Skip to content
← 1 Chronicles

Chapter 10 · Amharic

1 Chronicles

1ፍልስጥኤማውያንም፡ከእስራኤል፡ጋራ፡ተዋጉ፤የእስራኤልም፡ሰዎች፡ከፍልስጥኤማውያን፡ፊት፡ ሸሹ፥ተወግተውም፡በጊልቦአ፡ተራራ፡ላይ፡ወደቁ።

2ፍልስጥኤማውያንም፡ሳኦልንና፡ልጆቹን፡በእግር፡በእግራቸው፡ተከትለው፡አባረሯቸው፤ፍልስጥኤማውያንም፡ የሳኦልን፡ልጆች፡ዮናታንንና፡ዐሚናዳብን፡ሜልኪሳንም፡ገደሉ።

3ሰልፍም፡በሳኦል፡ላይ፡ጠነከረ፥ቀስተኛዎችም፡አገኙት፤ከቀስተኛዎችም፡የተነሣ፡ተጨነቀ።

4ሳኦልም፡ጋሻ፡ዣግሬውን፦እነዚህ፡ቈላፋን፡መጥተው፡እንዳይዘብቱብኝ፡ሰይፍኽን፡መዘ፟ኽ፡ውጋኝ፡ አለው።ጋሻ፡ዣግሬው፡ግን፡እጅግ፡ፈርቶ፡ነበርና፥እንቢ፡አለ።ሳኦልም፡ሰይፉን፡ወስዶ፡በላዩ፡ወደቀ።

5ጋሻ፡ዣግሬውም፡ሳኦል፡እንደ፡ሞተ፡ባየ፡ጊዜ፡ርሱ፡ደግሞ፡በሰይፉ፡ላይ፡ወድቆ፡ሞተ።

6ሳኦልና፡ሦስቱ፡ልጆቹ፡የቤቱም፡ሰዎች፡ዅሉ፡ባንድ፡ላይ፡ሞቱ።

7በሸለቆውም፡የነበሩት፡የእስራኤል፡ሰዎች፡ዅሉ፡እንደ፡ሸሹ፥ሳኦልና፡ልጆቹም፡እንደ፡ሞቱ፡ባዩ፡ጊዜ፡ ከተማዎቻቸውን፡ለቀ፟ው፡ሸሹ፤ፍልስጥኤማውያንም፡መጥተው፡ተቀመጡባቸው።

8በነጋውም፡ፍልስጥኤማውያን፡የሞቱትን፡ለመግፈፍ፡በመጡ፡ጊዜ፡ሳኦልንና፡ልጆቹን፡በጊልቦአ፡ተራራ፡ ላይ፡ወድቀው፡አገኟቸው።

9ገፈፉትም፥ራሱንና፡መሣሪያውንም፡አንሥተው፡ለጣዖቶቻቸውና፡ለሕዝቡ፡የምሥራች፡ይወስዱ፡ዘንድ፡ ወደፍልስጥኤማውያን፡አገር፡ዙሪያ፡ሰደዱ።

10መሣሪያውንም፡በአምላኮቻቸው፡ቤት፡ውስጥ፡አኖሩ፤ራሱንም፡በዳጎን፡ቤት፡ውስጥ፡ቸነከሩት።

11የኢያቢስ፡ገለዓድም፡ሰዎች፡ዅሉ፡ፍልስጥኤማውያን፡በሳኦል፡ላይ፡ያደረጉትን፡ዅሉ፡በሰሙ፡ጊዜ፥ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

12ጽኑአን፡ሰዎች፡ዅሉ፡ተነሥተው፡የሳኦልን፡ሬሳ፡የልጆቹንም፡ሬሳ፡ወሰዱ፥ወደ፡ኢያቢስም፡ አመጧቸው፤በኢያቢስም፡ካለው፡ከትልቁ፡ዛፍ፡በታች፡ዐጥንቶቻቸውን፡ቀበሩ፥ሰባት፡ቀንም፡ጾሙ።

13እንዲሁ፡ሳኦል፡በእግዚአብሔር፡ላይ፡ስላደረገው፡ኀጢአት፥የእግዚአብሔርንም፡ቃል፡ስላልጠበቀ፡ ሞተ።ደግሞም፡መናፍስት፡ጠሪ፡

14ስለ፡ጠየቀ፡እግዚአብሔርንም፡ስላልጠየቀ፥ስለዚህ፡ገደለው፥መንግሥቱንም፡ወደእሴይ፡ልጅ፡ወደ፡ ዳዊት፡አሳለፈው።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source