1ዳዊትም፡በከተማው፡ላይ፡ለራሱ፡ቤቶችን፡ሠራ፤ለእግዚአብሔርም፡ታቦት፡ስፍራ፡አዘጋጀ፥ድንኳንም፡ ተከለለት።
2በዚያን፡ጊዜም፡ዳዊት።የእግዚአብሔርን፡ታቦት፡ይሸከሙ፡ዘንድ፥ለዘለዓለሙም፡ያገለግሉት፡ዘንድ፡ እግዚአብሔር፡ከመረጣቸው፡ከሌዋውያን፡በቀር፡ማንም፡የእግዚአብሔርን፡ታቦት፡ይሸከም፡ዘንድ፡አይገ፟ባ፟ውም፡ አለ።
3ዳዊትም፡ወዳዘጋጀለት፡ስፍራ፡የእግዚአብሔርን፡ታቦት፡ያመጣ፡ዘንድ፡እስራኤልን፡ዅሉ፡ወደ፡ ኢየሩሳሌም፡ሰበሰበ።
4ዳዊትም፡የአሮንን፡ልጆችና፡ሌዋውያንን፡ሰበሰበ።
5ከቀአት፡ልጆች፤አለቃው፡ኡርኤል፥ወንድሞቹም፡መቶ፡ኻያ፤
6ከሜራሪ፡ልጆች፤አለቃው፡ዐሳያ፥ወንድሞቹም፡ኹለት፡መቶ፡ኻያ፤
7ከጌድሶን፡ልጆች፤አለቃው፡ኢዮኤል፥ወንድሞቹም፡መቶ፡ሠላሳ፤ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
8ከኤሊጻፋን፡ልጆች፤አለቃው፡ሸማያ፥ወንድሞቹም፡ኹለት፡መቶ፤
9ከኬብሮን፡ልጆች፤አለቃው፡ኤሊኤል፥ወንድሞቹም፡ሰማንያ፤
10ከዑዝኤል፡ልጆች፤አለቃው፡ዐሚናዳብ፥ወንድሞቹም፡መቶ፡ዐሥራ፡ኹለት።
11ዳዊትም፡ካህናቱን፡ሳዶቅንና፡አቢያታርን፥ሌዋውያንንም፡ ኡርኤልን፥ዐሳያን፥ኢዮኤልን፥ሸማያን፥ኤሊኤልን፥ዐሚናዳብንም፡ጠርቶ፦
12እናንተ፡የሌዋውያን፡አባቶች፡ቤቶች፡አለቃዎች፡ናችኹ፤ወዳዘጋጀኹለት፡ስፍራ፡የእስራኤልን፡አምላክ፡ የእግዚአብሔርን፡ታቦት፡ታመጡ፡ዘንድ፡እናንተና፡ወንድሞቻችኹ፡ተቀደሱ።
13ቀድሞም፡አልተሸከማችኹምና፥እንደ፡ሥርዐቱም፡አልፈለግነውምና፡አምላካችን፡እግዚአብሔር፡ በመካከላችን፡ስብራት፡አደረገ፡አላቸው።
14የእስራኤልንም፡አምላክ፡የእግዚአብሔርን፡ታቦት፡ያመጡ፡ዘንድ፡ካህናቱና፡ሌዋውያኑ፡ተቀደሱ።
15ሙሴም፡እንዳዘዘው፡እንደእግዚአብሔር፡ቃል፡የሌዋውያን፡ልጆች፡የእግዚአብሔርን፡ታቦት፡በትከሻቸው፡ ላይ፡በመሎጊያዎቹ፡ተሸከሙ።
16ዳዊትም፡በዜማ፡ዕቃ፡በመሰንቆና፡በበገና፡በጸናጽልም፡እንዲያዜሙ፥ድምፃቸውንም፡በደስታ፡ከፍ፡ እንዲያደርጉ፡መዘምራኑን፡ወንድሞቻቸውን፡ይሾሙ፡ዘንድ፡ለሌዋውያን፡አለቃዎች፡ተናገረ።
17ሌዋውያኑም፡የኢዮኤልን፡ልጅ፡ኤማንን፥ከወንድሞቹም፡የበራክያን፡ልጅ፡አሣፍን፥ከወንድሞቻቸውም፡ ከሜራሪ፡ልጆች፡የቂሳን፡ልጅ፡ኤታንን፥
