1እስራኤልም፡ዅሉ፡በየትውልዳቸው፡ተቈጠሩ፤እንሆም፥በእስራኤል፡ነገሥታት፡መጽሐፍ፡ ተጽፈዋል።ይሁዳም፡ስለ፡ኀጢአታቸው፡ወደ፡ባቢሎን፡ተማረኩ።
2በአውራጃዎቻቸውና፡በከተማዎቻቸው፡መዠመሪያ፡የተቀመጡ፡እስራኤልና፡ካህናት፡ሌዋውያንም፡ናታኒምም፡ ነበሩ።
3ከይሁዳ፡ልጆችና፡ከብንያም፡ልጆች፡ከኤፍሬምና፡ከምናሴ፡ልጆች፡በኢየሩሳሌም፡ተቀመጡ።
4ከይሁዳ፡ልጅ፡ከፋሬስ፡ልጆች፡የባኒ፡ልጅ፡የአምሪ፡ልጅ፡የዖምሪ፡ልጅ፡የዐሚሁድ፡ልጅ፡ዑታይ፡ደግሞ፡ ተቀመጠ።
5ከሴሎናውያንም፡በኵሩ፡ዐሣያና፡ልጆቹ።
6ከዛራም፡ልጆች፡ይዑኤልና፡ወንድሞቻቸው፥ስድስት፡መቶ፡ዘጠና።
7ከብንያምም፡ልጆች፡የሐስኑአ፡ልጅ፡የሆዳይዋ፡ልጅ፡የሜሱላም፡ልጅ፡ሰሉ፤
8የይሮሐም፡ልጅ፡ብኔያ፤የሚክሪ፡ልጅ፡የዖዚ፡ልጅ፡ኤላ፤የዪብኒያ፡ልጅ፡የራጉኤል፡ልጅ፡የሰፋጥያስ፡ ልጅ፡ሜሱላም፤
9በየትውልዳቸውም፡ወንድሞቻቸው፡ዘጠኝ፡መቶ፡ኀምሳ፡ስድስት፡ነበሩ፤እነዚህ፡ሰዎች፡ዅሉ፡ የአባቶቻቸው፡ቤቶች፡አለቃዎች፡ነበሩ።
10ከካህናቱም፡ዮዳዔ፥ዮአሪብ፥ያኪን፤ 222ዕብ.፥አቢናዳብ፤አለዚያም፡ዐሚናዳብ፡(ኪ.ወ.ክ.፥627)። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
11የእግዚአብሔርም፡ቤት፡አለቃ፡የአኪጦብ፡ልጅ፡የመራዮት፡ልጅ፡የሳዶቅ፡ልጅ፡ሜሱላም፡ልጅ፡ የኬልቅያስ፡ልጅ፡ዐዛርያስ፤
12የመልኪያ፡ልጅ፡የጳስኮር፡ልጅ፡የይሮሐም፡ልጅ፡ዓዳያ፤የኢሜር፡ልጅ፡የምሺላሚት፡ልጅ፡የሜሱላም፡ ልጅ፡የየሕዜራ፡ልጅ፡የዓዲኤል፡ልጅ፡መዕሣይ፤
13የአባቶቻቸውም፡ቤቶች፡አለቃዎች፡ወንድሞቻቸው፡ሺሕ፡ሰባት፡መቶ፡ስድሳ፡ነበሩ፤ለእግዚአብሔር፡ ቤት፡ማገልገል፡ሥራ፡እጅግ፡ብልኀተኛዎች፡ሰዎች፡ነበሩ።
14ከሌዋውያንም፡የሜራሪ፡ልጆች፡የዐሳብያ ፡ልጅ፡የዐዝሪቃም፡ልጅ፡የዐሱብ ፡ልጅ፡ሸማያ፤
15በቅበቃር፥ዔሬስ ፥ጋላል፥የአሣፍ፡ልጅ፡የዝክሪ፡ልጅ፡የሚካ፡ልጅ፡መታንያ፤
