1እንዲህም፡ኾነ፤በዓመት፡መለወጫ፡ነገሥታት፡ወደ፡ሰልፍ፡በሚወጡበት፡ጊዜ፡ኢዮአብ፡ሰራዊቱን፡ አወጣ፥የዐሞንንም፡ልጆች፡አገር፡አጠፋ፤መጥቶም፡ረባትን፡ከበበ።ዳዊትም፡በኢየሩሳሌም፡ቈይቶ፡ነበር።
2ኢዮአብም፡ረባትን፡መቶ፟፡አፈረሳት።ዳዊትም፡የንጉሣቸውን፡ዘውድ፡ከራሱ፡ላይ፡ወሰደ፥ክብደቱም፡ አንድ፡መክሊት፡ወርቅ፡ያኽል፡ነበር፥ክቡርም፡ዕንቍ፡ነበረበት፥በዳዊትም፡ራስ፡ላይ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org አስቀመጡት፤ከከተማዪቱም፡እጅግ፡ብዙ፡ምርኮ፡አወጣ።
3በውስጧም፡የነበረውን፡ሕዝብ፡አውጥቶ፡በመጋዝና፡በብረት፡መቈፈሪያ፡በመጥረቢያም፡እንዲሠሩ፡ አደረጋቸው።እንዲሁም፡ዳዊት፡በዐሞን፡ልጆች፡ከተማዎች፡ዅሉ፡አደረገ።ዳዊትም፡ሕዝቡም፡ዅሉ፡ወደ፡ ኢየሩሳሌም፡ተመለሱ።
4ከዚህም፡በዃላ፡በጌዝር፡ላይ፡ከፍልስጥኤማውያን፡ጋራ፡ሰልፍ፡ኾነ፤ኩሳታዊውም፡ሴቦካይ፡ከራፋይም፡ ወገን፡የነበረውን፡ሲፋይን፡ገደለ።
5ደግሞም፡ከፍልስጥኤማውያን፡ጋራ፡ሰልፍ፡ነበረ፤የያዒርም፡ልጅ፡ኤልያናን፡የጦሩ፡የቦ፡እንደ፡ሸማኔ፡ መጠቅለያ፡የነበረውን፡የጌት፡ሰው፡የጎልያድን፡ወንድም፡ለሕሚን፡ገደለ።
6ደግሞ፡በጌት፡ላይ፡ሰልፍ፡ነበረ፤ከዚያም፡በእጁና፡በእግሩ፡ስድስት፡ስድስት፡ዅላዅሉ፡ኻያ፡አራት፡ ጣቶች፡ያሉት፡አንድ፡ረዥም፡ሰው፡ነበረ፤ርሱም፡ደግሞ፡ከራፋይም፡የተወለደ፡ነበረ።
7እስራኤልንም፡በተገዳደረ፡ጊዜ፡የዳዊት፡ወንድም፡የሳምዓ፡ልጅ፡ዮናታን፡ገደለው።
8እነዚያም፡በጌት፡ውስጥ፡ከራፋይም፡የተወለዱ፡ነበሩ፤በዳዊትም፡እጅ፡በባሪያዎቹም፡እጅ፡ወደቁ።