Skip to content
← 1 Chronicles

Chapter 21 · Amharic

1 Chronicles

1ሰይጣን ም፡በእስራኤል፡ላይ፡ተነሣ፥እስራኤልንም፡ይቈጥር፡ዘንድ፡ዳዊትን፡አንቀሳቀሰው።

2ዳዊትም፡ኢዮአብንና፡የሕዝቡን፡አለቃዎች፦ኺዱ፥ከቤርሳቤሕ፡ዠምሮ፡እስከ፡ዳን፡ድረስ፡እስራኤልን፡ ቍጠሩ፥ድምራቸውንም፡ዐውቅ፡ዘንድ፡አስታውቁኝ፡አላቸው።

3ኢዮአብም፦እግዚአብሔር፡ሕዝቡን፡በአኹኑ፡ላይ፡መቶ፡ዕጥፍ፡ይጨምር፤ጌታዬ፡ንጉሥ፡ሆይ፥ዅሉ፡ የጌታዬ፡ባሪያዎች፡አይደሉምን፧ይህን፡ነገር፡ጌታዬ፡ለምን፡ይሻል፧በእስራኤል፡ላይ፡በደል፡ስለ፡ምን፡ ያመጣል፧

4ነገር፡ግን፥የንጉሡ፡ቃል፡በኢዮአብ፡ላይ፡አሸነፈ፤ኢዮአብም፡ወጥቶ፡በእስራኤል፡ዅሉ፡ላይ፡ ተዘዋወረ፥ወደ፡ኢየሩሳሌምም፡መጣ።

5ኢዮአብም፡የቈጠራቸውን፡የሕዝቡን፡ድምር፡ለዳዊት፡ሰጠ፤ከእስራኤልም፡ዅሉ፡አንድ፡ሚልዮን፡ከመቶ፡ ሺሕ፡ሰይፍ፡የሚመዙ፟፡ሰዎችን፡አገኘ፤ከይሁዳም፡አራት፡መቶ፡ሰባ፡ሺሕ፡ሰይፍ፡የሚመዙ፟፡ሰዎችን፡አገኘ።

6የንጉሡ፡ትእዛዝ፡ግን፡በኢዮአብ፡ዘንድ፡የተጠላ፡ነበርና፥ሌዊና፡ብንያም፡ከነርሱ፡ጋራ፡አልተቈጠሩም።

7ከዚህም፡ነገር፡የተነሣ፡እግዚአብሔር፡ተቈጣ፥እስራኤልንም፡ቀሠፈ።

8ዳዊትም፡እግዚአብሔርን፦ይህን፡በማድረግ፡እጅግ፡በድያለኹ፤አኹን፡ግን፡ታላቅ፡ስንፍና፡ አድርጌያለኹና፡የባሪያኽን፡ኀጢአት፡ታስወግድ፡ዘንድ፡እለምንኻለኹ፡አለው።

9እግዚአብሔርም፡ለዳዊት፡ባለራእይ፡ለጋድ።

10ኺድ፥ለዳዊት፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ሦስቱን፡ነገሮች፡በፊትኽ፡አኖራለኹ፤አደርግብኽ፡ ዘንድ፡ከነርሱ፡አንዱን፡ምረጥ፡ብለኽ፡ንገረው፡ብሎ፡ተናገረው።

11ጋድም፡ወደ፡ዳዊት፡መጥቶ፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦የምትወደ፟ውን፡ምረጥ፤

12የሦስት፡ዓመት፡ራብ፥ወይም፡ሦስት፡ወር፡የጠላቶችኽ፡ሰይፍ፡እንዲያገኝኽ፡ከጠላቶችኽ፡ መሰደድን፥ወይም፡ሦስት፡ቀን፡የእግዚአብሔር፡ሰይፍ፡ቸነፈርም፡በምድር፡ላይ፡መኾንን፥የእግዚአብሔርም፡ መልአክ፡በእስራኤል፡ምድር፡ዅሉ፡ማጥፋትን፡ምረጥ፤አኹንም፡ለላከኝ፡ምን፡እንድመልስ፡ተመልከት፡ አለው። 228 ዕብ.፥ሳጣን፡(ሰይጣን•ጠላት፥ባላጋራ፥ከሳሽ፥አሳጭ)። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

13ዳዊትም፡ጋድን፦እጅግ፡ተጨንቄያለኹ፤ምሕረቱ፡ብዙ፡ነውና፥በእግዚአብሔር፡እጅ፡ልውደቅ፤በሰው፡ እጅ፡ግን፡አልውደቅ፡አለው።

14እግዚአብሔርም፡በእስራኤል፡ላይ፡ቸነፈርን፡ሰደደ፤ከእስራኤልም፡ሰባ፡ሺሕ፡ሰዎች፡ወደቁ።

15እግዚአብሔርም፡ያጠፋት፡ዘንድ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡መልአክን፡ሰደደ፤ሊያጠፋትም፡በቀረበ፡ጊዜ፡ እግዚአብሔር፡አይቶ፡ስለ፡ክፉው፡ነገር፡ተጸጸተ፥የሚያጠፋውንም፡መልአክ፦በቃኽ፤አኹን፡እጅኽን፡ መልስ፡አለው።የእግዚአብሔርም፡መልአክ፡በኢያቡሳዊው፡በኦርና፡ዐውድማ፡አጠገብ፡ቆሞ፡ነበር።

