Skip to content
← 1 Chronicles

Chapter 11 · Amharic

1 Chronicles

1እስራኤልም፡ዅሉ፡በኬብሮን፡ወደ፡ዳዊት፡ተሰብስበው፦እንሆ፥እኛ፡የዐጥንትኽ፡ፍላጭ፡የሥጋኽ፡ ቍራጭ፡ነን፤

2አስቀድሞ፡ሳኦል፡ንጉሥ፡ኾኖ፡ሳለ፡እስራኤልን፡የምታወጣና፡የምታገባ፡አንተ፡ነበርኽ፤አምላክኽ፡ እግዚአብሔርም፦ሕዝቤን፡እስራኤልን፡አንተ፡ትጠብቃለኽ፤በሕዝቤም፡በእስራኤል፡ላይ፡አለቃ፡ትኾናለኽ፡ ብሎኽ፡ነበር፡አሉት።

3የእስራኤልም፡ሽማግሌዎች፡ዅሉ፡ወደ፡ንጉሡ፡ወደ፡ኬብሮን፡መጡ፤ዳዊትም፡በኬብሮን፡ በእግዚአብሔር፡ፊት፡ቃል፡ኪዳን፡ከነርሱ፡ጋራ፡አደረገ፤በሳሙኤልም፡እጅ፡እንደተናገረው፡ እንደእግዚአብሔር፡ቃል፡በእስራኤል፡ላይ፡ንጉሥ፡ይኾን፡ዘንድ፡ዳዊትን፡ቀቡት።

4ዳዊትም፡እስራኤልም፡ዅሉ፡ኢያቡስ፡ወደምትባል፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ኼዱ፤በአገሩም፡የተቀመጡ፡ ኢያቡሳውያን፡በዚያ፡ነበሩ።

5በኢያቡስም፡የተቀመጡ፡ዳዊትን፦ወደዚህ፡አትገባም፡አሉት፤ዳዊት፡ግን፡ዐምባዪቱን፡ጽዮንን፡ ያዘ፤ርሷም፡የዳዊት፡ከተማ፡ናት።

6ዳዊትም፦ኢያቡሳውያንን፡አስቀድሞ፡የሚመታ፡ሰው፡አለቃና፡መኰንን፡ይኾናል፡አለ።የጽሩያም፡ልጅ፡ ኢዮአብ፡አስቀድሞ፡ወጣ፥አለቃም፡ኾነ።

7ዳዊትም፡በዐምባዪቱ፡ውስጥ፡ተቀመጠ፤ስለዚህም፡የዳዊት፡ከተማ፡ብለው፡ጠሯት።

8ከሚሎም፡ዠምሮ፡በዙሪያው፡ከተማ፡ሠራ፤ኢዮአብም፡የቀረውን፡ከተማ፡አበጀ።

9ዳዊትም፡የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡ከርሱ፡ጋራ፡ነበርና፥እየበረታ፡ኼደ።

10ለዳዊትም፡የነበሩት፡የኀያላን፡አለቃዎች፡እነዚህ፡ናቸው፤ስለ፡እስራኤል፡እንደተናገረው፡የእግዚአብሔር፡ ቃል፡ያነግሡት፡ዘንድ፡ከእስራኤል፡ዅሉ፡ጋራ፡በመንግሥቱ፡ላይ፡አጸኑት።

11የዳዊትም፡ኀያላን፡ቍጥር፡ይህ፡ነበረ፤የሠላሳው፡አለቃ፡የአክሞናዊው፡ልጅ፡ያሾብአም፡ነበረ፤ርሱ፡ ጦሩን፡አንሥቶ፡ሦስት፡መቶ፡ሰው፡ባንድ፡ጊዜ፡ገደለ።

12ከርሱም፡በዃላ፡በሦስቱ፡ኀያላን፡መካከል፡የነበረ፡የአሆሃሂው፡የዱዲ፡ልጅ፡አልዓዛር፡ነበር።

13ርሱ፡ከዳዊት፡ጋራ፡በፈስደሚም፡ነበረ፥በዚያም፡ገብስ፡በሞላበት፡ዕርሻ፡ውስጥ፡ፍልስጥኤማውያን፡ ለሰልፍ፡ተሰብስበው፡ነበር፤ሕዝቡም፡ከፍልስጥኤማውያን፡ፊት፡ሸሹ።

