Skip to content
← 1 Chronicles

Chapter 13 · Amharic

1 Chronicles

1ዳዊትም፡ከሻለቃዎችና፡ከመቶ፡አለቃዎች፡ከአለቃዎቹም፡ዅሉ፡ጋራ፡ተማከረ።

2ዳዊትም፡የእስራኤልን፡ጉባኤ፡ዅሉ፦መልካም፡መስሎ፡የታያችኹ፡እንደ፡ኾነ፥ከአምላካችን፡ ከእግዚአብሔርም፡ወጥቶ፡እንደ፡ኾነ፥በእስራኤል፡አገር፡ዅሉ፡ለቀሩት፡ወንድሞቻችን፡በከተማዎቻቸውና፡ በመሰምሪያዎቻቸውም፡ለሚቀመጡ፡ካህናትና፡ሌዋውያን፡ወደ፡እኛ፡ይሰበሰቡ፡ዘንድ፡እንላክ፤

3በሳኦልም፡ዘመን፡አልፈለግነውምና፡የአምላካችንን፡ታቦት፡ወደ፡እኛ፡እንመልስ፡አላቸው።

4ነገሩም፡በሕዝቡ፡ዅሉ፡ዐይን፡ዘንድ፡ቅን፡ነበረና፡ጉባኤው፡ዅሉ፦እንዲሁ፡እናደርጋለን፡አሉ።

5የእግዚአብሔርንም፡ታቦት፡ከቂርያትይዓሪም፡ያመጡ፡ዘንድ፡ዳዊት፡እስራኤልን፡ዅሉ፡ከግብጽ፡ወንዝ፡ ከሺሖር፡ዠምሮ፡እስከሐማት፡መግቢያ፡ድረስ፡ሰበሰበ።

6ዳዊትም፡እስራኤልም፡ዅሉ፡በኪሩቤል፡ላይ፡የተቀመጠውን፡ስሙም፡በርሱ፡የተጠራውን፡የአምላክን፡ የእግዚአብሔርን፡ታቦት፡ከዚያ፡ያወጡ፡ዘንድ፡በይሁዳ፡ወዳለችው፡ቂርያትይዓሪም፡ወደተባለች፡ወደ፡በዓላ፡ ኼዱ።

7የእግዚአብሔርንም፡ታቦት፡በዐዲስ፡ሠረገላ፡ላይ፡ጫኑት፥ከዐሚናዳብም፡ቤት፡አመጡት፤ዖዛና፡አኂዮም፡ ሠረገላውን፡ይነዱ፡ነበር።

8ዳዊትና፡እስራኤል፡ዅሉ፡በቅኔና፡በበገና፡በመሰንቆና፡በከበሮ፡በጸናጽልና፡በመለከት፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ በሙሉ፡ኀይላቸው፡ይጫወቱ፡ነበር።

9ወደኪዶንም፡ዐውድማ፡በደረሱ፡ጊዜ፡በሬዎቹ፡ይፋንኑ፡ነበርና፥ታቦቱን፡ሊይዝ፡ዖዛ፡እጁን፡ዘረጋ።

10የእግዚአብሔርም፡ቍጣ፡በዖዛ፡ላይ፡ነደደ፥እጁንም፡ወደ፡ታቦቱ፡ስለ፡ዘረጋ፡ቀሠፈው፤በዚያም፡ በእግዚአብሔር፡ፊት፡ሞተ።

11እግዚአብሔርም፡ዖዛን፡ስለ፡ቀሠፈው፡ዳዊት፡ዐዘነ፤እስከ፡ዛሬም፡ድረስ፡የዚያን፡ስፍራ፡ስም፡የዖዛ፡ ስብራት፡ብሎ፡ጠራው።

12በዚያም፡ቀን፡ዳዊት፦የእግዚአብሔርን፡ታቦት፡ወደ፡እኔ፡እንዴት፡አመጣለኹ፡ብሎ፡እግዚአብሔርን፡ ፈራ።

13ዳዊትም፡ታቦቱን፡ወደጌት፡ሰው፡ወደአቢዳራ፡ቤት፡አሳለፈው፡እንጂ፡ወደ፡ርሱ፡ወደዳዊት፡ከተማ፡ አላመጣውም።

14የእግዚአብሔርም፡ታቦት፡በአቢዳራ፡ቤተ፡ሰብ፡ዘንድ፡በቤቱ፡ውስጥ፡ሦስት፡ወር፡ ተቀመጠ፤እግዚአብሔርም፡የአቢዳራን፡ቤትና፡ያለውን፡ዅሉ፡ባረከ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source