1የሐካልያ፡ልጅ፡የነሐምያ፡ቃል፦በኻያኛው፡ዓመት፡በካሴሉ፡ወር፡እንዲህ፡ኾነ፤
2እኔ፡በሱሳ፡ግንብ፡ሳለኹ፥ከወንድሞቼ፡አንዱ፡ዐናኒ፡ከርሱም፡ጋራ፡ሌላዎች፡ሰዎች፡ከይሁዳ፡ መጡ፤እኔም፡የዳኑትን፡ከምርኮ፡የተረፉትን፡የአይሁድን፡ነገር፡የኢየሩሳሌምንም፡ነገር፡ጠየቅዃቸው።
3እነርሱም፦በዚያ፡ስፍራ፡ያሉት፡ከምርኮ፡የተረፉት፡ቅሬታዎች፡በታላቅ፡መከራና፡ስድብ፡ አሉ፤የኢየሩሳሌምም፡ቅጥር፡ፈርሷል፥በሮቿም፡በእሳት፡ተቃጥለዋል፡አሉኝ።
4ይህንም፡ቃል፡በሰማኹ፡ጊዜ፡ተቀምጬ፡አለቀስኹ፥ዐያሌ፡ቀንም፡አዝን፡ነበር፤በሰማይም፡አምላክ፡ፊት፡ እጾምና፡እጸልይ፡ነበር፥
5እንዲህም፡አልኹ፦አቤቱ፡የሰማይ፡አምላክ፡ሆይ፥ለሚወዱኽና፡ትእዛዝኽን፡ለሚያደርጉ፡ቃል፡ኪዳንንና፡ ምሕረትን፡የምትጠብቅ፥ታላቅና፡የተፈራኽ፡አምላክ፡ሆይ፥
6እኔ፡ባሪያኽ፡ዛሬ፡በፊትኽ፡ስለ፡ባሪያዎችኽ፡ስለእስራኤል፡ልጆች፡ሌሊትና፡ቀን፡የምጸልየውን፡ጸሎት፡ ትሰማ፡ዘንድ፡ዦሮኽ፡ያድምጥ፥ዐይኖችኽም፡ይከፈቱ፤ባንተ፡ላይም፡ያደረግነውን፡የእስራኤልን፡ልጆች፡ ኀጢአት፡እናዘዝልኻለኹ፤እኔና፡የአባቴም፡ቤት፡በድለናል።
7እኛም፡ባንተ፡ላይ፡እጅግ፡ክፉ፡ሠርተናል፤ለባሪያኽም፡ለሙሴ፡ያዘዝኸውን፡ትእዛዝና፡ሥርዐት፡ሕግም፡ አልጠበቅንም።
9አኹንም፡ብትተላለፉ፡በአሕዛብ፡መካከል፡እበትናችዃለኹ፤ወደ፡እኔ፡ብትመለሱ፡ግን፡ትእዛዜንም፡ ብትጠብቁ፡ብታደርጓትም፥ከእናንተ፡ሰዎች፡እስከሰማይ፡ዳርቻ፡ድረስ፡ምንም፡ቢበተኑ፡ከዚያ፡ እሰበስባቸዋለኹ፥ስሜም፡ይኖርበት፡ዘንድ፡ወደ፡መረጥኹት፡ስፍራ፡አመጣቸዋለኹ፡ብለኽ፡ለባሪያኽ፡ለሙሴ፡ ያዘዝኸውን፡ቃል፡እባክኽ፡ዐስብ።
10እነዚህም፡በታላቅ፡ኀይልኽና፡በብርቱ፡እጅኽ፡የተቤዠኻቸው፡ባሪያዎችኽና፡ሕዝብኽ፡ናቸው።
11ጌታ፡ሆይ፥ዦሮኽ፡የባሪያኽን፡ጸሎት፥ስምኽንም፡ይፈሩ፡ዘንድ፡የሚወዱትን፥የባሪያዎችኽን፡ጸሎት፡ ያድምጥ፤ዛሬም፡ለባሪያኽ፡አከናውንለት፥በዚህም፡ሰው፡ፊት፡ምሕረትን፡ስጠው።እኔም፡ለንጉሡ፡ጠጅ፡ አሳላፊው፡ነበርኹ።