16ዳዊትም፡ዐይኖቹን፡አነሣ፤የእግዚአብሔር፡መልአክ፡በምድርና፡በሰማይ፡መካከል፡ቆሞ፥የተመዘዘም፡ ሰይፍ፡በእጁ፡ኾኖ፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡ተዘርግቶ፡አየ።ዳዊትም፡ሽማግሌዎችም፡ማቅ፡ለብሰው፡በግንባራቸው፡ ተደፉ።

17ዳዊትም፡እግዚአብሔርን፦ሕዝቡ፡ይቈጠር፡ዘንድ፡ያዘዝኹ፡እኔ፡አይደለኹምን፧የበደልኹና፡ክፉ፡ የሠራኹ፡እኔ፡ነኝ፤እነዚህ፡በጎች፡ግን፡ምን፡አድርገዋል፧አቤቱ፡አምላኬ፡ሆይ፥እጅኽ፡በእኔና፡በአባቴ፡ ቤት፡ላይ፡ትኹን፥ነገር፡ግን፥ይቀሠፍ፡ዘንድ፡በሕዝብኽ፡ላይ፡አትኹን፡አለው።

18የእግዚአብሔርም፡መልአክ፡ዳዊት፡ወጥቶ፡በኢያቡሳዊው፡በኦርና፡ዐውድማ፡ላይ፡ለእግዚአብሔር፡ መሠዊያ፡ይሠራ፡ዘንድ፡ለዳዊት፡እንዲነግረው፡ጋድን፡አዘዘው።

19ዳዊትም፡በእግዚአብሔር፡ስም፡እንደተናገረው፡እንደ፡ጋድ፡ነገር፡ወጣ።

20ኦርናም፡ዘወር፡ብሎ፡መልአኩን፡አየ፥ከርሱም፡ጋራ፡የነበሩ፡አራቱ፡ልጆቹ፡ተሸሸጉ፤ኦርናም፡ስንዴ፡ ያበራይ፡ነበር።

21ዳዊትም፡ወደ፡ኦርና፡በመጣ፡ጊዜ፡ኦርና፡ተመልክቶ፡ዳዊትን፡አየ፤ከዐውድማውም፡ወጥቶ፡ዳዊትን፡ እጅ፡ሊነሣ፡በምድር፡ላይ፡ተደፋ።

22ዳዊትም፡ኦርናን፦በላዩ፡ለእግዚአብሔር፡መሠዊያ፡እሠራ፡ዘንድ፡ይህን፡የዐውድማ፡ስፍራ፡ ስጠኝ፤በሙሉ፡ዋጋ፡ስጠኝ፤መቅሠፍቱን፡ከሕዝቡ፡ይከለከላል፡አለው።

23ኦርናም፡ዳዊትን፦ለአንተ፡ውሰደው፥ጌታዬ፡ንጉሡም፡ደስ፡የሚያሠኘውን፡ ያድርግ፤እንሆ፥ለሚቃጠለው፡መሥዋዕት፡በሬዎቹን፥ለዕንጨትም፡የዐውድማውን፡ዕቃ፥ከእኽልም፡ቍርባን፡ ስንዴውን፡እሰጥኻለኹ፤ዅሉን፡እሰጣለኹ፡አለው።

24ንጉሡም፡ዳዊት፡ኦርናን፦አይደለም፥ነገር፡ግን፥ለአንተ፡ያለውን፡ለእግዚአብሔር፡አምጥቼ፡የሚቃጠል፡ መሥዋዕት፡በከንቱ፡አላቀርብምና፡በሙሉ፡ዋጋ፡እገዛዋለኹ፡አለው።

25ዳዊትም፡ስለ፡ስፍራው፡ስድስት፡መቶ፡ሰቅል፡ወርቅ፡በሚዛን፡ለኦርና፡ሰጠው።

26ዳዊትም፡በዚያ፡ለእግዚአብሔር፡መሠዊያ፡ሠራ፥የሚቃጠለውን፡መሥዋዕትና፡የደኅንነቱን፡መሥዋዕት፡ አቀረበ፥እግዚአብሔርንም፡ጠራ፤ከሰማይም፡ለሚቃጠለው፡መሥዋዕት፡በሚኾነው፡መሠዊያ፡ላይ፡በእሳት፡ መለሰለት።

27እግዚአብሔርም፡መልአኩን፡አዘዘው፥ሰይፉንም፡በአፎቱ፡ከተተው።

28በዚያን፡ጊዜ፡እግዚአብሔር፡በኢያቡሳዊው፡በኦርና፡ዐውድማ፡እንደ፡መለሰለት፡ዳዊት፡ባየ፡ጊዜ፥በዚያ፡ መሥዋዕት፡ሠዋ።

29ሙሴም፡በምድረ፡በዳ፡የሠራት፡የእግዚአብሔር፡ማደሪያና፡ለሚቃጠል፡መሥዋዕት፡የሚኾነው፡መሠዊያ፡ በዚያን፡ጊዜ፡በገባዖን፡ባለው፡በኰረብታው፡መስገጃ፡ነበሩ።

30ዳዊት፡ግን፡የእግዚአብሔርን፡መልአክ፡ሰይፍ፡ስለ፡ፈራ፡እግዚአብሔርን፡ለመጠየቅ፡ወደዚያ፡ይኼድ፡ ዘንድ፡አልቻለም። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source