Skip to content
← 1 Kings

Chapter 4 · Amharic

1 Kings

1ንጉሡም፡ሰሎሞን፡በእስራኤል፡ዅሉ፡ላይ፡ነግሦ፡ነበር።

2የነበሩትም፡አለቃዎች፡እነዚህ፡ናቸው፤የሳዶቅ፡ልጅ፡ካህኑ፡ዐዛርያስ ፥

3ጸሓፊዎቹም፡የሴባ፡ልጆች፡ኤልያፍና፡አኪያ፥ታሪክ፡ጸሓፊም፡የአኂሉድ፡ልጅ፡ኢዮሳፍጥ፥

4የዮዳዔም፡ልጅ፡በናያስ፡የሰራዊት፡አለቃ፡ነበረ፤ሳዶቅና፡አብያታርም፡ካህናት፡ነበሩ፤

5የናታንም፡ልጅ፡ዐዛርያስ፡የሹሞች፡አለቃ፡ነበረ፤የናታንም፡ልጅ፡ዛቡድ፡የንጉሡ፡አማካሪና፡ወዳጅ፡ ነበረ፤

6አኂሳርም፡የቤት፡አዛዥ፥የዓብዳም፡ልጅ፡አዶኒራም፡አስገባሪ፡ነበረ።

7ለንጉሡና፡ለቤተ፡ሰቡም፡ቀለብ፡የሚሰጡ፡በእስራኤል፡ዅሉ፡ላይ፡ዐሥራ፡ኹለት፡ሹሞች፡ለሰሎሞን፡ ነበሩት።ከዓመቱ፡ውስጥ፡አንዱን፡ወር፡እያንዳንዳቸው፡ይቀልቡ፡ነበር።

8ስማቸውም፡ይህ፡ነበረ፤በተራራማው፡አገር፡በኤፍሬም፡የሑር፡ልጅ፤

9በማቃጽና፡በሸዓልቢም፡በቤትሳሚስና፡በኤሎንቤትሐናን፡የዴቀር፡ልጅ፤ 158 ዕብ.፥ዐዛርያ። http://www.gzamargna.net

10በአሩቦት፡የሔሴድ፡ልጅ፥ለርሱም፡ሰኰትና፡የኦፌር፡አገር፡ዅሉ፡ነበረ፤

11በዶር፡አገር፡ዳርቻ፡ዅሉ፡የዐሚናዳብ፡ልጅ፥ርሱም፡የሰሎሞንን፡ልጅ፡ጣፈትን፡አግብቶ፡ነበር፤

12ከቤትሳን፡ዠምሮ፡እስከ፡አቤልምሖላና፡እስከዮቅምዓም፡ማዶ፡ድረስ፡በታዕናክና፡በመጊዶ፡በጸርታንም፡ አጠገብ፡በኢይዝራኤል፡በታች፡ባለው፡በቤትሳን፡ዅሉ፡የአኂሉድ፡ልጅ፡በዓና፡ነበረ፤

13በሬማት፡ዘገለዓድ፡የጌበር፡ልጅ፡ነበረ፥ለርሱም፡በገለዓድ፡ያሉት፡የምናሴ፡ልጅ፡የኢያዕር፡መንደሮች፡ ነበሩ፤ለርሱም፡ደግሞ፡በባሳን፡በአርጎብ፡ዳርቻ፡ያሉት፡ቅጥርና፡የናስ፡መወርወሪያዎች፡የነበረባቸው፡ስድሳ፡ ታላላቅ፡ከተማዎች፡ነበሩበት፤

14በመሃናይም፡የዒዶ፡ልጅ፡አኂናዳብ፤

15በንፍታሌም፡አኪማዐስ፡ነበረ፥ርሱም፡የሰሎሞንን፡ልጅ፡ባስማትን፡አግብቶ፡ነበር፤

16በአሴር ና፡በበዓሎት፡የኩሲ፡ልጅ፡በዓና፤

17በይሳኮር፡የፋሩዋ፡ልጅ፡ኢዮሳፍጥ፤

18በብንያም፡የኤላ፡ልጅ፡ሳሚ፤

19በአሞራውያን፡ንጉሥ፡በሴዎንና፡በባሳን፡ንጉሥ፡በዐግ፡አገር፥በገለዓድ፡አገር፥የኡሪ፡ልጅ፡ጌበር፡ ነበረ፤በዚያችም፡ምድር፡ላይ፡ርሱ፡ብቻውን፡ሹም፡ነበረ።

