1ስሙ፡ቂስ፡የተባለ፡አንድ፡ብንያማዊ፡ሰው፡ነበረ፤ርሱም፡የአቢኤል፡ልጅ፥የጽሮር፡ልጅ፥የብኮራት፡ ልጅ፥የብንያማዊው፡የአፌቅ ፡ልጅ፥ጽኑዕ፡ኀያል፡ሰው፡ነበረ።
2ለርሱም፡ሳኦል፡የሚባል፡የተመረጠ፡መልካም፡ልጅ፡ነበረው፤ከእስራኤልም፡ልጆች፡ከርሱ፡ይልቅ፡ 136 ዕብ.፥አፍያሕ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org መልካም፡የኾነ፡ሰው፡አልነበረም፤ከሕዝቡም፡ዅሉ፡ይልቅ፡ከትከሻውና፡ከዚያም፡በላይ፡ቁመቱ፡ዘለግ፡ያለ፡ ነበረ።
3የሳኦልም፡አባት፡የቂስ፡አህያዎች፡ጠፍተው፡ነበር፤ቂስም፡ልጁን፡ሳኦልን፦ከብላቴናዎቹ፡አንዱን፡ ወስደኽ፡ተነሣ፥አህያዎችንም፡ለመሻት፡ኺድ፡አለው።
4በተራራማው፡በኤፍሬም፡አገርና፡በሻሊሻ፡ዐለፉ፥አላገኟቸውምም፡በሻዕሊም፡ምድርም፡ዐለፉ፥በዚያም፡ አልነበሩም፤በብንያም፡ምድርም፡ዐለፉ፥አላገኟቸውምም።
5ወደጹፍ፡ምድር፡በመጡ፡ጊዜም፡ሳኦል፡ከርሱ፡ጋራ፡የነበረውን፡ብላቴና፦አባቴ፡ስለ፡አህያዎች፡ማሰብ፡ ትቶ፡ስለ፡እኛ፡እንዳይጨነቅ፥ና፥እንመለስ፡አለው።
6ርሱም፦እንሆ፥አንድ፡የእግዚአብሔር፡ሰው፡በዚች፡ከተማ፡አለ፤ርሱም፡የተከበረ፡ሰው፡ ነው፥የሚናገረውም፡ዅሉ፡በእውነት፡ይፈጸማል፤አኹን፡ወደዚያ፡እንኺድ፤ምናልባት፡የምንኼድበትን፡ መንገድ፡ይነግረናል፡አለው።
7ሳኦልም፡ብላቴናውን፦እንሆ፥እንኼዳለን፤ነገር፡ግን፥ለእግዚአብሔር፡ሰው፡ምን፡ እናመጣለታለን፧እንጀራ፡ከከረጢታችን፡አልቋልና፥እጅ፡መንሻም፡የለንምና፡ለእግዚአብሔር፡ሰው፡ የምናመጣለት፡ምን፡አለን፧አለው።
8ብላቴናው፡ደግሞ፡ለሳኦል፡መልሶ፦እንሆ፥በእጄ፡የሰቅል፡ብር፡ሩቡ፡አለኝ፤ርሱንም፡መንገዳችንን፡ እንዲነግረን፡ለእግዚአብሔር፡ሰው፡እሰጣለኹ፡አለ።
9ዛሬ፡ነቢይ፡የሚባለው፡ቀድሞ፡ባለራእይ፡ይባል፡ነበርና፥አስቀድሞ፡በእስራኤል፡ዘንድ፡ሰው፡ እግዚአብሔርን፡ለመጠየቅ፡ሲኼድ፦ኑ፥ወደ፡ባለራእይ፡እንኺድ፡ይል፡ነበር።
10ሳኦልም፡ብላቴናውን፦የተናገረኸው፡ነገር፡መልካም፡ነው፤ና፥እንኺድ፡አለውና፡የእግዚአብሔር፡ሰው፡ ወዳለበት፡ከተማ፡ኼዱ።
11በከተማዪቱም፡ዳገት፡በወጡ፡ጊዜ፡ቈነዣዥት፡ውሃውን፡ሊቀዱ፡ሲወጡ፡አገኙና፦ባለራእይ፡በዚህ፡አለ፡ ወይ፧አሏቸው።
12እነርሱም፦አዎን፤እንሆ፥በፊታችኹ፡ነው፤ዛሬ፡ወደ፡ከተማዪቱ፡መጥቷልና፥ዛሬም፡ሕዝቡ፡ በኰረብታው፡ላይ፡ባለው፡መስገጃ፡መሥዋዕት፡ማቅረብ፡አለባቸውና፡ፈጥናችኹ፡ውጡ።
13ወደ፡ከተማዪቱም፡በገባችኹ፡ጊዜ፡መሥዋዕቱን፡ርሱ፡የሚባርክ፡ስለ፡ኾነ፡ርሱ፡ሳይወጣ፡ሕዝቡ፡ምንም፡ አይቀምሱምና፥ከዚያም፡በዃላ፡የተጠሩት፡ይበላሉና፡ለመብላት፡ወደኰረብታው፡መስገጃ፡ሳይወጣ፡ ታገኙታላችኹ፤በዚህም፡ጊዜ፡ታገኙታላችኹና፡አኹን፡ውጡ፡አሏቸው።
