዚህም፡ነገር፡ዐይናችን፡ፈዟ፟ል፤
18ስለጽዮን፡ተራራ፥ባድማ፡ኾናለችና፥ቀበሮዎችም፡ተመላልሰውባታልና።
19አቤቱ፥አንተ፡ለዘለዓለም፡ትኖራለኽ፤ዙፋንኽ፡ከትውልድ፡እስከ፡ትውልድ፡ነው።
20ስለ፡ምን፡ለዘለዓለም፡ትረሳናለኽ፧ስለ፡ምንስ፡ለረዥም፡ዘመን፡ትተወናለኽ፧
21አቤቱ፥ወዳንተ፡መልሰን፡እኛም፡እንመለሳለን፤ዘመናችንን፡እንደ፡ቀድሞ፡ዐድስ።
22ነገር፡ግን፥ፈጽመኽ፡ጥለኸናል፤እጅግ፡ተቈጥተኸናል፨ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org