16የኤዶታም፡ልጅ፡የጋላል፡ልጅ፡የሰሙስ፡ልጅ፡ዐብድያ ፤በነጦፋውያንም፡መንደሮች፡የተቀመጠው፡ የሕልቃና፡ልጅ፡የአሣ፡ልጅ፡በራክያ።
17በረኛዎችም፡ሰሎም፥ዐቁብ፥ጤልሞን፥አኂማን፥ወንድሞቻቸውም፡ነበሩ፤ሰሎምም፡አለቃ፡ነበረ።
18እስከ፡ዛሬም፡ድረስ፡በንጉሥ፡በር፡በምሥራቅ፡በኩል፡ነበሩ፤ለሌዊ፡ልጆች፡ሰፈር፡በረኛዎች፡ነበሩ።
19የቆሬም፡ልጅ፡የአብያሣፍ፡ልጅ፡የቆሬ፡ልጅ፡ሰሎም፡ከአባቱም፡ቤት፡የነበሩ፡ወንድሞቹ፡ቆሬያውያን፡ በማገልገል፡ሥራ፡ላይ፡ነበሩ፥የድንኳኑንም፡መድረክ፡ይጠብቁ፡ነበር።አባቶቻቸውም፡የእግዚአብሔርን፡ሰፈር፡ መግቢያ፡ጠብቀው፡ነበር።
20አስቀድሞም፡የአልዓዛር፡ልጅ፡ፊንሐስ፡አለቃቸው፡ነበረ፤እግዚአብሔርም፡ከርሱ፡ጋራ፡ነበረ።
21የሜሱላም፡ልጅ፡ዘካርያስ፡የመገናኛው፡ድንኳን፡ደጅ፡በረኛ፡ነበረ።
22የመድረኩ፡በረኛዎች፡ይኾኑ፡ዘንድ፡የተመረጡ፡እነዚህ፡ዅሉ፡ኹለት፡መቶ፡ዐሥራ፡ኹለት፡ ነበሩ።ዳዊትና፡ነቢዩ፡ሳሙኤል፡በሥራቸው፡ያቆሟቸው፡እነዚህ፡በመንደሮቻቸው፡በየትውልዳቸው፡ተቈጠሩ።
23እነርሱና፡ልጆቻቸውም፡በእግዚአብሔር፡ቤት፡በድንኳኑ፡ደጆች፡ላይ፡ዘበኛዎች፡ነበሩ።
24በአራቱ፡ማእዘኖች፥በምሥራቅ፥በምዕራብ፥በሰሜን፥በደቡብ፥በረኛዎች፡ነበሩ።
25ወንድሞቻቸውም፡በመንደሮቻቸው፡ኾነው፥በየሰባትም፡ቀን፡ከነርሱ፡ጋራ፡ሊኾኑ፡ከጊዜ፡ወደ፡ጊዜ፡ ይገቡ፡ነበር።
26ከሌዋውያንም፡የነበሩ፡አራቱ፡የበረኛዎች፡አለቃዎች፡ዘወትር፡በሥራቸው፡ይቀመጡ፡ ነበር፤በእግዚአብሔርም፡ቤት፡ባሉ፡ጓዳዎችና፡ቤተ፡መዛግብት፡ላይ፡ነበሩ።
27የእግዚአብሔርንም፡ቤት፡የሚጠብቁ፥ጧት፡ጧትም፡ደጆቹን፡የሚከፍቱ፡እነርሱ፡ነበሩና፥በዚያ፡ያድሩ፡ ነበር።
28ዕቃውም፡በቍጥር፡ይገባና፡ይወጣ፡ነበርና፥ከነዚህ፡አንዳንዱ፡በማገልገያው፡ዕቃ፡ላይ፡ሹሞች፡ነበሩ።
29ከነርሱም፡አንዳንዶቹ፡በመቅደሱ፡ዕቃ፡ዅሉ፡በመልካሙም፡ዱቄት፥በወይን፡ ጠጁ፥በዘይቱም፥በዕጣኑም፥በሽቱውም፡ላይ፡ሹሞች፡ነበሩ።
