1በጺቅላግም፡ከቂስ፡ልጅ፡ከሳኦል፡በተሸሸገ፡ጊዜ፡ወደ፡ዳዊት፡የመጡ፡እነዚህ፡ናቸው፤በሰልፍም፡ ባገዙት፡ኀያላን፡መካከል፡ነበሩ።
2ቀስተኛዎችም፡ነበሩ፥በቀኝና፡በግራም፡እጃቸው፡ድንጋይ፡ሊወነጭፉ፡ፍላጻም፡ሊወረውሩ፡ይችሉ፡ ነበር፤ከብንያም፡ወገን፡የሳኦል፡ወንድሞች፡ነበሩ።
3አለቃቸው፡አኂዔዝር፡ነበረ፥ከርሱም፡በዃላ፡ኢዮአስ፥የጊብዓዊው፡የሸማዓ፡ ልጆች፤ይዝኤል፥ፋሌጥ፥የዓዝሞት፡ልጆች፤በራኪያ፥ዓናቶታዊው፡ኢዩ፥
4ገባዖናዊው፡ሰማያስ፥ርሱ፡በሠላሳው፡መካከልና፡በሠላሳው፡ላይ፡ኀያል፡ሰው፡ ነበረ፤ኤርምያስ፥የሕዚኤል፥ዮሐናን፥
5ገድሮታዊው፡ዮዛባት፥ኤሉዛይ፥ኢያሪሙት፥በዓልያ፥ሰማራያ፥ሐሩፋዊው፡ሰፋጥያስ፥
6ቆርያውያን፡ሕልቃና፥ይሺያ፥ዐዛርኤል፥ዮዛር፥ያሾቢአም፤
7የጌዶር፡ሰው፡የይሮሃም፡ልጆች፡የኤላ፥ዝባድያ፡
8ዳዊትም፡ከምድረ፡በዳ፡ውስጥ፡ባለችው፡በዐምባዪቱ፡ሳለ፡ከጋድ፡ወገን፡የኾኑ፡እነዚህ፡ጋሻና፡ጦር፡ የሚይዙ፥ጽኑዓን፡ኀያላን፥ሰልፈኛዎች፥ወደ፡ርሱ፡ተጠጉ፤ፊታቸውም፡እንደ፡አንበሳ፡ፊት፡ነበረ፥በተራራም፡ ላይ፡እንደሚዘል፟፡ሚዳቋ፡ፈጣኖች፡ነበሩ።
9አለቃው፡ዔጼር፥ኹለተኛው፡ዐብድዩ፥
10ሦስተኛው፡ኤልያብ፥አራተኛው፡መስመና፥
11ዐምስተኛው፡ኤርምያስ፥ስድስተኛው፡አታይ፥
12ሰባተኛው፡ኤሊኤል፥ስምንተኛው፡ዮሐናን፥
13ዘጠነኛው፡ኤልዛባድ፥ዐሥረኛው፡ኤርምያስ፥ዐሥራ፡አንደኛው፡መክበናይ።
14እነዚህ፡የጋድ፡ልጆች፡የጭፍራ፡አለቃዎች፡ነበሩ፤ከነርሱም፡ታናሹ፡ከመቶ፥ታላቁ፡ከሺሕ፡ይመዛዘኑ፡ ነበር።
15በመዠመሪያው፡ወር፡ዮርዳኖስ፡ከዳር፡እስከ፡ዳር፡ሞልቶ፡በነበረ፡ጊዜ፡የተሻገሩት፡እነዚህ፡ ናቸው፤በሸለቆውም፡ውስጥ፡በምሥራቅና፡በምዕራብ፡በኩል፡የተቀመጡትን፡ዅሉ፡አባረሩ።
16ዳዊትም፡ወደነበረባት፡ወደ፡ዐምባዪቱ፡ከብንያምና፡ከይሁዳ፡ወገን፡ሰዎች፡መጡ።