14በዕርሻውም፡መካከል፡ቆመው፡ጠበቁት፥ፍልስጥኤማውያንንም፡ገደሉ፤እግዚአብሔርም፡በታላቅ፡ማዳን፡ አዳናቸው።

15ከሠላሳውም፡አለቃዎች፡ሦስቱ፡ወርደው፡ዳዊት፡ወዳለበት፡ወደ፡አለቱ፡ወደዓዶላም፡ዋሻ፡ መጡ፤የፍልስጥኤማውያንም፡ጭፍራ፡በራፋይም፡ሸለቆ፡ሰፍሮ፡ነበር።

16በዚያም፡ጊዜ፡ዳዊት፡በምሽጉ፡ውስጥ፡ነበረ፥የፍልስጥኤማውያንም፡ጭፍራ፡በቤተ፡ልሔም፡ነበረ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

17ዳዊትም፦በበሩ፡አጠገብ፡ካለችው፡ከቤተ፡ልሔም፡ምንጭ፡ውሃ፡ማን፡ይሰጠኛል፧ብሎ፡ተመኘ።

18እነዚህም፡ሦስቱ፡የፍልስጥኤማውያንን፡ሰራዊት፡ቀደ፟ው፡ኼዱ፥በበሩም፡አጠገብ፡ካለችው፡ከቤተ፡ልሔም፡ ምንጭ፡ውሃ፡ቀዱ፤ይዘውም፡ለዳዊት፡አመጡለት።ርሱ፡ግን፡ሊጠጣ፡አልወደደም፥ነገር፡ ግን፥ለእግዚአብሔር፡አፍሶ፟።

19ይህን፡ኣደርግ፡ዘንድ፡አምላኬ፡ይከልክለኝ፤በነፍሳቸው፡የደፈሩትም፡እነዚህ፡ሰዎች፡ደም፡ እጠጣለኹን፧በነፍሳቸው፡አምጥተውታል፡አለ።ስለዚህም፡ይጠጣ፡ዘንድ፡አልወደደም።ሦስቱም፡ኀያላን፡ ያደረጉት፡ይህ፡ነው።

20የኢዮአብም፡ወንድም፡አቢሳ፡የሦስቱ፡አለቃ፡ነበረ፤ጦሩንም፡በሦስት፡መቶ፡ላይ፡አንሥቶ፡ ገደላቸው፥በሦስቱም፡መካከል፡ስሙ፡የተጠራ፡ነበረ።

21በኹለተኛውም፡ተራ፡በኾኑት፡በሦስቱ፡መካከል፡የከበረ፡ነበረ፥አለቃቸውም፡ኾነ፤ነገር፡ግን፥ወደ፡ ፊተኛዎቹ፡ወደ፡ሦስቱ፡አልደረሰም።

22በቀብስኤልም፡የነበረው፥ታላቅ፡ሥራ፡ያደረገው፡የጽኑዕ፡ሰው፡የዮዳዔ፡ልጅ፡በናያስ፡የሞዐባዊን፡ የአሪኤል፡ኹለቱን፡ልጆች፡ገደለ፤በዐመዳይም፡ወራት፡ወርዶ፡በጕድጓድ፡ውስጥ፡አንበሳ፡ገደለ።

23ቁመቱም፡ዐምስት፡ክንድ፡የነበረውን፡ረዥሙን፡ግብጻዊውን፡ሰው፡ገደለ፤በግብጻዊውም፡እጅ፡የሸማኔ፡ መጠቅለያ፡የመሰለ፡ጦር፡ነበረ፤ርሱ፡ግን፡በትር፡ይዞ፡ወደ፡ርሱ፡ወረደ፥ከግብጻዊውም፡እጅ፡ጦሩን፡ ነቅሎ፡በገዛ፡ጦሩ፡ገደለው።

