Skip to content
← Malachi

Chapter 4 · Amharic

Malachi

1እንሆ፥እንደ፡ምድጃ፡እሳት፡የሚነድ፟፡ቀን፡ይመጣል፤ትዕቢተኛዎችና፡ኀጢአትን፡የሚሠሩ፡ዅሉ፡ገለባ፡ ይኾናሉ፤የሚመጣውም፡ቀን፡ያቃጥላቸዋል፥ሥርንና፡ቅርንጫፍንም፡አይተውላቸውም፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡ እግዚአብሔር።

2ነገር፡ግን፥ስሜን፡ለምትፈሩት፡ለእናንተ፡የጽድቅ፡ፀሓይ፡ትወጣላችዃለች፥ፈውስም፡በክንፎቿ፡ውስጥ፡ ይኾናል፤እናንተም፡ትወጣላችኹ፥እንደ፡ሰባ፟ም፡እንቦሳ፡ትፈነጫላችኹ።

3በምሠራበት፡ቀን፡በደለኛዎች፡ከእግራችኹ፡ጫማ፡በታች፡ዐመድ፡ይኾናሉና፡እናንተ፡ ትረግጧቸዋላችኹ፥ይላል፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር።

4ለእስራኤል፡ዅሉ፡ሥርዐትንና፡ፍርድን፡አድርጌ፡በኰሬብ፡ያዘዝኹትን፡የባሪያዬን፡የሙሴን፡ሕግ፡ዐስቡ።

5እንሆ፥ታላቁና፡የሚያስፈራው፡የእግዚአብሔር፡ቀን፡ሳይመጣ፡ነቢዩን፡ኤልያስን፡እልክላችዃለኹ።

6መጥቼም፡ምድርን፡በርግማን፡እንዳልመታ፡ርሱ፡የአባቶችን፡ልብ፡ወደ፡ልጆች፥የልጆችንም፡ልብ፡ወደ፡ አባቶች፡ይመልሳል፨ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source