Skip to content
← 1 Samuel

Chapter 10 · Amharic

1 Samuel

1ሳሙኤልም፡የዘይቱን፡ብርሌ፡ወስዶ፡በራሱ፡ላይ፡አፈሰሰው፥ሳመውም፥እንዲህም፡አለው፦በርስቱ፡ላይ፡ አለቃ፡ትኾን፡ዘንድ፡እግዚአብሔር፡ቀብቶኻል፤የእግዚአብሔርንም፡ሕዝብ፡ትገዛለኽ፥በዙሪያውም፡ካሉ፡ ጠላቶቻቸው፡እጅ፡ታድናቸዋለኽ።

2ዛሬ፡ከእኔ፡በተለየኽ፡ጊዜ፡በብንያም፡ዳርቻ፡በጼልጻህ፡አገር፡ባለው፡በራሔል፡መቃብር፡አጠገብ፡ ኹለት፡ሰዎች፡ታገኛለኽ፤እነርሱም፦ልትሻቸው፡ኼደኽ፡የነበርኽላቸው፡አህያዎች፡ ተገኝተዋል፤እንሆም፥አባትኽ፡ስለ፡አህያዎች፡ማሰብ፡ትቶ፦የልጄን፡ነገር፡እንዴት፡አደርጋለኹ፧እያለ፡ ስለ፡እናንተ፡ይጨነቃል፡ይሉኻል።

3ከዚያም፡ደግሞ፡ወደ፡ፊት፡ትኼዳለኽ፤ወደ፡ታቦር፡ወደ፡ትልቁ፡ዛፍ፡ትደርሳለኽ፤በዚያም፡ሦስት፡ ሰዎች፥አንዱ፡ሦስት፡ሰዎች፥አንዱ፡ሦስት፡የፍየል፡ጠቦቶች፥ኹለተኛው፡ሦስት፡ዳቦ፥ሦስተኛውም፡የወይን፡ ጠጅ፡አቍማዳ፡ይዘው፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ወደ፡ቤቴል፡ሲወጡ፡ያገኙኻል፤

4ሰላምታም፡ይሰጡኻል፥ኹለትም፡ዳቦ፡ይሰጡኻል፥ከእጃቸውም፡ትቀበላለኽ።

5ከዚያም፡በዃላ፡የፍልስጥኤማውያን፡ጭፍራ፡ወዳለበት፡ወደእግዚአብሔር፡ኰረብታ፡ትመጣለኽ፤ወደዚያም፡ ወደ፡ከተማዪቱ፡በደረስኽ፡ጊዜ፥በገናና፡ከበሮ፡እንቢልታና፡መሰንቆ፡ይዘው፡ትንቢት፡እየተናገሩ፡ ከኰረብታው፡መስገጃ፡የሚወርዱ፡የነቢያት፡ጉባኤ፡ያገኙኻል።

6የእግዚአብሔርም፡መንፈስ፡በኀይል፡ይወርድብኻል፥ከነርሱም፡ጋራ፡ትንቢት፡ትናገራለኽ፥እንደ፡ሌላ፡ ሰውም፡ኾነኽ፡ትለወጣለኽ።

7እነዚህም፡ምልክቶች፡በደረሱኽ፡ጊዜ፡እግዚአብሔር፡ከአንተ፡ጋራ፡ነውና፥እጅኽ፡የምታገኘውን፡ዅሉ፡ አድርግ።

8በፊቴም፡ወደ፡ገልገላ፡ትወርዳለኽ፤እኔም፥እንሆ፥የሚቃጠለውን፡መሥዋዕት፡አቀርብ፡ ዘንድ፥የደኅንነትም፡መሥዋዕት፡እሠዋ፡ዘንድ፡ወዳንተ፡እወርዳለኹ፤እኔ፡ወዳንተ፡እስክመጣና፡ የምታደርገውን፡እስክነግርኽ፡ድረስ፡ሰባት፡ቀን፡ትቈያለኽ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

9ከሳሙኤልም፡ዘንድ፡ለመኼድ፡ፊቱን፡በመለሰ፡ጊዜ፡እግዚአብሔር፡ሌላ፡ልብ፡ለወጠለት፤በዚያም፡ቀን፡ እነዚህ፡ምልክቶች፡ዅሉ፡ደረሱለት።

10ወደዚያም፡ኰረብታ፡በደረሰ፡ጊዜ፥እንሆ፥የነቢያት፡ጉባኤ፡አገኙት፤የእግዚአብሔርም፡መንፈስ፡በኀይል፡ ወረደበት፥በመካከላቸውም፡ትንቢት፡ተናገረ።

11ቀድሞም፡የሚያውቁት፡ዅሉ፡ከነቢያት፡ጋራ፡ትንቢት፡ሲናገር፡ባዩት፡ጊዜ፡ሕዝቡ፡ርስ፡ በርሳቸው።የቂስን፡ልጅ፡ያገኘው፡ምንድር፡ነው፧በእውኑ፡ሳኦል፡ከነቢያት፡ወገን፡ነውን፧ተባባሉ።

