1እንዲህም፡ኾነ፤ዳዊት፡በቤቱ፡በተቀመጠ፡ጊዜ፡ዳዊት፡ነቢዩን፡ናታንን፦እንሆ፥እኔ፡ከዝግባ፡በተሠራ፡ ቤት፡ተቀምጫለኹ፤የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ኪዳን፡ታቦት፡በመጋረጃዎች፡ውስጥ፡ተቀምጧል፡አለው።
2ናታንም፡ዳዊትን፦እግዚአብሔር፡ከአንተ፡ጋራ፡ነውና፥በልብኽ፡ያለውን፡ዅሉ፡አድርግ፡አለው።
3በዚያም፡ሌሊት፡የእግዚአብሔር፡ቃል፡ወደ፡ናታን፡መጣ፡እንዲህም፡አለው፦
5ኺድ፥ለባሪያዬ፡ለዳዊት፡ንገረው፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እስራኤልን፡ካወጣኹበት፡ቀን፡ ዠምሮ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡ከድንኳን፡ወደ፡ድንኳን፥ከማደሪያም፡ወደ፡ማደሪያ፡እኼድ፡ነበር፡እንጂ፡በቤት፡ ውስጥ፡አልኖርኹምና፡የምኖርበትን፡ቤት፡አትሠራልኝም።
6ከእስራኤል፡ዅሉ፡ጋራ፡ባለፍኹበት፡ስፍራ፡ዅሉ፦ስለ፡ምን፡ቤትን፡ከዝግባ፡ዕንጨት፡ አልሠራችኹልኝም፧ብዬ፡ሕዝቤን፡ይጠብቅ፡ዘንድ፡ከእስራኤል፡ፈራጆች፡ላዘዝኹት፡ለአንዱ፡በእውኑ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ተናግሬያለኹን፧
7አኹንም፡ባሪያዬን፡ዳዊትን፡እንዲህ፡በለው፦የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦አንተ፡ መንጋውን፡ስትከተል፡በሕዝቤ፡በእስራኤል፡ላይ፡አለቃ፡ትኾን፡ዘንድ፡ከበግ፡ጥበቃ፡ወሰድኹኽ።
8በኼድኽበትም፡ዅሉ፡ከአንተ፡ጋራ፡ነበርኹ፥ጠላቶችኽንም፡ዅሉ፡ከፊትኽ፡አጠፋኹ፤በምድርም፡ላይ፡ እንዳሉ፡እንደታላላቆች፡ስም፡ለአንተ፡ስም፡አደርጋለኹ።
10ለሕዝቤም፡ለእስራኤል፡ስፍራ፡አደርግለታለኹ፥እተክለውማለኹ፥በስፍራውም፡ይቀመጣል፥ከዚያም፡ በዃላ፡አይናወጥም፤እንደቀድሞው፡ዘመንና፡በሕዝቤም፡በእስራኤል፡ላይ፡ፈራጆች፡እንዳስነሣኹበት፡ጊዜ፡ ግፈኛዎች፡ተመልሰው፡አያስጨንቁትም፤ጠላቶችኽንም፡ዅሉ፡አዋርዳቸዋለኹ።እግዚአብሔር፡ደግሞ፡ቤት፡ እንዲሠራልኽ፡እነግርኻለኹ።
11ወደ፡አባቶችኽም፡ትኼድ፡ዘንድ፡ዕድሜኽ፡በተፈጸመ፡ጊዜ፡ከልጆችኽ፡የሚኾነውን፡ዘርኽን፡ከአንተ፡ በዃላ፡አስነሣለኹ፤መንግሥቱንም፡አጸናለኹ።
12ርሱ፡ቤት፡ይሠራልኛል፤ዙፋኑንም፡ለዘለዓለም፡አጸናለኹ።
