1አኹንም፡እናንተ፡ካህናት፡ሆይ፥ይህ፡ትእዛዝ፡ለእናንተ፡ነው።
2ለስሜ፡ክብር፡ትሰጡ፡ዘንድ፡ባትሰሙ፥በልባችኹም፡ባታደርጉት፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡ እግዚአብሔር፥ርግማን፡እሰድ፟ባችዃለኹ፥በረከታችኹንም፡እረግማታለኹ፤አኹንም፡በልባችኹ፡ አላደረጋችኹትምና፡እኔ፡ረግሜያታለኹ።
3እንሆ፥ክንዳችኹን፡እገሥጻለኹ፥የመሥዋዕታችኹንም፡ፋንድያ፡በፊታችኹ፡ላይ፡እበትናለኹ፤ከርሱም፡ ጋራ፡በአንድነት፡ትወሰዳላችኹ።
4ቃል፡ኪዳኔ፡ከሌዊ፡ጋራ፡ይኾን፡ዘንድ፡ይህን፡ትእዛዝ፡እንደ፡ሰደድኹላችኹ፡ታውቃላችኹ፥ይላል፡ የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
5ቃል፡ኪዳኔ፡ከርሱ፡ጋራ፡የሕይወትና፡የሰላም፡ቃል፡ኪዳን፡ነበረ፤ይፈራ፡ዘንድም፡እነርሱን፡ ሰጠኹት፤ርሱም፡ፈራኝ፥ከስሜም፡የተነሣ፡ደነገጠ።
6የእውነት፡ሕግ፡በአፉ፡ውስጥ፡ነበረች፥በከንፈሩም፡ውስጥ፡በደል፡አልተገኘበትም፤ከእኔም፡ጋራ፡በሰላምና፡ በቅንነት፡ኼደ፥ብዙ፡ሰዎችንም፡ከኀጢአት፡መለሰ።
7ካህኑ፡የሰራዊት፡ጌታ፡የእግዚአብሔር፡መልእክተኛ፡ነውና፥ከንፈሮቹ፡ዕውቀትን፡ይጠብቁ፡ዘንድ፡ ይገ፟ባ፟ቸዋል፥ሰዎችም፡ሕግን፡ከአፉ፡ይፈልጉ፡ዘንድ፡ይገ፟ባ፟ቸዋል።
8እናንተ፡ግን፡ከመንገዱ፡ፈቀቅ፡ብላችዃል፤በሕግም፡ብዙ፡ሰዎችን፡አሰናክላችዃል፤የሌዊንም፡ቃል፡ ኪዳን፡አስነውራችዃል፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር።
9ስለዚህ፥መንገዴን፡እንዳልጠበቃችኹ፥በሕግም፡ለሰው፡ፊት፡እንዳዳላችኹ፡መጠን፥እኔ፡ደግሞ፡በሕዝብ፡ ዅሉ፡ፊት፡የተናቃችኹና፡የተዋረዳችኹ፡አድርጌያችዃለኹ።
10ለዅላችን፡አንድ፡አባት፡ያለን፡አይደለምን፧አንድ፡አምላክስ፡የፈጠረን፡አይደለምን፧የአባቶቻችንን፡ቃል፡ ኪዳን፡ለማስነቀፍ፡እኛ፡እያንዳንዳችን፡ወንድማችንን፡ስለ፡ምን፡አታለልን፧
11እግዚአብሔር፡የወደደውን፡መቅደስ፡ይሁዳ፡አርክሷልና፥የእንግዳውንም፡አምላክ፡ልጅ፡ሚስት፡አድርጎ፡ አግብቷልና፥ይሁዳ፡አታ፟ሏ፟ል፥በእስራኤልና፡በኢየሩሳሌም፡ውስጥ፡ርኵሰት፡ተሠርቷል።
12ይህን፡ከሚያደርግ፡ሰው፥እግዚአብሔር፡የሚጠራውንና፡የሚመልሰውን፡ለሰራዊትም፡ጌታ፡ለእግዚአብሔር፡ ቍርባን፡የሚያቀርበውን፡ከያዕቆብ፡ድንኳን፡ያጠፋል።
13ይህንም፡ደግሞ፡አድርጋችዃል፤እግዚአብሔር፡ቍርባኑን፡ዳግመኛ፡እንዳይመለከት፥ከእጃችኹም፡በደስታ፡ እንዳይቀበለው፡መሠዊያውን፡በእንባና፡በልቅሶ፡በሐዘንም፡ትከድናላችኹ።
14እናንተም፦ስለ፡ምንድር፡ነው፧ብላችዃል።ሚስትኽ፡ባልንጀራኽና፡የቃል፡ኪዳንኽ፡ሚስት፡ኾና፡ሳለች፡ ርሷን፡አታ፟ለኻ ፟ ታልና፥እግዚአብሔር፡በአንተና፡በልጅነት፡ሚስትኽ፡መካከል፡ምስክር፡ስለ፡ኾነ፡ነው።
15እግዚአብሔር፡የሕይወትን፡መንፈስ፡አንድ፡አድርጎ፡ጠብቆልን፡የለምን፧ርሱም፡የሚፈልገው፡ምንድር፡ ነው፧ዘር፡አይደለምን፧ስለዚህ፡መንፈሳችኹን፡ጠብቁ፥ማንም፡የልጅነት፡ሚስቱን፡አያታል፟።
16መፋታትን፡እጠላለኹ፥ይላል፡የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፥ልብሱንም፡በግፍ፡ሥራ፡የሚከድነውን፡ ሰው፡እጠላለኹ፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፤ስለዚህ፥እንዳታታልሉ፡መንፈሳችኹን፡ጠብቁ።
17እግዚአብሔርን፡በቃላችኹ፡አታክታችዃል።እናንተም፦ያታከትነው፡በምንድር፡ነው፧ብላችዃል።ክፉን፡ የሚያደርግ፡ዅሉ፡በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡መልካም፡ነው፥ርሱም፡በእነርሱ፡ደስ፡ይለዋል፤ወይስ።የፍርድ፡ አምላክ፡ወዴት፡አለ፧በማለታችኹ፡ነው።