Skip to content
← 1 Chronicles

Chapter 16 · Amharic

1 Chronicles

1የእግዚአብሔርንም፡ታቦት፡ይዘው፡ገቡ፥ዳዊትም፡በተከለለት፡ድንኳን፡ውስጥ፡አኖሩት፤የሚቃጠለውን፡ መሥዋዕትና፡የደኅንነቱን፡መሥዋዕትም፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡አቀረቡ።

2ዳዊትም፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕትና፡የደኅንነቱን፡መሥዋዕት፡ማቅረብ፡በፈጸመ፡ጊዜ፡በእግዚአብሔር፡ ስም፡ሕዝቡን፡ባረከ።

3ለእስራኤልም፡ለወንዱም፡ለሴቱም፡ለያንዳንዱ፡አንዳንድ፡እንጀራ፤አንዳንድም፡ቍራጭ፡ሥጋ፥አንዳንድም፡ የዘቢብ፡ጥፍጥፍ፡አካፈለ።

4በእግዚአብሔርም፡ታቦት፡ፊት፡ያገለግሉ፡ዘንድ፥የእስራኤልንም፡አምላክ፡እግዚአብሔርን፡ይወድሱት፡ ዘንድ፥ያመሰግኑትና፡ያከብሩትም፡ዘንድ፡ከሌዋውያን፡ወገን፡አቆመ።

5አለቃው፡አሣፍ፡ነበረ፤ከርሱም፡በዃላ፡ ዘካርያስ፥ይዒኤል፥ሰሚራሞት፥ይሒኤል፥መቲትያ፥ኤልያብ፥በናያስ፥ዖቤድኤዶም፥ይዒኤል፡በመሰንቆና፡ በበገና፡አሣፍም፡በጸናጽል፡ይዘምሩ፡ነበር።

6ካህናቱም፡በናያስና፡የሕዚኤል፡በእግዚአብሔር፡ቃል፡ኪዳን፡ታቦት፡ፊት፡ዅልጊዜ፡መለከት፡ይነፉ፡ነበር።

7በዚያም፡ቀን፡ዳዊት፡በአሣፍና፡በወንድሞቹ፡እጅ፡እግዚአብሔርን፡እንዲያመሰግኑ፡ትእዛዝን፡ሰጠ።

8እግዚአብሔርን፡አመስግኑ፥ስሙን፡ጥሩ፤ለአሕዛብ፡ሥራውን፡አውሩ።

9ተቀኙለት፥ዘምሩለት፤ተኣምራቱንም፡ዅሉ፡ተናገሩ።

10በቅዱስ፡ስሙ፡ተጓደዱ፤እግዚአብሔርን፡የሚፈልግ፡ልብ፡ደስ፡ይበለው።

11እግዚአብሔርን፡ፈልጉት፥ትጸናላችኹም፤ዅልጊዜ፡ፊቱን፡ፈልጉ።

13ባሪያዎቹ፡የእስራኤል፡ዘር፥ለርሱም፡የተመረጣችኹ፡የያዕቆብ፡ልጆች፡ሆይ፥የሠራትን፡ድንቅ፡ ዐስቡ፥ተኣምራቱንም፡የአፉንም፡ፍርድ።

14ርሱ፡እግዚአብሔር፡አምላካችን፡ነው፤ፍርዱ፡በምድር፡ዅሉ፡ነው።ቃል፡ኪዳኑን፡ለዘለዓለም፥እስከ፡ ሺሕ፡ትውልድ፡ያዘዘውን፡ቃሉን፡ዐሰበ፥

16ለአብርሃም፡ያደረገውን፥ለይሥሐቅም፡የማለውን፤

17ለያዕቆብ፡ሥርዐት፡እንዲኾን፡ለእስራኤልም፡የዘለዓለም፡ኪዳን፡እንዲኾን፡አጸና፤

18እንዲህም፡አለ፦ለአንተ፡የከነዓንን፡ምድር፡የርስታችኹን፡ገመድ፡እሰጣለኹ፤

19ይህም፡የኾነው፡እነርሱ፡በቍጥር፡ጥቂቶች፡ሰዎች፥እጅግ፡ጥቂቶችና፡ስደተኛዎች፡ሲኾኑ፡ነው።

20ከሕዝብ፡ወደ፡ሕዝብ፥ከመንግሥትም፡ወደ፡ሌላ፡ሕዝብ፡ዐለፉ።

22የቀባዃቸውን፡አትዳስሱ፥በነቢያቴም፡ክፉ፡አታድርጉ፡ብሎ፥ሰው፡ግፍ፡ያደርግባቸው፡ዘንድ፡ አልፈቀደም፤ስለ፡እነርሱም፡ነገሥታትን፡ገሠጸ።

