Skip to content
← Malachi

Chapter 1 · Amharic

Malachi

1በሚልክያስ፡እጅ፡ለእስራኤል፡የኾነ፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ሸክም፡ይህ፡ነው።

2ወድጃችዃለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር፤እናንተ፡ግን፦በምን፡ወደድኸን፧ብላችዃል።ዔሳው፡የያዕቆብ፡ ወንድም፡አልነበረምን፧ይላል፡እግዚአብሔር፤ያዕቆብንም፡ወደድኹ፥ዔሳውንም፡ጠላኹ፤

3ተራራዎቹንም፡በረሓ፡አደረግዃቸው፥ርስቱንም፡ለምድረ፡በዳ፡ቀበሮዎች፡አሳልፌ፡ሰጠዃቸው።

4ኤዶምያስ፦እኛ፡ፈርሰናል፥ነገር፡ግን፥የፈረሰውን፡መልሰን፡እንሠራለን፡ቢል፥የሰራዊት፡ጌታ፡ እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እነርሱ፡ይሠራሉ፥እኔ፡ግን፡አፈርሳለኹ፤በሰዎችም፡ዘንድ፦የበደል፡ዳርቻና፡ እግዚአብሔር፡ለዘለዓለም፡የተቈጣው፡ሕዝብ፡ይባላል።

5ዐይኖቻችኹም፡ያያሉ፥እናንተም፦እግዚአብሔር፡ከእስራኤል፡ዳርቻ፡ወዲያ፡ታላቅ፡ይኹን፡ትላላችኹ።

6እናንተ፡ስሜን፡የምታቃልሉ፡ካህናት፡ሆይ፥ልጅ፡አባቱን፥ባሪያም፡ጌታውን፡ያከብራል፤እኔስ፡አባት፡ ከኾንኹ፡ክብሬ፡ወዴት፡አለ፧ጌታስ፡ከኾንኹ፡መፈራቴ፡ወዴት፡አለ፧ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡ እግዚአብሔር።እናንተም፦ስምኽን፡ያቃለልን፡በምንድር፡ነው፧ብላችዃል።

7በመሠዊያዬ፡ላይ፡ርኩስ፡እንጀራ፡ታቀርባላችኹ።እናንተም፦ያረከስንኽ፡በምንድር፡ ነው፧ብላችዃል።የእግዚአብሔር፡ገበታ፡የተነቀፈ፡ነው፡በማለታችኹ፡ነው።

8ዕውር፡መሥዋዕትንም፡ስታቀርቡ፡ይህ፡ክፉ፡አይደለምን፧ዐንካሳውንና፡የታመመውን፡ስታቀርቡ፡ይህ፡ክፉ፡ አይደለምን፧ያንን፡ለአለቃኽ፡አቅርብ፤በእውኑ፡ባንተ፡ደስ፡ይለዋልን፧ወይስ፡ፊትኽን፡ይቀበላልን፧ይላል፡ የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር።

9አኹንም፡ጸጋን፡ይሰጠን፡ዘንድ፡እግዚአብሔርን፡ለምኑ፤ይህ፡ከእጃችኹ፡የተሰጠ፡ሲኾን፡ከቶ፡ፊታችኹን፡ ይቀበላልን፧ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር።

10በመሠዊያዬ፡ላይ፡እሳትን፡በከንቱ፡እንዳታቃጥሉ፡ከእናንተ፡ዘንድ፡ደጅ፡የሚዘጋ፡ሰው፡ምነው፡በተገኘ! በእናንተ፡ደስ፡አይለኝም፥ቍርባንንም፡ከእጃችኹ፡አልቀበልም፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር።

11ከፀሓይ፡መውጫ፡ዠምሮ፡እስከ፡መግቢያዋ፡ድረስ፡ስሜ፡በአሕዛብ፡ዘንድ፡ታላቅ፡ ይኾናልና፤በየስፍራውም፡ለስሜ፡ዕጣን፡ያጥናሉ፥ንጹሕም፡ቍርባን፡ያቀርባሉ፤ስሜ፡በአሕዛብ፡ዘንድ፡ታላቅ፡ ይኾናልና፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር።

12እናንተ፡ግን፦የእግዚአብሔር፡ገበታ፡ርኩስ፡ነው፤ፍሬውና፡መብሉም፡የተናቀ፡ነው፡በማለታችኹ፡ አስነቀፋችኹት።

13እናንተ፦እንሆ፥ይህ፡ድካም፡ነው፡ብላችኹ፡ጢቅ፡አላችኹበት፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡ እግዚአብሔር፤በቅሚያ፡የያዛችኹትንም፡ዐንካሳውንም፡የታመመውንም፡አቅርባችዃል፤እንዲሁ፡ቍርባንን፡ ታመጣላችኹ፤በእውኑ፡ከእጃችኹ፡ይህን፡ልቀበለውን፧ይላል፡እግዚአብሔር።

14እኔ፡ታላቅ፡ንጉሥ፡ነኝና፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፥ስሜም፡በአሕዛብ፡ዘንድ፡የተፈራ፡ ነውና፥በመንጋው፡ውስጥ፡ተባት፡እያለው፡ለጌታ፡ተስሎ፡ነውረኛውን፡የሚሠዋ፡ሸንጋይ፡ሰው፡ርጉም፡ ይኹን። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source