Skip to content
← Micah

Chapter 7 · Amharic

Micah

1የዛፍ፡ፍሬና፡የወይን፡ፍሬ፡ከተለቀሙ፡በዃላ፡እንደ፡ቀረው፡ቃርሚያ፡ኾኛለኹና፡ወዮልኝ! መብል፡ የሚኾን፡ዘለላ፥ነፍሴም፡የተመኘችው፡በመዠመሪያ፡የበሰለው፡በለስ፡የለም።

2ደግ፡ሰው፡ከምድር፡ጠፍቷል፥በሰውም፡መካከል፡ቅን፡የለም፤ዅሉ፡ደምን፡ለማፍሰስ፡ያደባሉ፥ሰውም፡ ዅሉ፡ወንድሙን፡በመረብ፡ለመያዝ፡ይከታተለዋል።

3እጆቻቸውን፡ለክፋት፡ያነሣሉ፤አለቃውና፡ፈራጁ፡ጕቦን፡ይፈልጋሉ፥ትልቁም፡ሰው፡እንደ፡ነፍሱ፡ምኞት፡ ይናገራል፤እንዲሁም፡ክፋትን፡ይጐነጕናሉ።

4ከነርሱም፡ዅሉ፡የተሻለው፡ርሱ፡እንደ፡አሜከላ፡ነው፥ከዅሉም፡ቅን፡የኾነው፡እንደ፡ኵርንችት፡ ነው፤ጠባቂዎችኽ፡የሚጐበኙበት፡ቀን፡መጥቷል፤አኹን፡ይሸበራሉ።

5ባልንጀራን፡አትመኑ፥በወዳጅም፡አትታመኑ፤የአፍኽን፡ደጅ፡በብብትኽ፡ከምትተኛው፡ጠብቅ።

6ወንድ፡ልጅ፡አባቱን፡ይንቃልና፥ሴት፡ልጅ፡በእናቷ፡ላይ፥ምራቲቱም፡በአማቷ፡ላይ፡ትነሣለችና፥የሰው፡ ጠላቶች፡የቤቱ፡ሰዎች፡ናቸውና። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

7እኔ፡ግን፡ወደ፡እግዚአብሔር፡እመለከታለኹ፥የመድኀኒቴንም፡አምላክ፡ተስፋ፡አደርጋለኹ፤አምላኬም፡ ይሰማኛል።

8ጠላቴ፡ሆይ፥ብወድቅ፡እነሣለኹና፥በጨለማም፡ብቀመጥ፡እግዚአብሔር፡ብርሃን፡ይኾንልኛልና፥በእኔ፡ ላይ፡ደስ፡አይበልሽ።

9በእግዚአብሔር፡ላይ፡ኀጢአት፡ሠርቻለኹና፡እስኪሟገትልኝ፡ድረስ፥ፍርድን፡ለእኔ፡እስኪያደርግ፡ድረስ፡ ቍጣውን፡እታገሣለኹ።ወደ፡ብርሃን፡ያወጣኛል፥ጽድቅንም፡አያለኹ።

10ጠላቴም፡ታያለች፥እኔንም፦አምላክኽ፡እግዚአብሔር፡ወዴት፡ነው፧ያለች፡በዕፍረት፡ትከደናለች።

11ዐይኖቼ፡ይመለከቷታል፤አኹን፡እንደ፡መንገድ፡ጭቃ፡ትረገጣለች።ቅጥርሽ፡በሚሠራበት፡በዚያ፡ቀን፡ ድንበርሽ፡ትስፋፋለች።

12በዚያ፡ቀን፡ከአሶርና፡ከግብጽ፡ከተማዎች፥ከግብጽ፡እስከ፡ወንዙ፥ከባሕርም፡እስከ፡ባሕር፥ከተራራም፡ እስከ፡ተራራ፡ድረስ፡ወደ፡አንቺ፡ይመጣሉ።

13ምድሪቱ፡ግን፡በሚኖሩባት፡በሥራቸው፡ፍሬ፡ምክንያት፡ባድማ፡ትኾናለች።

14በቀርሜሎስ፡መካከል፡ባለው፡ዱር፡ብቻቸውን፡የተቀመጡት፡ሰዎችኽ፥የርስትኽን፡በጎች፥በበትርኽ፡ አግድ፤እንደ፡ቀደመውም፡ዘመን፡በበሳንና፡በገለዓድ፡ይሰማሩ።

15ከግብጽ፡ምድር፡እንደ፡ወጣኽበት፡ዘመን፡ተኣምራትን፡አሳያቸዋለኹ።

16አሕዛብ፡አይተው፡በጕልበታቸው፡ዅሉ፡ያፍራሉ፤እጃቸውን፡በአፋቸው፡ላይ፡ያኖራሉ፥ዦሯቸውም፡ ትደነቍራለች፤

17እንደ፡እባብም፡መሬት፡ይልሳሉ፥እንደምድርም፡ተንቀሳቃሾች፡እየተንቀጠቀጡ፡ከግንባቸው፡ ይመጣሉ፤ፈርተውም፡ወደ፡አምላካችን፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ይመጣሉ፥ስለ፡አንተም፡ይፈራሉ።

18በደልን፡ይቅር፡የሚል፥የርስቱንም፡ቅሬታ፡ዐመፅ፡የሚያሳልፍ፡እንደ፡አንተ፡ያለ፡አምላክ፡ማን፡ ነው፧ምሕረትን፡ይወዳ፟ልና፥ቍጣውን፡ለዘለዓለም፡አይጠብቅም።

19ተመልሶ፡ይምረናል፤ክፋታችንንም፡ይጠቀጥቃል፥ኀጢአታችንንም፡በባሕሩ፡ጥልቅ፡ይጥለዋል።

20ከቀድሞ፡ዘመን፡ዠምረኽ፡ለአባቶቻችን፡የማልኽላቸውን፡እውነት፡ለያዕቆብ፥ምሕረትንም፡ለአብርሃም፡ ታደርጋለኽ፨ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source