17ዳዊትም፡ሊገናኛቸው፡ወጥቶ፦ትረዱኝ፡ዘንድ፡በሠላም፡ወደ፡እኔ፡መጥታችኹ፡እንደ፡ኾነ፡ልቤ፡ ከእናንተ፡ጋራ፡አንድ፡ይኾናል፤ለጠላቶቼ፡አሳልፋችኹ፡ልትሰጡኝ፡መጥታችኹ፡እንደ፡ኾነ፡ግን፥በእጄ፡ ዐመፅ፡የለብኝምና፡የአባቶቻችን፡አምላክ፡ይመልከተው፥ይፍረደውም፡አላቸው። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
18መንፈስም፡በሠላሳው፡አለቃ፡በአማሳይ፡ላይ፡መጣ፥ርሱም፦ዳዊት፡ሆይ፥እኛ፡የአንተ፡ነን፤የእሴል፡ ልጅ፡ሆይ፥እኛ፡ከአንተ፡ጋራ፡ነን፤አምላክኽ፡ይረዳኻልና፥ሰላም፡ሰላም፡ለአንተ፡ይኹን፥ለሚረዱኽም፡ ሰላም፡ይኹን፡አለ።ዳዊትም፡ተቀበላቸው፥የጭፍራም፡አለቃዎች፡አደረጋቸው።
19ዳዊትም፡ከፍልስጥኤማውያን፡ጋራ፡ሳኦልን፡ሊወጋ፡በመጣ፡ጊዜ፡ከምናሴ፡ወገን፡ሰዎች፡ወደ፡ዳዊት፡ ከዱ፤የፍልስጥኤማውያን፡አለቃዎች፡ግን፦በራሳችን፡ላይ፡ጕዳት፡አድርጎ፡ወደ፡ጌታው፡ወደ፡ሳኦል፡ ይመለሳል፡ሲሉ፡ተማክረው፡ሰደ፟ውታልና፥እነርሱ፡አልረዷቸውም።
20ወደ፡ጺቅላግም፡ሲኼድ፡ከምናሴ፡ወገን፡የምናሴ፡ሻለቃዎች፡የነበሩ፡ ዓድና፥ዮዛባት፥ይዲኤል፥ሚካኤል፥ዮዛባት፥ኤሊሁ፥ጺልታይ፡ወደ፡ርሱ፡ከዱ።
21ዅሉም፡ጽኑዓን፡ኀያላንና፡በሰራዊቱ፡ላይ፡አለቃዎች፡ነበሩና፥በአደጋ፡ጣዮቹ፡ላይ፡ዳዊትን፡አገዙት።
22እንደእግዚአብሔርም፡ሰራዊት፡ታላቅ፡ሰራዊት፡እስኪኾን፡ድረስ፡ዳዊትን፡ለመርዳት፡ዕለት፡ዕለት፡ ይመጡ፡ነበር።
23እንደእግዚአብሔርም፡ቃል፡የሳኦልን፡መንግሥት፡ወደ፡ርሱ፡ይመልሱ፡ዘንድ፡በኬብሮን፡ሳለ፡ወደ፡ ዳዊት፡የመጡት፡የሰራዊቱ፡አለቃዎች፡ቍጥር፡ይህ፡ነው።
24ጋሻና፡ጦር፡ተሸክመው፡ለሰልፍ፡የተዘጋጁ፡የይሁዳ፡ልጆች፡ስድስት፡ሺሕ፡ስምንት፡መቶ፡ነበሩ።
25ለሰልፍ፡ጽኑዓን፡ኀያላን፡ሰዎች፡የነበሩ፡የስምዖን፡ልጆች፡ሰባት፡ሺሕ፡አንድ፡መቶ፡ነበሩ።
26የሌዊ፡ልጆች፡አራት፡ሺሕ፡ስድስት፡መቶ፡ነበሩ።
27የአሮንም፡ቤት፡አለቃ፡ዮዳዔ፡ነበረ፥ከርሱም፡ጋራ፡ሦስት፡ሺሕ፡ሰባት፡መቶ፡ነበሩ፤
28ከርሱም፡ጋራ፡ጽኑዕ፡ኀያል፡ጕልማሳ፡ሳዶቅ፡ነበረ፥ከአባቱም፡ቤት፡ኻያ፡ኹለት፡አለቃዎች፡ነበሩ።
