Skip to content
← Micah

Chapter 5 · Amharic

Micah

1የጭፍራዎች፡ሴት፡ልጅ፡ሆይ፥ጭፍራዎችሽን፡አኹን፡ሰብስቢ፤ከቦ፟፡አስጨንቆናል፤የእስራኤልን፡ፈራጅ፡ ጕንጩን፡በበትር፡ይመታሉ።

2አንቺም፡ቤተ፡ልሔም፡ኤፍራታ፡ሆይ፥አንቺ፡በይሁዳ፡አእላፋት፡መካከል፡ትኾኚ፡ዘንድ፡ታናሽ፡ ነሽ፤ከአንቺ፡ግን፡አወጣጡ፡ከቀድሞ፡ዠምሮ፡ከዘለዓለም፡የኾነ፥በእስራኤልም፡ላይ፡ገዢ፡የሚኾን፡ ይወጣልኛል።

3ስለዚህ፥ወላጂቱ፡እስከምትወልድበት፡ጊዜ፡ድረስ፡አሳልፎ፡ይሰጣቸዋል፤የቀሩትም፡ወንድሞቹ፡ወደ፡ እስራኤል፡ልጆች፡ይመለሳሉ።

4ርሱም፡ይቆማል፥በእግዚአብሔርም፡ኀይል፡በአምላኩ፡በእግዚአብሔር፡ስም፡ግርማ፡መንጋውን፡ ይጠብቃል፤እነርሱም፡ይኖራሉ፤ርሱ፡አኹን፡እስከምድር፡ዳርቻ፡ድረስ፡ታላቅ፡ይኾናልና።

5ይህም፡ለሰላም፡ይኾናል፤አሶራዊውም፡ወደ፡አገራችን፡በገባ፡ጊዜ፥ምድራችንንም፡በረገጠ፡ጊዜ፡ሰባት፡ እረኛዎችና፡ስምንት፡አለቃዎች፡እናስነሣበታለን።

6የአሶርንም፡አገር፡በሰይፍ፥የናምሩድንም፡አገር፡በመግቢያው፡ውስጥ፡ያፈርሳሉ፤አሶራዊውም፡ወደ፡ አገራችን፡በገባ፡ጊዜ፥ዳርቻዎቻችንንም፡በረገጠ፡ጊዜ፡ርሱ፡ይታደገናል።

7የያዕቆብም፡ቅሬታ፡በብዙ፡አሕዛብ፡መካከል፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡እንደሚወርድ፡ጠል፥በሣር፡ላይ፡ እንደሚወርድ፡ካፊያ፤ሰውንም፡እንደማይጠብቅ፥የሰውንም፡ልጆች፡ተስፋ፡እንደማያደርግ፡ይኾናል።

8በዱር፡አራዊትም፡መካከል፡እንዳለ፡አንበሳ፥በበጎች፡መንጋም፡መካከል፡ዐልፎ፡ እንደሚረግጥ፥የሚታደግም፡ሳይኖር፡እንደሚነጥቅ፡እንደ፡አንበሳ፡ደቦል፥እንዲሁ፡የያዕቆብ፡ቅሬታ፡በአሕዛብና፡ በብዙ፡ወገኖች፡መካከል፡ይኾናል።

9እጅኽ፡በጠላቶችኽ፡ላይ፡ከፍ፡ከፍ፡ትበል፥ጠላቶችኽም፡ዅሉ፡ይጥፉ።

10በዚያም፡ቀን፡ፈረሶችኽን፡ከመካከልኽ፡አጠፋለኹ፥ሠረገላዎችኽንም፡እሰብራለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር፤

11የምድርኽንም፡ከተማዎች፡አጠፋለኹ፥ምሽጎችኽንም፡ዅሉ፡አፈርሳለኹ፤

12መተትንም፡ከእጅኽ፡አጠፋለኹ፥ሟርተኛዎችም፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡አይኾኑልኽም፤

13የተቀረጹትን፡ምስሎችኽንና፡ሐውልቶችኽን፡ከመካከልኽ፡አጠፋለኹ፥ለእጅኽም፡ሥራ፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡ አትሰግድም፤

14የማምለኪያ፡ዐጸዶችኽንም፡ከመካከልኽ፡እነቅላለኹ፥ከተማዎችኽንም፡አፈርሳለኹ።

15ባልሰሙም፡አሕዛብ፡ላይ፡በቍጣና፡በመዓት፡እበቀላለኹ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source