12ከዚያም፡ስፍራ፡ያለ፡አንድ፡ሰው፦አባታቸውስ፡ማን፡ነው፧ብሎ፡መለሰ።ስለዚህም፦ሳኦል፡ደግሞ፡ ከነቢያት፡ወገን፡ነውን፧የሚል፡ምሳሌ፡ኾነ።

13ትንቢት፡መናገሩንም፡በፈጸመ፡ጊዜ፡ወደኰረብታው፡መስገጃ፡መጣ።

14አጎቱም፡ሳኦልንና፡ብላቴናውን፥ወዴት፡ኼዳችኹ፡ኖሯል፧አላቸው።ርሱም፦አህያዎችን፡ልንሻ፡ኼደን፡ ነበር፤ባጣናቸውም፡ጊዜ፡ወደ፡ሳሙኤል፡መጣን፡አለ።

15የሳኦልም፡አጎት፦ሳሙኤል፡የነገረኽን፥እባክኽ፥ንገረኝ፡አለው።

16ሳኦልም፡አጎቱን፦አህያዎች፡እንደ፡ተገኙ፡ገለጠልን፡አለው፤ነገር፡ግን፥ሳሙኤል፡የነገረውን፡ የመንግሥትን፡ነገር፡አላወራለትም።

17ሳሙኤልም፡ሕዝቡን፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ወደ፡ምጽጳ፡ጠራ።

18የእስራኤልንም፡ልጆች፦የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እስራኤልን፡ከግብጽ፡ አወጣኹ፥ከግብጻውያንም፡እጅ፡ከሚያስጨንቋችኹም፡ነገሥታት፡ዅሉ፡እጅ፡አዳንዃችኹ።

19ዛሬ፡ግን፡ከመከራችኹና፡ከጭንቃችኹ፡ዅሉ፡ያዳናችኹን፡አምላካችኹን፡ንቃችኹ።እንዲህ፡ አይኹን፥ነገር፡ግን፥ንጉሥ፡አታንግሥልን፡አላችኹት።አኹንም፡በየነገዳችኹና፡በየወገናችኹ፡ወደ፡ እግዚአብሔር፡ፊት፡ቅረቡ፡አላቸው።

20ሳሙኤልም፡የእስራኤልን፡ነገዶች፡ዅሉ፡አቀረበ፥ዕጣውም፡በብንያም፡ነገድ፡ላይ፡ወደቀ።

21የብንያምንም፡ነገድ፡በየወገናቸው፡አቀረበ፥ዕጣውም፡በማጥሪ፡ወገን፡ላይ፡ወደቀ።የማጥሪንም፡ወገን፡ በየሰዉ፡አቀረበ፥ዕጣውም፡በቂስ፡ልጅ፡በሳኦል፡ላይ፡ወደቀ፤ፈለጉትም፥አላገኙትምም።

22ከእግዚአብሔርም፦ገና፡ወደዚህ፡የሚመጣ፡ሰው፡አለን፧ብለው፡ደግሞ፡ ጠየቁት፤እግዚአብሔርም፦እንሆ፥በዕቃ፡መካከል፡ተሸሽጓል፡ብሎ፡መለሰ።

23እነርሱም፡ሮጠው፡ከዚያ፡አመጡት፤ርሱም፡በሕዝቡ፡መካከል፡ቆመ፥ከሕዝቡም፡ዅሉ፡ይልቅ፡ ከትከሻው፡ወደ፡ላይ፡ከፍ፡ያለ፡ቁመተ፡ረዥም፡ነበረ።

24ሳሙኤልም፡ለሕዝቡ፡ዅሉ፦ከሕዝቡ፡ዅሉ፡ርሱን፡የሚመስል፡እንደሌለ፡እግዚአብሔር፡የመረጠውን፡ ታያላችኹን፧አላቸው፤ሕዝቡም፡ዅሉ፦ንጉሥ፡ሕያው፡ይኹን፡እያሉ፡እልልታ፡አደረጉ።

25ሳሙኤልም፡የመንግሥቱን፡ወግ፡ነገረ፥በመጽሐፍም፡ጻፈው፡በእግዚአብሔርም፡ፊት፡ አኖረው።ሳሙኤልም፡ሕዝቡን፡ዅሉ፡ወደ፡እየቤታቸው፡አሰናበታቸው።

26ሳኦልም፡ወደ፡ቤቱ፡ወደ፡ጊብዓ፡ኼደ፤እግዚአብሔር፡ልባቸውን፡የነካ፡ኀያላንም፡ከርሱ፡ጋራ፡ኼዱ።

27ምናምንቴዎች፡ሰዎች፡ግን፦ይህ፡ሰው፡እንዴት፡ያድነናል፧ብለው፡ናቁት፥እጅ፡መንሻም፡ አላመጡለትም።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source