Skip to content
← 1 Samuel

Chapter 8 · Amharic

1 Samuel

1እንዲህም፡ኾነ፤ሳሙኤል፡በሸመገለ፡ጊዜ፡ልጆቹን፡በእስራኤል፡ላይ፡ፈራጆች፡አደረጋቸው።

2የበኵር፡ልጁም፡ስም፡ኢዮኤል፥የኹለተኛውም፡ስም፡አብያ ፡ነበረ።እነርሱም፡በቤርሳቤሕ፡ይፈርዱ፡ ነበር።

3ልጆቹም፡በመንገዱ፡አልኼዱም፥ነገር፡ግን፥ረብ፡ለማግኘት፡ፈቀቅ፡አሉ፥ጕቦም፡እየተቀበሉ፡ፍርድን፡ ያጣምሙ፡ነበር። 135 ዕብ.፥አቢያህ፡(አበ፡ያህ፥አምላክን፡የታመነ፡አባት)። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

4የእስራኤልም፡ሽማግሌዎች፡ዅሉ፡ተሰብስበው፡ወደ፡ሳሙኤል፡ወደ፡አርማቴም፡መጡና።

5እንሆ፥አንተ፡ሸምግለኻል፥ልጆችኽም፡በመንገድኽ፡አይኼዱም፤አኹንም፡እንደ፡አሕዛብ፡ዅሉ፡ የሚፈርድልን፡ንጉሥ፡አድርግልን፡አሉት።

6የሚፈርድልንም፡ንጉሥ፡ስጠን፡ባሉት፡ጊዜ፡ነገሩ፡ሳሙኤልን፡አስከፋው፤ሳሙኤልም፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ ጸለየ።

7እግዚአብሔርም፡ሳሙኤልን፡አለው፦በእነርሱ፡ላይ፡እንዳልነግሥ፡እኔን፡እንጂ፡አንተን፡አልናቁምና፡ በሚሉኽ፡ነገር፡ዅሉ፡የሕዝቡን፡ቃል፡ስማ።

8ከግብጽ፡ካወጣዃቸው፡ቀን፡ዠምሮ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡እኔን፡ትተው፡እንግዳዎች፡አማልክት፡ በማምለካቸው፡እንደ፡ሠሩት፡ሥራ፡ዅሉ፡እንዲሁ፡ባንተ፡ደግሞ፡ያደርጉብኻል።

9አኹንም፡ቃላቸውን፡ስማ፤ነገር፡ግን፥ጽኑ፡ምስክር፡መስክርባቸው፥በእነርሱም፡ላይ፡የሚነግሠውን፡ የንጉሡን፡ወግ፡ንገራቸው።

10ሳሙኤልም፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ዅሉ፡ንጉሥን፡ለፈለጉ፡ሕዝብ፡ነገራቸው።

11እንዲህም፡አለ፦በእናንተ፡ላይ፡የሚነግሠው፡የንጉሡ፡ወግ፡ይህ፡ነው፤ወንዶች፡ልጆቻችኹን፡ወስዶ፡ ሠረገለኛዎችና፡ፈረሰኛዎች፡ያደርጋቸዋል፥በሠረገላዎቹም፡ፊት፡ይሮጣሉ፤

12ለራሱም፡የሻለቃዎችና፡የመቶ፡አለቃዎች፡ያደርጋቸዋል፤ዕርሻውንም፡የሚያርሱ፡እኽሉንም፡የሚያጭዱ፡ የጦር፡መሣሪያውንና፡የሠረገላዎቹንም፡ዕቃ፡የሚሠሩ፡ይኾናሉ።

13ሴቶች፡ልጆቻችኹንም፡ወስዶ፡ሽቶ፡ቀማሚዎችና፡ወጥቤቶች፡ዐበዛዎችም፡ያደርጋቸዋል።

14ከዕርሻችኹና፡ከወይናችኹም፡መልካም፡መልካሙን፡ወስዶ፡ለሎሌዎቹ፡ይሰጣቸዋል።

15ከዘራችኹና፡ከወይናችኹም፡ዓሥራት፡ወስዶ፡ለጃን፡ደረባዎቹና፡ለሎሌዎቹ፡ይሰጣቸዋል።

16ሎሌዎቻችኹንና፡ገረዶቻችኹን፥ከከብቶቻችኹና፡ከአህያዎቻችኹም፡መልካም፡መልካሞቹን፡ወስዶ፡ ያሠራቸዋል።

17ከበጎቻችኹና፡ከፍየሎቻችኹ፡ዓሥራት፡ይወስዳል፤እናንተም፡ባሪያዎች፡ትኾኑታላችኹ።

18በዚያም፡ቀን፡ለእናንተ፡ከመረጣችኹት፡ከንጉሣችኹ፡የተነሣ፡ትጮኻላችኹ፤በዚያም፡ቀን፡እግዚአብሔር፡ አልሰማችኹም።

19ሕዝቡ፡ግን፡የሳሙኤልን፡ነገር፡ይሰማ፡ዘንድ፡እንቢ፡አለ።እንዲህ፡አይኹን፥ነገር፡ግን፥ንጉሥ፡ ይኹንልን፥

20እኛም፡ደግሞ፡እንደ፡አሕዛብ፡ዅሉ፡እንኾናለን፤ንጉሣችንም፡ይፈርድልናል፥በፊታችንም፡ወጥቶ፡ስለ፡ እኛ፡ይዋጋል፡አሉት።

21ሳሙኤልም፡የሕዝቡን፡ቃል፡ዅሉ፡ሰማ፥ለእግዚአብሔርም፡ተናገረ።

22እግዚአብሔርም፡ሳሙኤልን፦ቃላቸውን፡ስማ፥ንጉሥም፡አንግሥላቸው፡አለው።ሳሙኤልም፡ የእስራኤልን፡ሰዎች፦እያንዳንዳችኹ፡ወደ፡ከተማችኹ፡ኺዱ፡አላቸው።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source