30ከካህናቱም፡ልጆች፡አንዳንዶቹ፡የሽቱውን፡ቅባት፡ያጣፍጡ፡ነበር።
31የቆሬያዊውም፡የሰሎም፡በኵር፡ሌዋዊው፡ማቲትያ፡በምጣድ፡በሚጋገረው፡ነገር፡ላይ፡ሹም፡ነበረ።
32በየሰንበቱም፡ያዘጋጁ፡ዘንድ፡ከወንድሞቻቸው፡ከቀአታውያን፡አንዳንዱ፡በገጹ፡ኅብስት፡ላይ፡ሹሞች፡ ነበሩ። 223 ዕብ.፥ሐሻብያህ፡(ሐሰቦ፡እግዚእ•የጌታ፡ዐሰበው)። 224 ዕብ.፥ሐሹብ፡(ሐሳቢ•ዐሳቢ)። 225 ዕብ.፥ሔሬሽ። 226 ዕብ.፥ዖባድያህ፡(ዐብደ፡እግዚእ፥የጌታ፡አገልጋይ)። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
33ከሌዋውያኑም፡ወገን፡የአባቶቻቸው፡ቤቶች፡አለቃዎች፡የነበሩ፡መዘምራን፡እነዚህ፡ናቸው፤ሥራቸውም፡ ሌሊትና፡ቀን፡ነበረና፡ያለሌላ፡ሥራ፡በየጓዳቸው፡ይቀመጡ፡ነበር።
34እነዚህ፡ከሌዋውያን፡የአባቶቻቸው፡ቤቶች፡አለቃዎች፡በየትውልዳቸው፡አለቃዎች፡ነበሩ።እነዚህም፡ በኢየሩሳሌም፡ይቀመጡ፡ነበር።
35የሚስቱ፡ስም፡መዓካ፡የነበረው፡የገባዖን፡አባት፡ይዒኤል፥
36የበኵር፡ልጁም፡ዐብዶን፥
37ዱር፥ቂስ፥በዓል፥ኔር፥ናዳብ፥ጌዶር፥አኂዮ፥ዛኩር፥ሚቅሎት፥በገባኦን፡ይቀመጡ፡ነበር።
38ሚቅሎትም፡ሳምአን፡ወለደ፤እነርሱ፡ደግሞ፡ከወንድሞቻቸው፡ጋራ፡በኢየሩሳሌም፡በወንድሞቻቸው፡ፊት፡ ለፊት፡ይቀመጡ፡ነበር።
39ኔርም፡ቂስን፡ወለደ፤ቂስም፡ሳኦልን፡ወለደ፤ሳኦልም፡ዮናታንን፥ሚልኪሳን፥ዐሚናዳብን፥አስበዓልን፡ ወለደ።
40የዮናታንም፡ልጅ፡መሪበዓል፡ነበረ፤መሪበዓልም፡ሚካን፡ወለደ።
41የሚካም፡ልጆች፡ፒቶን፥ሜሌክ፥ታሬዓ፥አካዝ፡ነበሩ።
42አካዝም፡የዕራን፡ወለደ፤የዕራም፡ዓሌሜትን፥ዓዝሞትን፥ዘምሪን፡ወለደ፤ዘምሪም፡ሞጻን፡ወለደ።
43ሞጻም፡ቢንዓን፡ወለደ፥ልጁም፡ረፋያ፡ነበረ፥ልጁ፡ኤልዓሣ፥ልጁ፡ኤሴል፤
44ለኤሴልም፡ስድስት፡ልጆች፡ነበሩት፤ስማቸውም፡ይህ፡ ነበረ፤ዐዝሪቃም፥ቦክሩ፥እስማኤል፥ሸዓሪያ፥ዐብድዩ፥ሐናን፤እነዚህ፡የኤሴል፡ልጆች፡ነበሩ።