18ከነርሱም፡ጋራ፡በኹለተኛው፡ተራ፡የኾኑትን፡ወንድሞቻቸውን፡ ዘካርያስን፥ቤንን፥ያዝኤልን፥ሰሚራሞትን፥ይሒኤልን፥ዑኒን፥ኤልያብን፥በናያስን፥መዕሴያን፥መቲትያን፥ኤሊ ፍሌሁን፥ሚቅንያን፥በረኛዎችንም፡ዖቤድኤዶምንና፡ይዒኤልን፡አቆሙ።
19መዘምራንም፡ኤማንና፡አሣፍ፡ኤታንም፡በናስ፡ጸናጽል፡ከፍ፡አድርገው፡ያሰሙ፡ነበር።
20ዘካርያስ፥ዓዝዔል፥ሰሚራሞት፥ይሒኤል፥ዑኒ፥ኤልያብ፥መዕሴያ፥በናያስ፡በመሰንቆ፡ምስጢር፡ነገር፡ ያዜሙ፡ነበር።
21መቲትያ፥ኤልፍሌሁ፥ሚቅኒያ፥ዖቤድኤዶም፥ይዒኤል፥ዓዛዝያ፡ስምንት፡አውታር፡ባለው፡በገና፡ይዘምሩ፡ ነበር።
22የሌዋውያኑም፡አለቃ፡ክናንያ፡በዜማ፡ላይ፡ተሹሞ፡ነበር።ብልኀተኛ፡ነበረና፡ዜማ፡ያስተምራቸው፡ነበር።
23በራክያና፡ሕልቃናም፡ለታቦቱ፡በረኛዎች፡ነበሩ።
24ካህናቱም፡ሰበንያ፥ኢዮሳፍጥ፥ናትናኤል፥ዐማሳይ፥ዘካርያስ፥በናያስ፥አልዓዛር፡በእግዚአብሔር፡ታቦይ፡ ፊት፡መለከት፡ይነፉ፡ነበር።ዖቤድኤዶምና፡ይሒያም፡ለታቦቱ፡በረኛዎች፡ነበሩ።
25ዳዊትም፥የእስራኤልም፡ሽማግሌዎች፥የሻለቃዎችም፡የእግዚአብሔርን፡የቃል፡ኪዳኑን፡ታቦት፡ከአቢዳራ፡ ቤት፡በደስታ፡ያመጡ፡ዘንድ፡ኼዱ።
26የእግዚአብሔርንም፡ቃል፡ኪዳን፡ታቦት፡የተሸከሙትን፡ሌዋውያንን፡እግዚአብሔር፡በረዳቸው፡ጊዜ፡ሰባት፡ በሬዎችና፡ሰባት፡አውራ፡በጎች፡ሠዉ።
27ዳዊትም፥ታቦቱንም፡የተሸከሙ፡ሌዋውያን፡ዅሉ፥መዘምራኑም፥የመዘምራኑም፡አለቃ፡ከናንያ፡የጥሩ፡ በፍታ፡ቀሚስ፡ለብሰው፡ነበር፤ዳዊትም፡የበፍታ፡ኤፉድ፡ነበረው።
28እንዲሁ፡እስራኤል፡ዅሉ፡ሆ፡እያሉ፡ቀንደ፡መለከትና፡እንቢልታ፡እየነፉ፥ጸናጽልና፡መሰንቆም፡በገናም፡ እየመቱ፥የእግዚአብሔርን፡የቃል፡ኪዳን፡ታቦት፡አመጡ።
29የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ኪዳን፡ታቦት፡ወደዳዊት፡ከተማ፡በደረሰ፡ጊዜ፡የሳኦል፡ልጅ፡ሜልኮል፡በመስኮት፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ኾና፡ተመለከተች፤ንጉሡም፡ዳዊት፡ሲዘፍንና፡ሲጫወት፡አይታ፡በልቧ፡ናቀችው።