20ይሁዳና፡እስራኤልም፡እንደ፡ባሕር፡አሸዋ፡ብዛት፡ብዙ፡ነበሩ፤በልተውም፡ጠጥተውም፡ደስ፡ብሏቸው፡ ነበር።

21ሰሎሞንም፡ከወንዙ፡ዠምሮ፡እስከግብጽ፡ዳርቻ፡እስከ፡ፍልስጥኤም፡ድረስ፡በመንግሥታት፡ዅሉ፡ላይ፡ ነግሦ፡ነበር፤ግብርም፡ያመጡለት፡ነበር፥በዕድሜውም፡ሙሉ፡ለሰሎሞን፡ይገዙ፡ነበር።

22ለሰሎሞንም፡ለቀን፡ለቀኑ፡ቀለብ፡የሚኾን፡ሠላሳ፡ኰር፡መልካም፡ዱቄትና፡ስድሳ፡ኰር፡መናኛ፡ድቄት፥

23ከዋላና፡ከሚዳቋ፡ከበረሓ፡ፍየልና፡ከሰቡ፡ወፎች፡በቀር፡ዐሥር፡ፍሪዳዎች፡ኻያም፡የተሰማሩ፡በሬዎች፡ አንድ፡መቶም፡በጎች፡ነበረ።

24ከወንዙ፡ወዲህ፡ባሉት፡ነገሥታት፡ዅሉ፡ከወንዙም፡ወዲህ፡ባለው፡አገር፡ዅሉ፡ላይ፡ከቲፍሳ፡ዠምሮ፡ እስከ፡ጋዛ፡ድረስ፡ነግሦ፡ነበር፤በዙሪያውም፡ባለው፡በዅሉ፡ወገን፡ሰላም፡ኾኖለት፡ነበር።

25በሰሎሞንም፡ዘመን፡ዅሉ፡ይሁዳና፡እስራኤል፡ከዳን፡ዠምሮ፡እስከ፡ቤርሳቤሕ፡ድረስ፡እያንዳንዱ፡ ከወይኑና፡ከበለሱ፡በታች፡ተዘልሎ፡ይቀመጥ፡ነበር።

26ለሰሎሞንም፡በአርባ፡ሺሕ፡ጋጥ፡የሚገቡ፡የሠረገላ፡ፈረሶች፡ዐሥራ፡ኹለትም፡ሺሕ፡ፈረሰኛዎች፡ ነበሩት።

27እነዚያም፡ሹሞች፡እያንዳንዱ፡በየወሩ፡ንጉሡን፡ሰሎሞንንና፡ወደንጉሡ፡ወደሰሎሞን፡ማእድ፡ የሚቀርቡትን፡ዅሉ፡ይቀልቡ፡ነበር፤ምንም፡አያጐድሉም፡ነበር።

28እያንዳንዱም፡እንደ፡ደንቡ፡ለፈረሶቹና፡ለሰጋር፡በቅሎዎች፡ገብስና፡ጭድ፡ወደ፡ስፍራቸው፡ያመጡ፡ ነበር።

29እግዚአብሔርም፡ለሰሎሞን፡እጅግ፡ብዙ፡ጥበብና፡ማስተዋል፡በባሕርም፡ዳር፡እንዳለ፡አሸዋ፡የልብ፡ ስፋት፡ሰጠው።

30የሰሎሞንም፡ጥበብ፡በምሥራቅ፡ካሉ፡ሰዎች፡ዅሉ፡ጥበብና፡ከግብጽ፡ጥበብ፡ዅሉ፡በለጠ። 159 ዕብ.፥አሼር። http://www.gzamargna.net

31ከሰውም፡ዅሉ፡ይልቅ፡ከኢይዝራኤላዊው፡ከኤታንና፡ከማሖል ፡ልጆች፣ከሄማን ና፡ከከልቀድ፣ከደራልም፡ ይልቅ፡ጥበበኛ፡ነበረ።በዙሪያውም፡ባሉ፡አሕዛብ፡ዅሉ፡ዝናው፡ወጣ።

32ርሱም፡ሦስት፡ሺሕ፡ምሳሌዎች፡ተናገረ፤መሐልዩም፡ሺሕ፡ዐምስት፡ነበረ።

33ስለ፡ዛፍም፡ከሊባኖስ፡ዝግባ፡ዠምሮ፡በቅጥር፡ግንብ፡ላይ፡እስከሚበቅለው፡እስከ፡ሂሶጵ፡ድረስ፡ይናገር፡ ነበር፤ደግሞም፡ስለ፡አውሬዎችና፡ስለ፡ወፎች፡ስለ፡ተንቀሳቃሾችና፡ስለ፡ዓሣዎች፡ይናገር፡ነበር።

34ከአሕዛብም፡ዅሉ፥ጥበቡንም፡ሰምተው፡ከነበሩ፡ከምድር፡ነገሥታት፡ዅሉ፡የሰሎሞንን፡ጥበብ፡ለመስማት፡ ሰዎች፡ይመጡ፡ነበር።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source