24የዮዳዔ፡ልጅ፡በናያስ፡ያደረገው፡ይህ፡ነው፤ስሙም፡በሦስቱ፡ኀያላን፡መካከል፡የተጠራ፡ነበር።

25እንሆ፥ከሠላሳው፡ይልቅ፡የከበረ፡ነበረ፥ነገር፡ግን፥ወደ፡ፊተኛዎቹ፡ወደ፡ሦስቱ፡አልደረሰም።ዳዊትም፡ በዘበኛዎቹ፡ላይ፡ሾመው።

26ደግሞም፡በጭፍራዎች፡ዘንድ፡የነበሩት፡ኀያላን፡እነዚህ፡ናቸው፤የኢዮአብ፡ወንድም፡ዐሳሄል፥የቤተ፡ ልሔሙ፡ሰው፡የዱዲ፡ልጅ፡ኤልያናን፥

27ሃሮራዊው፡ሳሞት፥ፈሎናዊው፡ሴሌስ፥

28የቴቁሔ፡ሰው፡የዒስካ፡ልጅ፡ዒራስ፥

29ዓናቶታዊው፡አቢዔዜር፥ኩሳታዊ ው፡ሴቤካይ፥

30አሖሓዊው፡ዔላይ፥ነጦፋዊው፡ኖኤሬ፥የነጦፋዊው፡የበዓና፡ልጅ፡ሔሌድ፥

31ከብንያም፡ወገን፡ከግብዓ፡የሪባይ፡ልጅ፡ኤታይ፥

32ጲርዓቶናዊው፡በናያስ፥የገዓስ፡ወንዝ፡ሰው፡ኡሪ፥

33ዐረባዊው፡አቢኤል፥ባሕሩማዊው፡ዓዝሞት፥

34ሰዓልቦናዊው፡ኤሊያሕባ፥የጊዞናዊው፡የአሣን፡ልጆች፥የሃራራዊው፡የሻጌ፡ልጅ፡ዮናታን፥

35የአሮዳዊው፡የአራር፡ልጅ፡አምናን፥

36የኡር፡ልጅ፡ኤሊፋል፥ሚኬራታዊው፡ኦፌር፥

37ፍሎናዊው፡አኪያ፥ቀርሜሎሳዊው፡ሐጽሮ፥የኤዝባይ፡ልጅ፡ነዕራይ፥

38የናታንም፡ወንድም፡ኢዮኤል፥የሐግሪ፡ልጅ፡ሚብሐር፥

39አሞናዊው፡ጼሌቅ፥የጽሩያ፡ልጅ፡የኢዮአብ፡ጋሻ፡ዣግሬ፡ቤሮታዊው፡ነሃራይ፥

40ይትራዊው፡ዒራስ፥ይትራዊው፡ጋሬብ፥ 227 ዕብ.፥ሑሻቲ፡(ሑሰታዊ•የሑሰት፣የፍጥነት፡ወገን)። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

41ኬጢያዊው፡ኦርዮ፥የአሕላይ፡ልጅ፡ዛባድ፥

42የሮቤላዊው፡የሺዛ፡ልጅ፡ዓዲና፥ርሱ፡የሮቤላውያን፡አለቃ፡ነበረ፥

43ከርሱም፡ጋራ፡ሠላሳ፡ሰዎች፡ነበሩ፥የማዕካ፡ልጅ፡ሐናን፥ሚትናዊው፡ኢዮሳፍጥ፥

44ዐስታሮታዊው፡ዖዝያ፥የአሮኤራዊው፡የኮታም፡ልጆች፡ሻማና፡ይዒኤል፥

45የሽምሪ፡ልጅ፡ይድኤል፥ወንድሙም፡ይድኤል፥ወንድሙም፡ቲዳዊው፡ዮሐ፥

46መሐዋዊው፡ኤሊኤል፥ይሪባይ፥ዮሻዊያ፥የኤልናዓም፡ልጆች፥ሞዐባዊው፡ይትማ፥

47ኤልኤል፥ዖቤድ፥ምጾባዊው፡የዕሢኤል።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source