Skip to content
← Micah

Chapter 3 · Amharic

Micah

1እንዲህም፡አልኹ።የያዕቆብ፡አለቃዎችና፡የእስራኤል፡ቤት፡ገዢዎች፡ሆይ፥እባካችኹ፡ስሙኝ፤ፍርድን፡ ታውቁ፡ዘንድ፡አይገ፟ባ፟ችኹምን፧

2መልካሙን፡ጠልታችዃል፥ክፉውንም፡ወዳ፟ችዃል፤ቍርበታቸውን፡ገፋ፟ችዃቸዋል፥ሥጋቸውንም፡ ከዐጥንታቸው፡ለያይታችዃል፤

3የሕዝቤን፡ሥጋ፡በልታችዃል፥ቍርበታቸውንም፡ገፋ፟ችዃቸዋል፥ዐጥንታቸውንም፡ሰብራችዃል፤ለአፍላል፡ እንደሚኾን፡ሥጋ፡ለድስትም፡እንደሚኾን፡ሙዳ፡ቈራረጣችዃቸው።

4የዚያን፡ጊዜ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ይጮኻሉ፥ርሱም፡አይሰማቸውም፤ሥራቸውንም፡ክፉ፡ አድርገዋልና፥በዚያን፡ጊዜ፡ፊቱን፡ከነርሱ፡ይሰውራል።

5እግዚአብሔር፡ሕዝቤን፡ስለሚያስቱ፡ነቢያት፡እንዲህ፡ይላል፤በጥርሳቸው፡ሲነክሱ፡በሰላም፡ ይሰብካሉ፤በአፋቸው፡ግን፡አንዳች፡በማይሰጥ፡ሰው፡ላይ፡ሰልፍን፡ያስቡበታል።

6ስለዚህ፥ሌሊት፡ይኾንባችዃል፡እንጂ፡ራእይ፡አይኾንላችኹም፤ጨለማም፡ይኾንባችዃል፡እንጂ፡ አታሟርቱም፤ፀሓይም፡በነቢያት፡ላይ፡ትገባለች፥ቀኑም፡ይጠቍርባቸዋል።

7ከእግዚአብሔርም፡ዘንድ፡መልስ፡የለምና፡ባለራእዩቹ፡ያፍራሉ፥ሟርተኛዎችም፡ይዋረዳሉ፤ዅሉም፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ከንፈራቸውን፡ይሸፍናሉ።

8እኔ፡ግን፡በደሉን፡ለያዕቆብ፥ኀጢአቱንም፡ለእስራኤል፡እነግር፡ዘንድ፡በእግዚአብሔር፡መንፈስ፡ኀይልንና፡ ፍርድን፡ብርታትንም፡ተሞልቻለኹ።

9ፍርድን፡የምትጠሉ፡ቅን፡ነገርንም፡ዅሉ፡የምታጣምሙ፡እናንተ፡የያዕቆብ፡ቤት፡አለቃዎችና፡የእስራኤል፡ ቤት፡ገዢዎች፡ሆይ፥እባካችኹ፡ይህን፡ስሙ።

10ጽዮንን፡በደም፥ኢየሩሳሌምንም፡በኀጢአት፡ይሠራሉ።

11አለቃዎቿ፡በጕቦ፡ይፈርዳሉ፥ካህናቷም፡በዋጋ፡ያስተምራሉ፥ነቢያቷም፡በገንዘብ፡ያሟርታሉ፤ከዚህም፡ ጋራ።እግዚአብሔር፡በመካከላችን፡አይደለምን፧ክፉ፡ነገር፡ምንም፡አይመጣብንም፡እያሉ፡በእግዚአብሔር፡ ይታመናሉ።

12ስለዚህ፥በእናንተ፡ምክንያት፡ጽዮን፡እንደ፡ዕርሻ፡ትታረሳለች፥ኢየሩሳሌምም፡የድንጋይ፡ክምር፡ ትኾናለች፥የቤቱም፡ተራራ፡እንደ፡ዱር፡ከፍታ፡ይኾናል።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source