1በይሁዳ፡ንጉሥ፡በዓሞጽ፡ልጅ፡በኢዮስያስ፡ዘመን፡ወደሕዝቅያስ፡ልጅ፡ወደአማርያ፡ልጅ፡ወደጎዶልያስ፡ ልጅ፡ወደኵሲ፡ልጅ፡ወደ፡ሶፎንያስ ፡የመጣ፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ይህ፡ነው፦
2ነገርን፡ዅሉ፡ከምድር፡ፊት፡ፈጽሜ፡አጠፋለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
3ሰውንና፡እንስሳን፡አጠፋለኹ፤የሰማይን፡ወፎችና፡የባሕርን፡ዓሣዎች፡ማሰናከያንም፡ከኀጢአተኛዎች፡ጋራ፡ አጠፋለኹ፤ሰውንም፡ከምድር፡ፊት፡እቈርጣለኹ፥ይላል፡እግዚአብሔር።
4እጄንም፡በይሁዳ፡ላይ፡በኢየሩሳሌምም፡በሚኖሩት፡ዅሉ፡ላይ፡እዘረጋለኹ፤ከዚህም፡ስፍራ፡የበዓልን፡ ቅሬታና፡የጣዖታቱን፡ካህናት፡ስም፡አጠፋለኹ፤
5በሰገነትም፡ላይ፡ለሰማይ፡ሰራዊት፡የሚሰግዱትን፥በእግዚአብሔርና፡በንጉሣቸው፡በሚልኮም፡ምለው፡ የሚሰግዱትን፥
6እግዚአብሔርንም፡ከመከተል፡የተመለሱትን፥እግዚአብሔርንም፡ያልፈለጉትንና፡ያልጠየቁትን፡አጠፋለኹ።
7የእግዚአብሔር፡ቀን፡ቀርቧልና፥እግዚአብሔር፡መሥዋዕትን፡አዘጋጅቷልና፥የጠራቸውንም፡ ቀድሷልና፥በጌታ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ዝም፡በሉ።
8በእግዚአብሔርም፡መሥዋዕት፡ቀን፡አለቃዎችንና፡የንጉሥን፡ልጆች፡እንግዳ፡ልብስ፡የሚለብሱትንም፡ዅሉ፡ እቀጣለኹ።
9በዚያም፡ቀን፡በመድረኩ፡ላይ፡የሚዘሉ፟ትን፥የጌታቸውን፡ቤት፡ዐመፃንና፡ሽንገላን፡የሚሞሉትን፡ እቀጣለኹ።
10በዚያ፡ቀን፥ይላል፡እግዚአብሔር፥ከዓሣው፡በር፡የጩኸት፡ድምፅ፥ከከተማውም፡በኹለተኛው፡ክፍል፡ ውካታ፥ከኰረብታዎቹም፡ታላቅ፡ሽብር፡ይኾናል።
11እናንተ፡በመክቴሽ፡የምትኖሩ፡ሆይ፥የከነዓን፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ጠፍተዋልና፥ብርም፡የተሸከሙ፡ዅሉ፡ ተቈርጠዋልና፥አልቅሱ።
12በዚያም፡ዘመን፡ኢየሩሳሌምን፡በመብራት፡እመረምራለኹ፤በአተላቸውም፡ላይ፡ የሚቀመጡትን፥በልባቸውም፦እግዚአብሔር፡መልካምን፡አያደርግም፥ክፉም፡አያደርግም፡የሚሉትን፡ሰዎች፡ እቀጣለኹ።
13ብልጥግናቸውም፡ለምርኮ፡ይኾናል፥ቤቶቻቸውም፡ይፈርሳሉ፤ቤቶችንም፡ይሠራሉ፥ነገር፡ ግን፥አይቀመጡባቸውም፤ወይንንም፡ይተክላሉ፥የወይን፡ጠጁን፡ግን፡አይጠጡም።
14ታላቁ፡የእግዚአብሔር፡ቀን፡ቀርቧል፤የእግዚአብሔር፡ቀን፡ድምፅ፡ቀርቧል፡እጅግም፡ፈጥኗል፤ኀያሉም፡ በዚያ፡በመራራ፡ልቅሶ፡ይጮኻል።
15ያ፡ቀን፡የመዓት፡ቀን፡የመከራና፡የጭንቀት፡ቀን፥የመፍረስና፡የመጥፋት፡ቀን፥የጨለማና፡የጭጋግ፡ ቀን፥የደመናና፡የድቅድቅ፡ጨለማ፡ቀን፥
16በተመሸጉ፡ከተማዎችና፡በረዘሙ፡ግንቦች፡ላይ፡የመለከትና፡የሰልፍ፡ጩኸት፡ቀን፡ነው። 271 ዕብ.፥ጸፋንያህ፡(ጸፈነ፡እግዚእ•ጌታ፡ሰወረ፥ጨፈነ)። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
17በእግዚአብሔርም፡ላይ፡ኀጢአት፡ሠርተዋልና፥እንደ፡ዕውር፡እስኪኼዱ፡ድረስ፡ሰዎችን፡ አስጨንቃለኹ፤ደማቸውም፡እንደ፡ትቢያ፥ሥጋቸውም፡እንደ፡ጕድፍ፡ይፈሳ፟ል።
18በእግዚአብሔርም፡ቍጣ፡ቀን፡ብራቸውና፡ወርቃቸው፡ሊያድናቸው፡አይችልም፤ርሱም፡በምድር፡ የሚኖሩትን፡ዅሉ፡ፈጥኖ፡ይጨርሳቸዋልና፥ምድር፡ዅሉ፡በቅንአቱ፡እሳት፡ትበ፟ላ፟ለ፟ች።