1በመኝታቸው፡ላይ፡በደልን፡ለሚያስቡ፡ክፋትንም፡ለሚያደርጉ፡ወዮላቸው! ኀይል፡በእጃቸው፡ነውና፥ሲነጋ፡ ይፈጽሙታል። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
2በዕርሻው፡ላይ፡ይመኛሉ፥በግዴታም፡ይይዙታል፤በቤቶችም፡ላይ፡ይመኛሉ፥ይወስዷቸውማል፤ሰውንና፡ ቤቱን፥ሰውንና፡ርስቱንም፡ይነጥቃሉ።
3ስለዚህ፥እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እንሆ፥በዚህ፡ወገን፡ላይ፡በክፉ፡ዐስባለኹ፥ከዚያም፡ ዐንገታችኹን፡አታነሡም፤ዘመኑም፡ክፉ፡ነውና፥ቀጥ፡ብላችኹ፡አትኼዱም።
4በዚያ፡ቀን፡በምሳሌ፡ይመስሉባችዃል፥በጽኑ፡ልቅሶም፡ያለቅሱላችዃል፤እነርሱም፦ፈጽመን፡ ጠፍተናል፤የሕዝቤን፡ዕድል፡ፈንታ፡ይሰፍራል፥ርሱንም፡የሚከለክል፡የለም፤ዕርሻችንን፡ለዐመፀኛዎች፡ ይከፍላል፡ይላሉ።
5ስለዚህ፥በእግዚአብሔር፡ጉባኤ፡መካከል፡በዕጣ፡ገመድ፡የሚጥል፡አይኖርኽም።
6ትንቢት፡አትናገሩ፡ብለው፡ይናገራሉ፤በእነዚህ፡ላይ፡ትንቢት፡አይናገሩም፥ስድብም፡አይርቅም።
7የያዕቆብ፡ቤት፡የተባልኽ፡ሆይ፥በእውኑ፡የእግዚአብሔር፡መንፈስ፡የማይታገሥ፡ነውን፧ወይስ፡ሥራው፡ እንደዚች፡ናትን፧ቃሌስ፡በቅን፡ለሚኼድ፡በጎነት፡አያደርግምን፧
8ነገር፡ግን፥ከቅርብ፡ጊዜ፡ዠምሮ፡ሕዝቤ፡እንደ፡ጠላት፡ኾኖ፡ተነሥቷል፤ቀሚስንና፡መጐናጸፊያን፡ ገፈፋችኹ፤ሳይፈሩም፤የሚያልፉትን፡ከሰልፍ፡እንደሚመለሱ፡አደረጋችዃቸው።
9የሕዝቤንም፡ሴቶች፡ከተሸለሙ፡ቤቶቻቸው፡አሳደዳችዃቸው፤ከሕፃናታቸውም፡ክብሬን፡ለዘለዓለም፡ ወሰዳችኹ።
10በዚህ፡ዕረፍት፡የላችኹምና፡ተነሥታችኹ፡ኺዱ፤በርኵሰት፡ምክንያት፡ክፉ፡ጥፋት፡ታጠፋችዃለች።
11ነፋስንም፡ተከትሎ፦ስለወይን፡ጠጅና፡ስለ፡ስካር፡ትንቢት፡እናገርልኻለኹ፡ብሎ፡ሐሰትን፡የሚናገር፡ ሰው፡ቢኖር፡ርሱ፡ለዚህ፡ሕዝብ፡ነቢይ፡ይኾናል።
12ያዕቆብ፡ሆይ፥ዅለንተናኽን፡ፈጽሞ፡እሰበስባለኹ፥የእስራኤልንም፡ቅሬታ፡ፈጽሞ፡አከማቻለኹ፤እንደ፡ ባሶራ፡በጎችና፡እንደ፡መንጋ፡በማሰማሪያቸው፡ውስጥ፡በአንድነት፡አኖራቸዋለኹ፤ከሰው፡ብዛት፡የተነሣ፡ ድምፃቸውን፡ያሰማሉ።
13ሰባሪው፡በፊታቸው፡ወጥቷል፤እነርሱም፡ሰብረው፡ወደ፡በሩ፡አልፈዋል፥በርሱም፡በኩል፡ ወጥተዋል፤ንጉሣቸውም፡በፊታቸው፡ዐልፏል፥እግዚአብሔርም፡በራሳቸው፡ላይ፡ነው።