Skip to content
← Micah

Chapter 4 · Amharic

Micah

1በመጨረሻውም፡ዘመን፡የእግዚአብሔር፡ቤት፡ተራራ፡በተራራዎች፡ራስ፡ላይ፡ጸንቶ፡ ይቆማል፥ከኰረብታዎችም፡በላይ፡ከፍ፡ከፍ፡ይላል፤አሕዛብም፡ወደ፡ርሱ፡ይጐርፋሉ።

2ከጽዮን፡ሕግ፥ከኢየሩሳሌምም፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ይወጣልና፥ብዙዎች፡አሕዛብ፡ ኼደው፦ኑ፥ወደእግዚአብሔር፡ተራራ፥ወደያዕቆብ፡አምላክ፡ቤት፡እንውጣ፤ርሱም፡መንገዱን፡ ያስተምረናል፥በፍለጋውም፡እንኼዳለን፡ይላሉ።

3በብዙዎችም፡አሕዛብ፡መካከል፡ይፈርዳል፥በሩቅም፡ባሉ፡በብርቱዎች፡አሕዛብ፡ላይ፡ ይበይናል፤ሰይፋቸውንም፡ማረሻ፥ጦራቸውንም፡ማጭድ፡ለማድረግ፡ይቀጠቅጣሉ፤ሕዝብም፡በሕዝብ፡ላይ፡ ሰይፍ፡አያነሣም፡ከእንግዲህም፡ወዲህ፡ሰልፍ፡አይማሩም።

4የሰራዊት፡ጌታ፡የእግዚአብሔር፡አፍም፡ተናግሯልና፥ሰው፡እያንዳንዱ፡ከወይኑና፡ከበለሱ፡በታች፡ ይቀመጣል፥የሚያስፈራውም፡የለም።

5ሕዝብም፡ዅሉ፡እያንዳንዱ፡በያምላኩ፡ስም፡ይኼዳል፥እኛም፡በአምላካችን፡በእግዚአብሔር፡ስም፡ ለዘለዓለም፡እንኼዳለን።

6በዚያ፡ቀን፡ዐንካሳዪቱን፡እሰበስባለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር፥የባከነችውንና፡ያስጨነቅዃትንም፡አከማቻለኹ፤

7ዐንካሳዪቱንም፡ለቅሬታ፥ወደ፡ሩቅም፡የተጣለችውን፡ለብርቱ፡ሕዝብ፡አደርጋታለኹ፤ከዚያም፡ወዲያ፡ እስከ፡ዘለዓለም፡ድረስ፡እግዚአብሔር፡በጽዮን፡ተራራ፡በእነርሱ፡ላይ፡ይነግሣል።

8አንተም፡የመንጋ፡ግንብ፡ሆይ፥የጽዮን፡ሴት፡ልጅ፡ዐምባ፥ወዳንተ፡ትመጣለች፤የቀደመችው፡ ግዛት፥የኢየሩሳሌም፡ሴት፡ልጅ፡መንግሥት፡ትደርሳለች።

9አኹንስ፡ለምን፡ትጮኺያለሽ፧እንደምትወልድ፡ሴት፡ምጥ፡የደረሰብሽ፥ንጉሥ፡ስለሌለሽ፡ነውን፧ወይስ፡ መካሪ፡ስለ፡ጠፋብሽ፡ነውን፧

10የጽዮን፡ልጅ፡ሆይ፥እንደምትወልድ፡ሴት፡አምጠሽ፡ውለጂ፤አኹን፡ከከተማ፡ትወጫለሽና፥በሜዳም፡ ትቀመጫለሽ፥ወደ፡ባቢሎንም፡ትደርሻለሽ፤በዚያም፡ያድንሻል፥በዚያም፡እግዚአብሔር፡ከጠላቶችሽ፡እጅ፡ ይቤዥሻል።

11አኹንም፦ርኩስ፡ትኹን፥ዐይናችንም፡በጽዮን፡ላይ፡ይይ፡የሚሉ፡ብዙ፡አሕዛብ፡ባንቺ፡ላይ፡ ተሰብስበዋል።

12ነገር፡ግን፥የእግዚአብሔርን፡ዐሳብ፡አያውቁም፥ምክሩንም፡አያስተውሉም፤እንደ፡ነዶ፡ወደ፡ዐውድማ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org አከማችቷቸዋልና።

13የጽዮን፡ልጅ፡ሆይ፥ቀንድሽን፡ብረት፥ጥፍርሽንም፡ናስ፡አደርጋለኹና፡ተነሺ፥አኺጂ፤ብዙ፡አሕዛብንም፡ ታደቂ፟ያለሽ፤ትርፋቸውንም፡ለእግዚአብሔር፥ሀብታቸውንም፡ለምድር፡ዅሉ፡ጌታ፡ትቀድሻለሽ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source