Skip to content
← Zephaniah

Chapter 2 · Amharic

Zephaniah

2እናንተ፡ዕፍረት፡የሌላችኹ፡ሕዝብ፡ሆይ፥ትእዛዝ፡ሳይወጣ፥ቀኑም፡እንደ፡ገለባ፡ ሳያልፍ፥የእግዚአብሔርም፡ቍጣ፡ትኵሳት፡ሳይመጣባችኹ፥የእግዚአብሔርም፡ቍጣ፡ቀን፡ሳይደርስባችኹ፡ ተሰብሰቡ፥ተከማቹም።

3እናንተ፡ፍርዱን፡የጠበቃችኹ፡የምድር፡ትሑታን፡ዅሉ፥እግዚአብሔርን፡ፈልጉ፤ጽድቅንም፡ ፈልጉ፥ትሕትናንም፡ፈልጉ፤ምናልባት፡በእግዚአብሔር፡ቍጣ፡ቀን፡ትሰወሩ፡ይኾናል።

4ጋዛ፡ትበረበራለች፥አስቀሎናም፡ባድማ፡ትኾናለች፤አዞጦንንም፡በቀትር፡ወደ፡ውጭ፡ ያሳድዷታል፥ዐቃሮንም፡ትነቀላለች።

5በባሕር፡ዳር፡ለሚኖሩ፡ለከሊታውያን፡ሕዝብ፡ወዮላቸው! የፍልስጥኤማውያን፡ምድር፡ከነዓን፡ ሆይ፥የእግዚአብሔር፡ቃል፡ባንተ፡ላይ፡ነው፥የሚቀመጥብኽም፡ሰው፡እንዳይኖር፡አጠፋኻለኹ።

6ቀርጤስም፡የእረኛዎች፡መኖሪያና፡የመንጋዎች፡በረት፡ይኾናል።

7የባሕሩም፡ዳር፡ለይሁዳ፡ቤት፡ቅሬታ፡ይኾናል፥በዚያም፡ይሰማራሉ፤አምላካቸው፡እግዚአብሔር፡ ይጐበኛቸዋልና፥ምርኳቸውንም፡ይመልሳልና፥በአስቀሎና፡ቤቶች፡ውስጥ፡ማታ፡ይተኛሉ።

8በሕዝቤም፡ላይ፡ያላገጡባትን፥በድንበራቸውም፡ላይ፡እየታበዩ፡የተናገሩባትን፡የሞዐብን፡ማላገጥና፡ የዐሞንን፡ልጆች፡ስድብ፡ሰምቻለኹ።

9ስለዚህ፥የእስራኤል፡አምላክ፣የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እኔ፡ሕያው፡ነኝና፡በርግጥ፡ ሞዐብ፡እንደ፡ሰዶም፥የዐሞንም፡ልጆች፡እንደ፡ገሞራ፥የሳማ፡ስፍራና፡የጨው፡ጕድጓድ፡ለዘለዓለምም፡ ምድረ፡በዳ፡ኾነው፡ይኖራሉ፤የሕዝቤም፡ቅሬታ፡ይበዘብዛቸዋል፥ከወገኔም፡የተረፉት፡ይወርሷቸዋል።

10በሰራዊት፡ጌታ፡በእግዚአብሔር፡ሕዝብ፡ላይ፡አላግጠዋልና፥እየታበዩም፡ተናግረዋልና፥ይህ፡ስለ፡ ትዕቢታቸው፡ያገኛቸዋል።

11እግዚአብሔር፡በእነርሱ፡ላይ፡የተፈራ፡ይኾናል፥የምድርንም፡አማልክት፡ዅሉ፡ያከሳቸዋል፤በአሕዛብም፡ ደሴቶች፡ዅሉ፡ላይ፡የሚኖሩ፡ሰዎች፡ዅሉ፡በስፍራቸው፡ኾነው፡ለርሱ፡ይሰግዳሉ።

12እናንተም፡ኢትዮጵያውያን፡ደግሞ፥በሰይፌ፡ትገደላላችኹ።

13ርሱም፡በሰሜን፡ላይ፡እጁን፡ይዘረጋል፥አሶርንም፡ያጠፋል፤ነነዌንም፡ባድማ፥እንደ፡በረሓም፡ደረቅ፡ ያደርጋታል።

14መንጋዎችም፡የምድርም፡አራዊት፡ዅሉ፡በውስጧ፡ይመሰጋሉ፤ይብራና፡ዣርት፡በዐምዶቿ፡መካከል፡ ያድራሉ፤ድምፃቸው፡በመስኮቶቿ፡ይጮኻል፤የዝግባም፡ዕንጨት፡ሥራ፡ይገለጣልና፥በመድረኮቿ፡ላይ፡ጥፋት፡ ይኾናል።

15ተዘልላ፡የተቀመጠች፥በልቧም፦እኔ፡ነኝ፥ከእኔም፡በቀር፡ሌላ፡የለም፡ያለች፡ደስተኛዪቱ፡ከተማ፡ ይህች፡ናት፤አራዊት፡የሚመሰጉባት፡ባድማ፡እንዴት፡ኾነች! በርሷ፡በኩል፡የሚያልፈው፡ዅሉ፡እጁን፡ እያወዛወዘ፡ያፏጫል።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source