23ምድር፡ዅሉ፡እግዚአብሔርን፡አመስግኑ፤ዕለት፡ዕለት፡ማዳኑን፡አውሩ።

24ክብሩን፡ለአሕዛብ፥ተኣምራቱንም፡ለወገኖች፡ዅሉ፡ንገሩ።

25እግዚአብሔር፡ታላቅ፥ምስጋናውም፡ብዙ፡ነውና፤በአማልክትም፡ዅሉ፡ላይ፡የተፈራ፡ነው።

26የአሕዛብ፡አማልክት፡ዅሉ፡ጣዖታት፡ናቸው፤እግዚአብሔር፡ግን፡ሰማያትን፡ሠራ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

27ክብርና፡ግርማ፡በፊቱ፥ኀይልና፡ደስታ፡በስፍራው፡ውስጥ፡ናቸው።

28የአሕዛብ፡ወገኖች፡ለእግዚአብሔር፡አምጡ፥ክብርንና፡ኀይልን፡ለእግዚአብሔር፡አምጡ።

29ለስሙ፡የሚገ፟ባ፟፡ክብርን፡ለእግዚአብሔር፡አምጡ፤ቍርባንን፡ይዛችኹ፡በፊቱ፡ግቡ፤በቅድስናው፡ስፍራ፡ ለእግዚአብሔር፡ስገዱ።

30ምድር፡ዅሉ፡በፊቱ፡ትነዋወጥ፤ዓለሙም፡እንዳይናወጥ፡ጸንቷል።

31ሰማያት፡ደስ፡ይበላቸው፥ምድርም፡ሐሴትን፡ታድርግ፤በአሕዛብም፡መካከል።እግዚአብሔር፡ነገሠ፡በሉ።

32ባሕርና፡ሞላዋ፡ትናወጥ፤በረሓ፡በርሷም፡ያሉ፡ዅሉ፡ሐሤትን፡ያድርጉ።

33በምድር፡ሊፈርድ፡ይመጣልና፥የዱር፡ዛፎች፡በዚያን፡ጊዜ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ደስ፡ይላቸዋል።

34ቸር፡ነውና፥ምሕረቱም፡ለዘለዓለም፡ነውና፥እግዚአብሔርን፡አመስግኑ።

35የመዳናችን፡አምላክ፡ሆይ፥አድነን፤ቅዱስ፡ስምኽን፡እናመሰግን፡ዘንድ፥በምስጋናኽም፡እንመካ፡ ዘንድ፥ከአሕዛብ፡ሰብስበኽ፡ታደገን፡በሉ።

36ከዘለዓለም፡እስከ፡ዘለዓለም፥የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡ይባረክ።ሕዝቡም፡ዅሉ፡አሜን፡ ይበሉ፤እግዚአብሔርንም፡ያመስግኑ።

37እንዲሁም፡በየቀኑ፡እንደሚገ፟ባ፟ቸው፡በታቦቱ፡ፊት፡ዘወትር፡ያገለግሉ፡ዘንድ፡አሣፍንና፡ ወንድሞቹን፥ዖቤድኤዶምንም፥ስድሳ፡ስምንቱንም፡ወንድሞቻቸውን፡በዚያ፡በእግዚአብሔር፡ቃል፡ኪዳን፡ታቦት፡ ፊት፡ተዋቸው።

38የኤዶታምም፡ልጅ፡ዖቤድኤዶምና፡ሖሳ፡በረኛዎች፡ይኾኑ፡ዘንድ፡ተዋቸው።

39ካህኑም፡ሳዶቅንና፡ካህናቱን፡ወንድሞቹን፡በገባዖን፡በኰረብታው፡መስገጃ፡ባለው፡በእግዚአብሔር፡ ማደሪያ፡ፊት፡አቆማቸው፥

40ለእስራኤልም፡ባዘዘው፡በእግዚአብሔር፡ሕግ፡እንደ፡ተጻፈ፡ዅሉ፡ለሚቃጠለው፡መሥዋዕት፡በሚኾነው፡ መሠዊያ፡ላይ፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕት፡ዅል፡ጊዜ፡ጧትና፡ማታ፡ለእግዚአብሔር፡ያቀርቡ፡ዘንድ።

41ምሕረቱም፡ለዘለዓለም፡ነውና፥እግዚአብሔርን፡ያመሰግኑ፡ዘንድ፡ኤማንንና፡ኤዶታምን፥በስማቸውም፡ የተጻፉትን፡ተመርጠው፡የቀሩትን፡ከነርሱ፡ጋራ፡አቆመ።

42ከነርሱም፡ጋራ፡ካህናቱ፡ከፍ፡አድርገው፡ለማሰማት፡መለከትና፡ጸናጽል፡ለእግዚአብሔርም፡መዝሙራት፡ የዜማ፡ዕቃ፡ይዘው፡ነበር፤የኤዶታምም፡ልጆች፡በረኛዎች፡ነበሩ።

43ሕዝቡ፡ዅሉ፡እያንዳንዱ፡ወደ፡ቤቱ፡ኼደ፤ዳዊትም፡ቤቱን፡ይባርክ፡ዘንድ፡ተመለሰ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source