29የሳኦልም፡ወንድሞች፡ከኾኑ፡ከብንያም፡ወንድሞች፡የሚበልጠው፡ክፍል፡እስከዚያ፡ዘመን፡ድረስ፡ የሳኦልን፡ቤት፡ይከተል፡ነበርና፥ከነርሱ፡ዘንድ፡የመጡ፡ሦስት፡ሺሕ፡ነበሩ።
30ጽኑዓን፡ኀያላን፡የኾኑ፡በአባቶቻቸውም፡ቤት፡የታወቁ፡የኤፍሬም፡ልጆች፡ኻያ፡ሺሕ፡ስምንት፡መቶ፡ ነበሩ።
31በየስማቸውም፡የተጻፉ፡ዳዊትን፡ያነግሡት፡ዘንድ፡የመጡ፡የምናሴ፡ነገድ፡እኩሌታ፡ዐሥራ፡ስምንት፡ ሺሕ፡ነበሩ።
32እስራኤልም፡የሚገ፟ባ፟ውን፡ያደርግ፡ዘንድ፡ዘመኑን፡የሚያውቁ፡ጥበበኛዎች፡ሰዎች፡የይሳኮር፡ልጆች፡ አለቃዎች፡ኹለት፡መቶ፡ነበሩ፤ወንድሞቻቸውም፡ዅሉ፡ይታዘዟቸው፡ነበር።
33በጭፍራውም፡ውስጥ፡የወጡ፡ለሰልፍም፡የተዘጋጁ፥የማያመነቱ፥መሣሪያም፡ዅሉ፡የያዙ፡የዛብሎን፡ ሰዎች፡ዐምሳ፡ሺሕ፡ነበሩ።
34የንፍታሌምም፡አለቃዎች፡አንድ፡ሺሕ፡ነበሩ፥ከነርሱም፡ጋራ፡ጋሻና፡ጦር፡የሚይዙ፡ሠላሳ፡ሰባት፡ሺሕ፡ ነበሩ።
35ለሰልፍም፡የተዘጋጁ፡የዳን፡ሰዎች፡ኻያ፡ስምንት፡ሺሕ፡ስድስት፡መቶ፡ነበሩ።
36በጭፍራውም፡ውስጥ፡የሚወጡ፥ለሰልፍም፡የተዘጋጁ፡የአሴር፡ሰዎች፡አርባ፡ሺሕ፡ነበሩ።
37በዮርዳኖስም፡ማዶ፡ካሉ፡ከሮቤልና፡ከጋድ፡ሰዎች፡ከምናሴም፡ነገድ፡እኩሌታ፡መሣሪያን፡ዅሉ፡ይዘው፡ የመጡ፡መቶ፡ኻያ፡ሺሕ፡ነበሩ።
38እነዚህ፡ዅሉ፡ዳዊትን፡በእስራኤል፡ዅሉ፡ላይ፡ያነግሡት፡ዘንድ፡ዐርበኛዎችና፡ሰልፈኛዎች፡እየኾኑ፡ በፍጹም፡ልባቸው፡ወደ፡ኬብሮን፡መጡ፤ደግሞም፡ከእስራኤል፡የቀሩት፡ዅሉ፡ዳዊትን፡ያነግሡት፡ዘንድ፡ አንድ፡ልብ፡ነበሩ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
39ወንድሞቻቸውም፡አዘጋጅተውላቸው፡ነበርና፥እየበሉና፡እየጠጡ፡በዚያ፡ከዳዊት፡ጋራ፡ሦስት፡ቀን፡ ተቀመጡ።
40ደግሞም፡በእስራኤል፡ዘንድ፡ደስታ፡ኾኗልና፥እስከ፡ይሳኮርና፡እስከ፡ዛብሎን፡እስከ፡ንፍታሌምም፡ድረስ፡ ለርሱ፡አቅራቢያ፡የነበሩ፡በአህያና፡በግመል፡በበቅሎና፡በበሬ፡ላይ፡እንጀራና፡ዱቄት፡የበለስ፡ጥፍጥፍና፡ የዘቢበ፡ዘለላ፡የወይንም፡ጠጅ፡ዘይትም፡በሬዎችንና፡በጎችንም፡በብዙ፡አድርገው፡ያመጡ፡ነበር።