Skip to content
← 1 Kings

Chapter 5 · Amharic

1 Kings

1የጢሮስ፡ንጉሥ፡ኪራም፡ለዳዊት፡በዘመኑ፡ዅሉ፡ወዳጅ፡ስለ፡ነበረ፥ሰሎሞን፡በአባቱ፡ፋንታ፡ንጉሥ፡ ለመኾን፡እንደ፡ተቀባ፡ሰምቶ፡ባሪያዎቹን፡ወደ፡ሰሎሞን፡ሰደደ።

2ሰሎሞንም፡ወደ፡ኪራም፡እንዲህ፡ብሎ፡ላከ።

3እግዚአብሔር፡ከእግሩ፡በታች፡እስኪጥልለት፡ድረስ፡በዙሪያው፡ስለ፡ነበረ፡ሰልፍ፡አባቴ፡ዳዊት፡ የአምላኩን፡የእግዚአብሔርን፡ቤት፡መሥራት፡እንዳልቻለ፡አንተ፡ታውቃለኽ።

4አኹንም፡አምላኬ፡እግዚአብሔር፡በዙሪያዬ፡ካሉት፡ዕረፍት፡ሰጥቶኛል፤ጠላትም፡ክፉም፡ነገር፡የለብኝም።

5እንሆም፥እግዚአብሔር፡ለአባቴ፡ለዳዊት፦ባንተ፡ፋንታ፡በዙፋንኽ፡ላይ፡የማስቀምጠው፡ልጅኽ፡ርሱ፡ ለስሜ፡ቤት፡ይሠራል፡ብሎ፡እንደ፡ነገረው፥ለአምላኬ፡ለእግዚአብሔር፡ስም፡ቤት፡እሠራ፡ዘንድ፡ዐስባለኹ።

6አኹንም፡ከወገኔ፡እንደ፡ሲዶናውያን፡ዕንጨት፡መቈረጥ፡የሚያውቅ፡እንደሌለ፡ታውቃለኽና፡የዝግባ፡ዛፍ፡ ከሊባኖስ፡ይቈርጡልኝ፡ዘንድ፡ባሪያዎችኽን፡እዘዝ፤ባሪያዎቼም፡ከባሪያዎችኽ፡ጋራ፡ይኹኑ፤የባሪያዎችኽንም፡ ዋጋ፡እንደተናገርኸው፡ዅሉ፡እሰጥኻለኹ።

7ኪራምም፡የሰሎሞንን፡ቃል፡ሰምቶ፡እጅግ፡ደስ፡አለውና፦በዚህ፡በታላቅ፡ሕዝብ፡ላይ፡ጥበበኛ፡ልጅ፡ ለዳዊት፡የሰጠ፡እግዚአብሔር፡ዛሬ፡ይመስገን፡አለ።

8ኪራምም፦የላክኽብኝን፡ዅሉ፡ሰማኹ፤ስለ፡ዝግባውና፡ስለ፡ጥዱ፡ዕንጨት፡ፈቃድኽን፡ዅሉ፡ አደርጋለኹ።

9ባሪያዎቼ፡ከሊባኖስ፡ወደ፡ባሕር፡ይጐትቱታል፤እኔም፡በታንኳ፡አድርጌ፡በባሕር፡ላይ፡እያንሳፈፍኹ፡አንተ፡ እስከወሰንኸው፡ስፍራ፡ድረስ፡አደርስልኻለኹ፥በዚያም፡እፈታዋለኹ፥አንተም፡ከዚያ፡ታስወስደዋለኽ፤አንተም፡ ፈቃዴን፡ታደርጋለኽ፤ለቤቴም፡ቀለብ፡የሚኾነውን፡ትሰጠኛለኽ፡ብሎ፡ወደ፡ሰሎሞን፡ላከ።

10እንዲሁም፡ኪራም፡የዝግባውንና፡የጥዱን፡ዕንጨት፡እንደሚሻው፡ያኽል፡ዅሉ፡ለሰሎሞን፡ይሰጠው፡ነበር።

11ሰሎሞንም፡ለኪራም፡ስለ፡ቤቱ፡ቀለብ፡ኻያ፡ሺ፡የቆሮስ፡መስፈሪያ፡ስንዴ፡ኻያ፡ኰርም፡ጥሩ፡ዘይት፡ ይሰጠው፡ነበር፤ሰሎሞንም፡ለኪራም፡በየዓመቱ፡ይህን፡ይሰጥ፡ነበር።

12እግዚአብሔርም፡እንደ፡ነገረው፡ለሰሎሞን፡ጥበብን፡ሰጠው፤በኪራምና፡በሰሎሞንም፡መካከል፡ሰላም፡ ነበረ፤ኹለቱም፡ቃል፡ኪዳን፡ተጋቡ።

13ሰሎሞንም፡ከእስራኤል፡ዅሉ፡ገባሮቹን፡መርጦ፡አወጣ፤የገባሮቹም፡ቍጥር፡ሠላሳ፡ሺሕ፡ሰዎች፡ነበረ።

14በየወሩም፡እያከታተለ፡ወደ፡ሊባኖስ፡ዐሥር፡ዐሥር፡ሺሕ፡ይሰድ፟፡ነበር፤አንድ፡ወርም፡በሊባኖስ፡ኹለት፡ ወርም፡በቤታቸው፡ይቀመጡ፡ነበር።አዶኒራምም፡አስገባሪ፡ነበረ።

15ሰሎሞንም፡ሰባ፡ሺሕ፡ተሸካሚዎች፥ሰማንያ፡ሺሕም፡በተራራው፡ላይ፡የሚጠርቡ፡ጠራቢዎች፡ነበሩት። 160 ዕብ.፡ማሖል፡(ማሕሌት•በቁሙ)። 161 ዕብ.፥ሄይማን፡(ሀይማኒ•አማኝ)። http://www.gzamargna.net

16ይኸውም፡በሠራተኛው፡ሕዝብ፡ላይ፡ከተሾሙት፡ከሦስት፡ሺሕ፡ስድስት፡መቶ፡ሰዎች፡ሌላ፡ነው።

17ንጉሡም፡ታላላቅ፡ምርጥ፡ምርጥ፡ድንጋዮችን፡ይቈፍሩና፡ይጠርቡ፡ዘንድ፡ለቤቱም፡መሠረት፡ይረበርቡት፡ ዘንድ፡አዘዘ።

18የሰሎሞንና፡የኪራምም፡ዐናጢዎች፡ጌባላውያንም፡ወቀሯቸው፥ቤቱንም፡ለመሥራት፡ዕንጨቱንና፡ ድንጋዮቹን፡አዘጋጁ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source