1ከዚህም፡በዃላ፡የዐሞን፡ልጆች፡ንጉሥ፡ናዖስ፡ሞተ፥ልጁም፡በርሱ፡ፋንታ፡ነገሠ።
2ዳዊትም፦አባቱ፡ስላደረገልኝ፡ወረታ፡እኔ፡ለናዖስ፡ልጅ፡ለሐኖን፡ቸርነት፡አደርጋለኹ፡አለ።ዳዊትም፡ አባቱ፡ስለ፡ሞተ፡ሊያጽናናው፡መልእክተኛዎችን፡ላከ፤የዳዊትም፡ባሪያዎች፡ሊያጽናኑት፡ወደ፡ሐኖን፡ ወደዐሞን፡ልጆች፡ምድር፡መጡ።
3የዐሞን፡ልጆች፡አለቃዎች፡ግን፡ሐኖንን፦ዳዊት፡አባትኽን፡አክብሮ፡የሚያጽናኑኽን፡ወዳንተ፡የላከ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ይመስልኻልን፧ባሪያዎቹስ፡አገሪቱን፡ለመመርመር፥ለማጥፋት፥ለመሰለልም፡ወዳንተ፡የመጡ፡ አይደሉምን፧አሉት።
4ሐኖንም፡የዳዊትን፡ባሪያዎች፡ወስዶ፡አስላጫቸው፥ልብሳቸውንም፡እስከ፡ወገባቸው፡ድረስ፡ከኹለት፡ቀዶ፟፡ ሰደዳቸው።
5ወሬኛዎችም፡ኼደው፡በሰዎቹ፡ላይ፡የተደረገውን፡ለዳዊት፡አስታወቁት።ሰዎቹም፡በብዙ፡ ዐፍረዋልና፥ተቀባዮች፡ላከ፤ንጉሡም፦ጢማችኹ፡እስኪያድግ፡ድረስ፡በኢያሪኮ፡ተቀመጡ፥ከዚያም፡በዃላ፡ ተመለሱ፡አለ።
6የዐሞንም፡ልጆች፡በዳዊት፡ዘንድ፡እንደ፡ተጠሉ፡ባዩ፡ጊዜ፡ሐኖንና፡የዐሞን፡ልጆች፡ ከመስጴጦምያ፥ከአራምመዓካ፥ከሱባ፡ሠረገላዎችንና፡ፈረሰኛዎችን፡ይቀጥሩ፡ዘንድ፡አንድ፡ሺሕ፡መክሊት፡ ብር፡ላኩ።
7ሠላሳ፡ኹለትም፡ሺሕ፡ሠረገላዎች፡የመዓካንም፡ንጉሥ፡ሕዝቡንም፡ቀጠሩ፤መጥተውም፡በሜድባ፡ፊት፡ ለፊት፡ሰፈሩ።የዐሞንም፡ልጆች፡ከየከተማዎቻቸው፡ተሰብስበው፡ወደ፡ሰልፍ፡መጡ።
8ዳዊትም፡ይህ፡በሰማ፡ጊዜ፡ኢዮአብንና፡የኀያላኑን፡ሰራዊት፡ዅሉ፡ላከ።
9የዐሞንም፡ልጆች፡ወጥተው፡በከተማዪቱ፡በር፡አጠገብ፡ተሰለፉ፤የመጡትም፡ነገሥታት፡ለብቻቸው፡ በሜዳው፡ላይ፡በሩ።
10ኢዮአብም፡በፊትና፡በዃላ፡ሰልፍ፡እንደ፡ከበበው፡ባየ፡ጊዜ፡ከእስራኤል፡ምርጥ፡ምርጦችን፡ዅሉ፡ለይቶ፡ በሶርያውያን፡ላይ፡አሰለፋቸው።
11የቀረውንም፡ሕዝብ፡ለወንድሙ፡ለአቢሳ፡ሰጠው፥በዐሞንም፡ልጆች፡ላይ፡ተሰለፉ።
12ርሱም፦ሶርያውያን፡ቢበረቱብኝ፡ርዳኝ፤የዐሞንም፡ልጆች፡ቢበረቱብኽ፡እረዳኻለኹ።
13አይዞኽ፥ስለ፡ሕዝባችንና፡ስለአምላካችንም፡ከተማዎች፡እንበርታ፤እግዚአብሔርም፡ደስ፡ያሠኘውን፡ ያድርግ፡አለ።
14ኢዮአብና፡ከርሱም፡ጋራ፡የነበረው፡ሕዝብ፡ለሰልፍ፡ወደሶርያውያን፡ፊት፡ቀረቡ፥እነርሱም፡ከፊቱ፡ሸሹ።
15የዐሞንም፡ልጆች፡ሶርያውያን፡እንደ፡ሸሹ፡ባዩ፡ጊዜ፡እነርሱ፡ደግሞ፡ከወንድሙ፡ከአቢሳ፡ፊት፡ ሸሹ፥ወደ፡ከተማዪቱም፡ገቡ።ኢዮአብም፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡መጣ።
16ሶርያውያንም፡በእስራኤል፡ፊት፡እንደ፡ተሸነፉ፡ባዩ፡ጊዜ፡መልእክተኛዎች፡ልከው፡በወንዝ፡ማዶ፡ የነበሩትን፡ሶርያውያን፡አስመጡ፤የአድርዐዛርም፡ሰራዊት፡አለቃ፡ሾፋክ፡በፊታቸው፡ነበረ።
17ዳዊትም፡በሰማ፡ጊዜ፡እስራኤልን፡ዅሉ፡ሰበሰበ፥ዮርዳኖስንም፡ተሻግሮ፡መጣባቸው፥ከነርሱም፡ጋራ፡ ተዋጋ፤ዳዊትም፡በሶርያውያን፡ላይ፡በተሰለፈ፡ጊዜ፡እነርሱ፡ከርሱ፡ጋራ፡ተዋጉ።
18ሶርያውያንም፡ከእስራኤል፡ፊት፡ሸሹ፤ዳዊትም፡ከሶርያውያን፡ሰባት፡ሺሕ፡ሠረገለኛዎች፥አርባ፡ሺሕም፡ እግረኛዎች፡ገደለ፥የሰራዊቱንም፡አለቃ፡ሾፋክን፡ገደለ።
19የአድርዐዛርም፡ባሪያዎች፡በእስራኤል፡ፊት፡እንደ፡ተሸነፉ፡ባዩ፡ጊዜ፡ከዳዊት፡ጋራ፡ ታረቁ፥ገበሩለትም፤ሶርያውያንም፡ከዚያ፡ወዲያ፡የዐሞንን፡ልጆች፡ይረዱ፡ዘንድ፡እንቢ፡አሉ።