Skip to content
← 1 Chronicles

Chapter 22 · Amharic

1 Chronicles

1ዳዊትም፦ይህ፡የእግዚአብሔር፡ቤት፡ነው፥ይህም፡ለእስራኤል፡ለሚቃጠል፡መሥዋዕት፡የሚኾነው፡ መሠዊያ፡ነው፡አለ።

2ዳዊትም፡በእስራኤል፡ምድር፡የነበሩትን፡መጻተኛዎች፡ይሰበስቡ፡ዘንድ፡አዘዘ፤የእግዚአብሔርንም፡ቤት፡ ለመሥራት፡የሚወቀሩትን፡ድንጋዮች፡ይወቅሩ፡ዘንድ፡ጠራቢዎችን፡አኖረ።

3ዳዊትም፡ለበሮቹ፡ሳንቃ፡ለሚኾኑ፡ለምስማርና፡ለመጠረቂያ፡ብዙ፡ብረት፥ከብዛቱም፡የተነሣ፡የማይመዘን፡ ናስ፡አዘጋጀ።

4ሲዶናውያንና፡የጢሮስ፡ሰዎች፡ብዙ፡የዝግባ፡ዕንጨት፡ወደ፡ዳዊት፡ያመጡ፡ነበርና፥ቍጥር፡የሌላቸውን፡ የዝግባ፡ዕንጨቶች፡አዘጋጀ።

5ዳዊትም፦ልጄ፡ሰሎሞን፡ታናሽና፡ለጋ፡ብላቴና፡ነው፥ለእግዚአብሔርም፡የሚሠራው፡ቤት፡እጅግ፡ ማለፊያና፡በአገሩ፡ዅሉ፡ስሙና፡ክብሩ፡እንዲጠራ፡ይኾን፡ዘንድ፡ይገ፟ባ፟ል፤ስለዚህ፥አዘጋጅለታለኹ፡ አለ።ዳዊትም፡ሳይሞት፡አስቀድሞ፡ብዙ፡አዘጋጀ።

6ልጁንም፡ሰሎሞንን፡ጠርቶ፡ለእስራኤል፡አምላክ፡ለእግዚአብሔር፡ስም፡ቤት፡ይሠራ፡ዘንድ፡አዘዘው።

7ዳዊትም፡ሰሎሞንን፡እንዲህ፡አለ፦ልጄ፡ሆይ፥እኔ፡ለአምላኬ፡ለእግዚአብሔር፡ቤት፡እሠራ፡ዘንድ፡ በልቤ፡ዐስቤ፡ነበር።

8ነገር፡ግን፥የእግዚአብሔር፡ቃል፡እንዲህ፡ሲል፡ወደ፡እኔ፡መጣ፦እጅግ፡ደም፡አፍሰ፟ኻል፥ታላቅም፡ ሰልፍ፡አድርገኻል፤በፊቴ፡በምድር፡ላይ፡ብዙ፡ደም፡አፍሰ፟ኻልና፥ለስሜ፡ቤት፡አትሠራም።

9እንሆ፥የዕረፍት፡ሰው፡የሚኾን፡ልጅ፡ይወለድልኻል፤በዙሪያው፡ካሉ፡ከጠላቶቹ፡ዅሉ፡ አሳርፈዋለኹ፤ስሙ፡ሰሎሞን፡ይባላልና፥በዘመኑም፡ሰላምንና፡ጸጥታን፡ለእስራኤል፡እሰጣለኹ።

10ርሱ፡ለስሜ፡ቤት፡ይሠራል፥ልጅም፡ይኾነኛል፥እኔም፡አባት፡እኾነዋለኹ፤የመንግሥቱንም፡ዙፋን፡ በእስራኤል፡ላይ፡ለዘለዓለም፡አጸናለኹ።

11አኹንም፥ልጄ፡ሆይ፥እግዚአብሔር፡ከአንተ፡ጋራ፡ይኹን፤ስለ፡አንተም፡እንደተናገረው፡ ያከናውንልኽ፥የአምላክኽንም፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡ሥራ።

12ብቻ፡የአምላክኽን፡የእግዚአብሔርን፡ሕግ፡ትጠብቅ፡ዘንድ፡እግዚአብሔር፡ጥበብንና፡ማስተዋልን፡ ይስጥኽ፥በእስራኤልም፡ላይ፡ያሠልጥንኽ።

13እግዚአብሔር፡ስለ፡እስራኤል፡ሙሴን፡ያዘዘውን፡ሥርዐትና፡ፍርድ፡ታደርግ፡ዘንድ፡ብትጠነቀቅ፡በዚያን፡ ጊዜ፡ይከናወንልኻል፤አይዞኽ፥በርታ፤አትፍራ፥አትደንግጥም።

14አኹንም፥እንሆ፥በድኽነቴ፡ለእግዚአብሔር፡ቤት፡መቶ፡ሺሕ፡መክሊት፡ወርቅና፡አንድ፡ሚልዮን፡ መክሊት፡ብር፥ሚዛንም፡የሌላቸው፡ብዙ፡ናስና፡ብረት፡አዘጋጀኹ፤ደግሞም፡ዕንጨትና፡ድንጋዮች፡ አዘጋጀኹ፥አንተም፡ከዚያ፡በላይ፡ጨምር።

15ባንተም፡ዘንድ፡ብዙ፡ሠራተኛዎች፥ድንጋይና፡ዕንጨት፡ወቃሪዎችና፡ጠራቢዎች፥ሥራውንም፡ዅሉ፡ ለማድረግ፡ጠቢባን፡ሰዎች፡ዅሉ፡አሉ።

16የሚሠሩበት፡ወርቅና፡ብር፡ናስና፡ብረት፡ቍጥር፡የለውም፤ተነሥተኽ፡ሥራ፥እግዚአብሔርም፡ከአንተ፡ ጋራ፡ይኹን።

17ዳዊትም፡ደግሞ፡ልጁን፡ሰሎሞንን፡ያግዙ፡ዘንድ፡የእስራኤልን፡አለቃዎች፡ዅሉ፡እንዲህ፡ሲል፡አዘዛቸው።

18አምላካችኹ፡እግዚአብሔር፡ከእናንተ፡ጋራ፡አይደለምን፧በምድርም፡የሚቀመጡትን፡በእጄ፡አሳልፎ፡ ሰጥቷልና፥ምድርም፡በእግዚአብሔርና፡በሕዝቡ፡ፊት፡ተገዝታለችና፥በዙሪያችኹ፡ዅሉ፡ዕረፍትን፡ሰጥቷችዃል።

19አኹንም፡አምላካችኹን፡እግዚአብሔርን፡ትፈልጉ፡ዘንድ፡ልባችኹንና፡ነፍሳችኹን፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ስጡ፤ለእግዚአብሔርም፡ስም፡ወደሚሠራው፡ቤት፡የእግዚአብሔርን፡የቃል፡ኪዳኑን፡ታቦትና፡የእግዚአብሔርን፡ ንዋየ፡ቅድሳት፡ታመጡ፡ዘንድ፡ተነሥታችኹ፡የአምላክን፡የእግዚአብሔርን፡መቅደስ፡ሥሩ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source