13እኔም፡አባት፡እኾነዋለኹ፥ርሱም፡ልጅ፡ይኾነኛል፤ከአንተ፡አስቀድሞ፡ከነበረው፡እንዳራቅኹ፥ምሕረቴን፡ ከርሱ፡አላርቅም።
14በቤቴና፡በመንግሥቴም፡ለዘለዓለም፡አቆመዋለኹ፤ዙፋኑም፡ለዘለዓለም፡ይጸናል።
15እንደዚህ፡ነገር፡ዅሉ፡እንደዚህም፡ራእይ፡ዅሉ፡ናታን፡ለዳዊት፡ነገረው።
16ንጉሡም፡ዳዊት፡ገባ፥በእግዚአብሔርም፡ፊት፡ተቀምጦ፡እንዲህ፡አለ፦አቤቱ፡አምላክ፡ሆይ፥እስከዚህ፡ ያደረስኸኝ፡እኔ፡ማን፡ነኝ፧ቤቴስ፡ምንድር፡ነው፧
17አምላክ፡ሆይ፡ይህ፡በፊትኽ፡ጥቂት፡ነበረ፤አቤቱ፡አምላክ፡ሆይ፥ስለ፡ባሪያኽ፡ቤት፡ደግሞ፡ለሩቅ፡ ዘመን፡ተናገርኽ፤እንደ፡አንድ፡ባለማዕርግ፡ሰው፡ተመለከትኸኝ።
18አንተ፡ባሪያኽን፡ታውቀዋለኽና፡ለባሪያኽ፡ስለ፡ተደረገ፡ክብር፡ዳዊት፡ጨምሮ፡የሚለው፡ምንድር፡ነው፧
19አቤቱ፥ይህን፡ታላቅ፡ነገር፡ዅሉ፡ታስታውቀው፡ዘንድ፡ስለ፡ባሪያኽ፡እንደ፡ልብኽም፡ይህን፡ተኣምራት፡ ዅሉ፡አድርገኻል።
20አቤቱ፥እንዳንተ፡ያለ፡የለም፥በዦሯችንም፡እንደ፡ሰማን፡ዅሉ፡ከአንተ፡በቀር፡አምላክ፡የለም።
21አንተ፡እግዚአብሔር፡ከግብጽ፡ካወጣኸው፡ከሕዝብኽ፡ፊት፡አሕዛብን፡በማሳደድ፡በታላቅና፡በሚያስፈራ፡ ነገር፡ለአንተ፡ስም፡ታደርግ፡ዘንድ፥ለአንተም፡ሕዝብ፡ትቤዥ፡ዘንድ፡እንደኼድኽለት፡እንዳንተ፡ሕዝብ፡ እንደ፡እስራኤል፡ያለ፡በምድር፡ላይ፡ሌላ፡ሕዝብ፡አለን፧
22ሕዝብኽንም፡እስራኤልን፡ለዘለዓለም፡ሕዝብኽ፡አደረግኸው፤አንተም፥አቤቱ፥አምላክ፡ኾነኸዋል።
23አኹንም፥አቤቱ፥ስለ፡ባሪያኽና፡ስለ፡ቤቱ፡የተናገርኸው፡ለዘለዓለም፡የጸና፡ይኹን፤አንደ፡ተናገርኽም፡ አድርግ።
24የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡ርሱ፡የእስራኤል፡አምላክ፡ነው፥በእውነት፡የእስራኤል፡አምላክ፡ነው፡ ይባል፡ዘንድ፡ስምኽ፡ለዘለዓለም፡ጽኑና፡ታላቅ፡ይኹን፤የባሪያኽም፡የዳዊት፡ቤት፡በፊትኽ፡ጸንቷል።
25አምላኬ፡ሆይ፥ቤት፡እንድሠራለት፡ለባሪያኽ፡ገልጠኻልና፥ስለዚህ፡ባሪያኽ፡ወዳንተ፡ይጸልይ፡ዘንድ፡ በልቡ፡ደፈረ።
26አኹንም፥አቤቱ፥አንተ፡አምላክ፡ነኽ፥ይህንም፡መልካም፡ነገር፡ለባሪያኽ፡ተናግረኻል።
27አኹንም፡በፊትኽ፡ለዘለዓለም፡ይኖር፡ዘንድ፡የባሪያኽን፡ቤት፡እንድትባርክ፡ ፈቅደኻል፤አንተም፥አቤቱ፥ባርከኸዋል፥ለዘለዓለምም፡ቡሩክ፡ይኾናል። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org