14ወደ፡ከተማዪቱም፡ወጡ፤በከተማዪቱም፡ውስጥ፡በገቡ፡ጊዜ፥እንሆ፥ሳሙኤል፡ወደኰረብታው፡መስገጃ፡ ለመውጣት፡ወደ፡እነርሱ፡መጣ።
15ገናም፡ሳኦል፡ሳይመጣ፡ካንድ፡ቀን፡በፊት፡እግዚአብሔር፡ሳሙኤልን፡እንዲህ፡ብሎ፡ገልጦለት፡ነበር።
16ነገ፡በዚች፡ሰዓት፡ከብንያም፡አገር፡አንድ፡ሰው፡እሰድ፟ልኻለኹ፤ልቅሷቸው፡ወደ፡እኔ፡የደረስ፡ሕዝቤን፡ ተመልክቻለኹና፡ለሕዝቤ፡ለእስራኤል፡አለቃ፡ይኾን፡ዘንድ፡ትቀባዋለኽ፥ከፍልስጥኤማውያንም፡እጅ፡ሕዝቤን፡ ያድናል።
17ሳሙኤልም፡ሳኦልን፡ባየ፡ጊዜ፡እግዚአብሔር፦ያ፡የነገርኹኽ፡ሰው፡እንሆ፤ርሱም፡በሕዝቤ፡ላይ፡ ይሠለጥናል፡አለው።
18ሳኦልም፡በበሩ፡ወደ፡ሳሙኤል፡ቀርቦ፦የባለራእዩ፡ቤት፡ወዴት፡እንደ፡ኾነ፥እባክኽ፥ንገረኝ፡አለው።
19ሳሙኤልም፡መልሶ፡ሳኦልን፦ባለራእዩ፡እኔ፡ነኝ፤ዛሬም፡ከእኔ፡ጋራ፡ትበላላችኹና፡በፊቴ፡ ወደኰረብታው፡መስገጃ፡ውጡ፤ነገም፡አሰናብትኻለኹ፥በልብኽም፡ያለውን፡ዅሉ፡እነግርኻለኹ፤ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
20ከሦስት፡ቀንም፡በፊት፡የጠፉ፡አህያዎችኽ፡ተገኝተዋልና፥ልብኽን፡አትጣልባቸው።የእስራኤል፡ምኞት፡ ለማን፡ነው፧ለአንተና፡ለአባትኽ፡ቤት፡አይደለምን፧አለው።
21ሳኦልም፡መልሶ፦እኔ፡ከእስራኤል፡ነገዶች፡ከሚያንስ፡ወገን፡የኾንኹ፡ብንያማዊ፡አይደለኹምን፧ወገኔስ፡ ከብንያም፡ነገድ፡ወገኖች፡ዅሉ፡የሚያንስ፡አይደለምን፧እንዲህስ፡ያለውን፡ነገር፡ለምን፡ነገርኸኝ፧አለው።
22ሳሙኤልም፡ሳኦልንና፡ብላቴናውን፡ወስዶ፡ወደ፡አዳራሽ፡አገባቸው፥በመርፈቂያውም፡ራስ፡ አስቀመጣቸው፤የተጠሩትም፡ሠላሳ፡ሰዎች፡ያኽል፡ነበሩ።
23ሳሙኤልም፡ወጥቤቱን፦ባንተ፡ዘንድ፡አኑረው፡ብዬ፡የሰጠኹኽን፡ዕድል፡ፈንታ፡አምጣ፡አለው።
24ወጥቤቱም፡ጭኑንና፡በርሱ፡ላይ፡የነበረውን፡አምጥቶ፡በሳኦል፡ፊት፡አኖረው።ሳሙኤልም፦ሕዝቡን፡ ከጠራኹ፡ዠምሮ፡እስከተወሰነው፡ጊዜ፡ድረስ፡ለአንተ፡ተጠብቋልና፥እንሆ፥የተቀመጠልኽን፡በፊትኽ፡አኑረኽ፡ ብላው፡አለ።በዚያም፡ቀን፡ሳኦል፡ከሳሙኤል፡ጋራ፡በላ።
25ከኰረብታውም፡መስገጃ፡ወደ፡ከተማዪቱ፡ወረዱ፤ሳሙኤልም፡ለሳኦል፡በሰገነቱ፡ላይ፡መኝታ፡ አዘጋጀለት፥ርሱም፡ተኛ።
26ማልዶም፡ተነሡ፤በነጋም፡ጊዜ፡ሳሙኤል፡ሳኦልን፡ከሰገነቱ፡ላይ፡ጠርቶ፦ተነሣና፡ላሰናብትኽ፡ አለው።ሳኦልም፡ተነሣ፥ርሱና፡ሳሙኤልም፡ኹለቱ፡ወደ፡ሜዳ፡ወጡ።
27እነርሱም፡በከተማዪቱ፡ዳር፡ሲወርዱ፡ሳሙኤል፡ሳኦልን፦ብላቴናውን፡ወደ፡ፊታችን፡እንዲያልፍ፡ እዘዘው፤አንተ፡ግን፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡አሰማኽ፡ዘንድ፡በዚህ፡ቁም፡አለው።ብላቴናውም፡ዐለፈ።