Skip to content
← 1 Chronicles

Chapter 14 · Amharic

1 Chronicles

1የጢሮስም፡ንጉሥ፡ኪራም፡ቤት፡ይሠሩለት፡ዘንድ፡መልእክተኛዎችን፡የዝግባ፡ዕንጨትንም፡ጠራቢዎችንም፡ ዐናጢዎችንም፡ወደ፡ዳዊት፡ላከ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

2ስለ፡ሕዝቡም፡ስለ፡እስራኤል፡መንግሥቱ፡ከፍ፡ብሏልና፥እግዚአብሔር፡በእስራኤል፡ላይ፡ንጉሥ፡አድርጎ፡ እንዳጸናው፡ዳዊት፡ዐወቀ።

3ዳዊትም፡በኢየሩሳሌም፡ሚስቶችን፡ጨምሮ፡ሌላዎችን፡ወንዶችንና፡ሴቶችን፡ልጆች፡ወለደ።

4በኢየሩሳሌምም፡የወለዳቸው፡የልጆቹ፡ስም፡ይህ፡ነው፤ሳሙስ፥

5ሶባብ፥ናታን፥ሰሎሞን፥ኢያቤሐር፥ኤሊሱዔ፥

6ኤሊፋላት፥ኖጋ፥ናፌቅ፥ያፍያ፥

7ኤሊሳማ፥ኤሊዳሄ፥ኤሊፋላት።

8ፍልስጥኤማውያንም፡ዳዊት፡በእስራኤል፡ዅሉ፡ላይ፡ንጉሥ፡ኾኖ፡አንደ፡ተቀባ፡ሰሙ፥ፍልስጥኤማውያንም፡ ዅሉ፡ዳዊትን፡ሊፈልጉ፡ወጡ፤ዳዊትም፡በሰማ፡ጊዜ፡ሊጋጠማቸው፡ወጣ።

9ፍልስጥኤማውያንም፡መጥተው፡በራፋይም፡ሸለቆ፡አደጋ፡ጣሉ።

10ዳዊትም፦ወደ፡ፍልስጥኤማውያን፡ልውጣን፧በእጄስ፡አሳልፈኽ፡ትሰጣቸዋለኽን፧ብሎ፡እግዚአብሔርን፡ ጠየቀ።እግዚአብሔርም፦በእጅኽ፡አሳልፌ፡እሰጣቸዋለኹና፡ውጣ፡አለው።

11ወደ፡በአልፐራሲም፡ወጡ፥በዚያም፡ዳዊት፡መታቸው።ዳዊትም፦ውሃ፡እንዲያፈርስ፡እግዚአብሔር፡ ጠላቶቼን፡በእጄ፡አፈረሳቸው፡አለ።ስለዚህም፡የዚያን፡ስፍራ፡ስም፡በአልፐራሲም፡ብለው፡ጠሩት።

12አማልክታቸውንም፡በዚያ፡ተዉ፤ዳዊትም፡አዘዘ፥በእሳትም፡አቃጠሏቸው።

13ፍልስጥኤማውያንም፡ደግሞ፡በሸለቆው፡አደጋ፡ጣሉ።

14ዳዊትም፡እንደ፡ገና፡እግዚአብሔርን፡ጠየቀ፤እግዚአብሔርም፦ከነርሱ፡ዞረኽ፡በሾላው፡ዛፍ፡ፊት፡ ለፊት፡ግጠማቸው፡እንጂ፡ወደ፡እነርሱ፡አትውጣ።

15በሾላውም፡ዛፍ፡ራስ፡ውስጥ፡የሽውሽውታ፡ድምፅ፡ስትሰማ፡የፍልስጥኤማውያንን፡ጭፍራ፡ሊመታ፡ እግዚአብሔር፡በፊትኽ፡ይወጣልና፥በዚያን፡ጊዜ፡ወደ፡ሰልፍ፡ውጣ፡አለው።

16ዳዊትም፡እግዚአብሔር፡እንዳዘዘው፡አደረገ፤ከገባዖንም፡ዠምሮ፡እስከ፡ጌዝር፡ድረስ፡ የፍልስጥኤማውያንን፡ጭፍራ፡መቱት።

17የዳዊትም፡ዝና፡በያገሩ፡ዅሉ፡ወጣ፤መፈራቱንም፡እግዚአብሔር፡በአሕዛብ፡ዅሉ፡ዘንድ፡አደረገው።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source