Skip to content
← Micah

Chapter 6 · Amharic

Micah

1አኹን፦ተነሣ፥በተራራዎችም፡ፊት፡ተፋረድ፥ኰረብታዎችም፡ቃልኽን፡ይስሙ፡ብሎ፡እግዚአብሔር፡ የሚለውን፡ስሙ።

2ተራራዎች፡ሆይ፥ጠንካራዎች፡የምድር፡መሠረቶችም፡ሆይ፥እግዚአብሔር፡ከሕዝቡ፡ጋራ፡ክርክር፡ አለውና፥ከእስራኤልም፡ጋራ፡ይፋረዳልና፥የእግዚአብሔርን፡ክርክር፡ስሙ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

3ሕዝቤ፡ሆይ፥ምን፡አድርጌኻለኹ፧በምንስ፡አድክሜኻለኹ፧መስክርብኝ።

4ከግብጽ፡ምድር፡አውጥቼኻለኹ፥ከባርነት፡ቤትም፡ተቤዥቼኻለኹ፤በፊትኽም፡ሙሴንና፡አሮንን፡ ማርያምንም፡ልኬልኽ፡ነበር።

5ሕዝቤ፡ሆይ፥የሞዐብ፡ንጉሥ፡ባላቅ፡የመከረውን፥የቢዖርም፡ልጅ፡በለዓም፡የመለሰለትን፡አኹን፡ ዐስብ፤የእግዚአብሔርንም፡የጽድቅ፡ሥራ፡ታውቅ፡ዘንድ፡ከሰጢም፡ዠምሮ፡እስከ፡ገልገላ፡ድረስ፡ዐስብ።

6ምን፡ይዤ፡ወደእግዚአብሔር፡ፊት፡ልምጣና፡በልዑል፡አምላክ፡ፊት፡ልስገድ፧የሚቃጠለውን፡ መሥዋዕትና፡የአንዱን፡ዓመት፡ጥጃ፡ይዤ፡በፊቱ፡ልምጣን፧

7እግዚአብሔርስ፡በሺሕ፡አውራ፡በጎች፡ወይስ፡በእልፍ፡የዘይት፡ፈሳሾች፡ደስ፡ይለዋልን፧ወይስ፡የበኵር፡ ልጄን፡ስለ፡በደሌ፥የሆዴንም፡ፍሬ፡ስለነፍሴ፡ኀጢአት፡እሰጣለኹን፧

8ሰው፡ሆይ፥መልካሙን፡ነግሮኻል፤እግዚአብሔርም፡ከአንተ፡ዘንድ፡የሚሻው፡ምንድር፡ነው፧ፍርድን፡ ታደርግ፡ዘንድ፥ምሕረትንም፡ትወድ፟፡ዘንድ፥ከአምላክኽም፡ጋራ፡በትሕትና፡ትኼድ፡ዘንድ፡አይደለምን፧

9የእግዚአብሔር፡ድምፅ፡ከተማዪቱን፡ይጠራታል፤ስምኽን፡መፍራት፡ጥበብ፡ነው፤የመቅሠፍትን፡ በትር፥ርሱንም፡ያዘጋጀ፡ማን፡እንደ፡ኾነ፡ስሙ።

10በእውኑ፡በኀጢአተኛ፡ቤት፡የኀጢአት፡መዝገብ፥የተጸየፈም፡ውሸተኛ፡መስፈሪያ፡ገና፡አለ፡ይኾን፧

11በአባይ፡ሚዛንና፡በከረጢት፡ባለ፡በተንኰል፡መመዘኛ፡ንጹሕ፡እኾናለኹን፧

12ባለጠጋዎቿን፡ግፍ፡ሞልቶባቸዋል፤በርሷም፡የሚኖሩ፡በሐሰት፡ተናግረዋል፥ምላሳቸውም፡በአፋቸው፡ ውስጥ፡ተንኰለኛ፡ነው።

13ስለዚህ፥እኔ፡ደግሞ፡በክፉ፡ቍስል፡መታኹኽ፤ስለ፡ኀጢአትኽም፡አፈረስኹኽ።

14ትበላለኽ፥ነገር፡ግን፥አትጠግብም፤ችጋርኽም፡በመካከልኽ፡ይኾናል፤ትወስዳለኽ፥ነገር፡ ግን፥አታድንም፤የምታድነውንም፡ለሰይፍ፡እሰጣለኹ።

15ትዘራለኽ፥ነገር፡ግን፥አታጭድም፤ወይራውንም፡ትጨምቃለኽ፥ነገር፡ግን፥ዘይቱን፡አትቀባም፤ወይኑንም፡ ትጨምቃለኽ፥ነገር፡ግን፥የወይን፡ጠጁን፡አትጠጣም።

16አንተን፡ለጥፋት፥በርሷም፡የሚኖሩትን፡ለማፏጫ፡እሰጥ፡ዘንድ፡የዘንበሪን፡ሥርዐትና፡የአክአብን፡ቤት፡ ሥራ፡ዅሉ፡ጠብቃችዃል፥በምክራቸውም፡ኼዳችዃል፤የሕዝቤንም፡ስድብ፡ትሸከማላችኹ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source