Skip to content
← Zephaniah

Chapter 3 · Amharic

Zephaniah

1ለዐመፀኛዪቱና፡ለረከሰች፡ለአስጨናቂዪቱም፡ከተማ፡ወዮላት!

2ድምፅን፡አልሰማችም፥ተግሣጽንም፡አልተቀበለችም፤በእግዚአብሔርም፡አልታመነችም፥ወደ፡አምላኳም፡ አልቀረበችም።

3በውስጧ፡ያሉ፡አለቃዎቿ፡እንደሚያገሡ፡አንበሳዎች፡ናቸው፤ፈራጆቿም፡እስከ፡ነገ፡ድረስ፡ምንም፡ እንደማያስቀሩ፡እንደ፡ማታ፡ተኵላዎች፡ናቸው።

4ነቢያቷ፡ቅሌታሞችና፡ተንኰለኛዎች፡ሰዎች፡ናቸው፤ካህናቷም፡መቅደሱን፡አርክሰዋል፥በሕግም፡ላይ፡ግፍ፡ ሠርተዋል።

5እግዚአብሔር፡በውስጧ፡ጻድቅ፡ነው፤ክፋትን፡አያደርግም፤ፍርዱን፡በየማለዳው፡ወደ፡ብርሃን፡ ያወጣል፥ሳያወጣውም፡አይቀርም፤ዐመፀኛው፡ግን፡ዕፍረትን፡አያውቅም።

6አሕዛብን፡አጥፍቻለኹ፤ግንቦቻቸው፡ዅሉ፡ፈርሰዋል፤መንገዳቸውን፡ማንም፡እንዳያልፍባት፡ምድረ፡በዳ፡ አድርጌያለኹ፥ከተማዎቻቸውም፡ማንም፡እንዳይኖርባቸው፥አንድስ፡እንኳ፡እንዳይቀመጥባቸው፡ፈርሰዋል።

7እኔም፦ይፈሩኛል፥ተግሣጽንም፡ይቀበላሉ፤ካዘዝዃትም፡ዅሉ፡ከዐይኗ፡ምንም፡አይጠፋም፡ብዬ፡ ነበር፤እነርሱ፡ግን፡በማለዳ፡ተነሥተው፡ድርጊታቸውን፡ዅሉ፡አረከሱ።

8መዓቴንና፡የቍጣዬን፡ትኵሳት፡ዅሉ፡አፈስ፟ባቸው፡ዘንድ፡ፍርዴ፡አሕዛብን፡ለመሰብሰብ፥መንግሥታትንም፡ ለማከማቸት፡ነውና፥ምድርም፡ዅሉ፡በቅንአቴ፡እሳት፡ትበላለችና፡ስለዚህ፡ለመበዝበዝ፡እስከምነሣበት፡ቀን፡ ድረስ፡ጠብቁኝ፥ይላል፡እግዚአብሔር።

9በዚያን፡ጊዜም፡አሕዛብ፡ዅሉ፡አንድ፡ኾነው፡እግዚአብሔርን፡ያገለግሉት፡ዘንድ፡ስሙን፡እንዲጠሩ፡ ንጹሓን፡ልሳን፡እመልስላቸዋለኹ።

10ከኢትዮጵያ፡ወንዞች፡ማዶ፡የሚማልዱኝ፥የተበተኑት፡ሴቶች፡ልጆቼ፥ቍርባኔን፡ያመጡልኛል።

11በዚያን፡ጊዜ፡እየታበዩ፡የሚፎክሩትን፡ከመካከልሽ፡አወጣለኹና፥አንቺም፡በቅዱስ፡ተራራዬ፡ዳግመኛ፡ አትኰሪምና፡በዚያ፡ቀን፡በእኔ፡ላይ፡ተላልፈሽ፡በሠራሽው፡ሥራ፡ዅሉ፡አትፍሪም።

12በመካከልሽም፡የዋህና፡ትሑት፡ሕዝብን፡አስቀራለኹ፤በእግዚአብሔርም፡ስም፡ይታመናሉ።

13የእስራኤል፡ቅሬታ፡ኀጢአትን፡አይሠሩም፥ሐሰትንም፡አይናገሩም፥በአፋቸውም፡ውስጥ፡ተንኰለኛ፡ምላስ፡ አይገኝም፤እነርሱም፡ይሰማራሉ፥ይመሰጉማል፥የሚያስፈራቸውም፡የለም።

14የጽዮን፡ልጅ፡ሆይ፥ዘምሪ፤እስራኤል፡ሆይ፥እልል፡በል፤የኢየሩሳሌም፡ልጅ፡ሆይ፥በፍጹም፡ልብሽ፡ ሐሤት፡አድርጊ፡ደስም፡ይበልሽ።

15እግዚአብሔር፡ፍርድሽን፡አስወግዷል፥ጠላትሽንም፡ጥሏል፤የእስራኤል፡ንጉሥ፡እግዚአብሔር፡በመካከልሽ፡ አለ፥ከእንግዲህም፡ወዲህ፡ክፉ፡ነገርን፡አታዪም።

16በዚያን፡ቀን፡ለኢየሩሳሌም፦ጽዮን፡ሆይ፥አትፍሪ፥እጆችሽም፡አይዛሉ።

17አምላክሽ፡እግዚአብሔር፡በመካከልሽ፡ታዳጊ፡ኀያል፡ነው፤በደስታ፡ባንቺ፡ደስ፡ይለዋል፥በፍቅሩም፡ ያርፋል፥በእልልታም፡ባንቺ፡ደስ፡ይለዋል፡ይባላል።

18ከጉባኤው፡ርቀው፡የሚያዝኑትን፥ከአንቺም፡የኾኑትን፡እሰበስባለኹ፤ስድብ፡እንደ፡ሸክም፡ከብዶባቸው፡ ነበር።

19በዚያ፡ዘመን፥እንሆ፥ባስጨነቁሽ፡ዅሉ፡ላይ፡አደርግባቸዋለኹ፤ዐንካሳዪቱንም፡ አድናለኹ፥የተጣለችውንም፡እሰበስባታለኹ፤ባፈሩባትም፡ምድር፡ዅሉ፡ላይ፡ለምስጋናና፡ለከበረ፡ስም፡ አደርጋቸዋለኹ።

20በዚያ፡ዘመን፡አስገባችዃለኹ፥በዚያም፡ዘመን፡እሰበስባችዃለኹ፤ምርኳችኹንም፡በዐይናችኹ፡ፊት፡ በመለስኹ፡ጊዜ፡በምድር፡አሕዛብ፡ዅሉ፡መካከል፡ለከበረ፡ስምና፡ለምስጋና፡አደርጋችዃለኹ፥ይላል፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org እግዚአብሔር፨ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source