1ሳኦልም፡በእስራኤል፡ላይ፡ኹለት፡ዓመት፡ከነገሠ፡በዃላ፥
2ሳኦል፡ሦስት፡ሺሕ፡ሰዎች፡ከእስራኤል፡መረጠ፤ኹለቱም፡ሺሕ፡በማክማስና፡በቤቴል፡ተራራ፡ከሳኦል፡ ጋራ፡ነበሩ፥አንዱም፡ሺሕ፡በብንያም፡ጊብዓ፡ከዮናታን፡ጋራ፡ነበሩ፤የቀረውንም፡ሕዝብ፡እያንዳንዱ፡ወደ፡ ድንኳኑ፡አሰናበተ።
3ዮናታንም፡በናሲብ፡ውስጥ፡የነበረውን፡የፍልስጥኤማውያንን፡ጭፍራ፡መታ፥ፍልስጥኤማውያንም፡ያን፡ ሰሙ፤ሳኦልም፦ዕብራውያን፡ይስሙ፡ብሎ፡በአገሩ፡ዅሉ፡ቀንደ፡መለከት፡ነፋ። እጅ፡፩ዱ፡እጅ፡ነበረ።
4እስራኤልም፡ዅሉ፡ሳኦል፡የፍልስጥኤማውያንን፡ጭፍራ፡እንደ፡መታ፥ደግሞም፡እስራኤል፡ በፍልስጥኤማውያን፡ዘንድ፡እንደ፡ተጸየፉ፡ሰሙ፤ሕዝቡም፡ሳኦልን፡ለመከተል፡ወደ፡ገልገላ፡ተሰበሰቡ።
5ፍልስጥኤማውያንም፡ከእስራኤል፡ጋራ፡ለመዋጋት፡ተሰበሰቡ፤ሠላሳ፡ሺሕ፡ሠረገላዎች፡ስድስትም፡ሺሕ፡ ፈረሰኛዎች፡በባሕርም፡ዳር፡እንዳለ፡አሸዋ፡ብዙ፡ሕዝብ፡ነበሩ፤ወጥተውም፡ከቤትአዌን፡በምሥራቅ፡በኩል፡ በማክማስ፡ሰፈሩ።
6ሕዝቡም፡ተጨንቀው፡ነበርና፥የእስራኤል፡ሰዎች፡በጭንቀት፡እንዳሉ፡ባዩ፡ጊዜ፡ሕዝቡ፡በዋሻና፡በሾኽ፡ ቍጥቋጦ፡በገደልና፡በግንብ፡በጕድጓድም፡ውስጥ፡ተሸሸጉ።
7ከዕብራውያንም፡ዮርዳኖስን፡ተሻግረው፡ወደ፡ጋድና፡ወደገለዓድ፡ምድር፡ኼዱ፤ሳኦል፡ግን፡ገና፡በገልገላ፡ ነበረ፥ሕዝቡም፡ዅሉ፡ተንቀጥቅጠው፡ተከተሉት።
8ሳኦልም፡ሳሙኤል፡እንደ፡ቀጠረው፡ጊዜ፡ሰባት፡ቀን፡ቈየ፤ሳሙኤል፡ግን፡ወደ፡ገልገላ፡ አልመጣም፥ሕዝቡም፡ከርሱ፡ተለይተው፡ተበታተኑ።
9ሳኦልም፦የሚቃጠል፡መሥዋዕትና፡የደኅንነት፡መሥዋዕት፡አምጡልኝ፡አለ።የሚቃጠለውንም፡መሥዋዕት፡ አሳረገ።
10የሚቃጠለውንም፡መሥዋዕት፡ማሳረግ፡በፈጸመ፡ጊዜ፥እንሆ፥ሳሙኤል፡መጣ፤ሳኦልም፡እንዲመርቀው፡ ሊገናኘው፡ወጣ።
11ሳሙኤልም፦ያደረግኸው፡ምንድር፡ነው፧አለ።ሳኦልም፦ሕዝቡ፡ከእኔ፡ተለይተው፡እንደ፡ ተበታተኑ፥አንተም፡በቀጠሮው፡እንዳልመጣኽ፥ፍልስጥኤማውያንም፡ወደ፡ማክማስ፡እንደ፡ተሰበሰቡ፡አየኹ፤
12ሰለዚህ፦ፍልስጥኤማውያን፡አኹን፡ወደ፡ገልገላ፡ይወርዱብኛል፥እኔም፡የእግዚአብሔርን፡ሞገስ፡ አልለመንኹም፡አልኹ፤ስለዚህም፡ሳልታገሥ፡የሚቃጠልን፡መሥዋዕት፡አሳረግኹ፡አለ።
13ሳሙኤልም፡ሳኦልን፦አላበጀኽም፤አምላክኽ፡እግዚአብሔር፡ያዘዘኽን፡ትእዛዝ፡አልጠበቅኽም፤ዛሬ፡ እግዚአብሔር፡መንግሥትኽን፡በእስራኤል፡ላይ፡ለዘለዓለም፡አጽንቶልኽ፡ነበረ።
14አኹንም፡መንግሥትኽ፡አይጸናም፤እግዚአብሔር፡እንደ፡ልቡ፡የኾነ፡ሰው፡መርጧል፤እግዚአብሔርም፡ ያዘዘኽን፡አልጠበቅኽምና፡እግዚአብሔር፡በሕዝቡ፡ላይ፡አለቃ፡ይኾን፡ዘንድ፡አዞ፟ታል፡አለው።
15ሳሙኤልም፡ከገልገላ፡ተነሥቶ፡መንገዱን፡ኼደ፤የቀሩትም፡ሕዝብ፡ሳኦልን፡ተከተለው፡ሰልፈኛዎቹን፡ ሊገናኙ፡ኼዱ።ከገልገላም፡ተነሥተው፡ወደ፡ብንያም፡ጊብዓ፡መጡ፤ሳኦልም፡ከርሱ፡ጋራ፡የነበሩትን፡ሕዝብ፡ ቈጠረ፥ስድስት፡መቶም፡የሚያኽሉ፡ሰዎች፡ነበሩ።
16ሳኦልና፡ልጁ፡ዮናታንም፡ከነርሱም፡ጋራ፡የነበሩ፡ሕዝብ፡በብንያም፡ጊብዓ፡ ተቀመጡ፤ፍልስጥኤማውያንም፡በማክማስ፡ሰፈሩ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
17ከፍልስጥኤማውያንም፡ሰፈር፡ማራኪዎች፡በሦስት፡ክፍል፡ኾነው፡ወጡ፤አንዱም፡ክፍል፡በዖፍራ፡ መንገድ፡ወደሦጋል፡ምድር፡ኼደ።
18ኹለተኛው፡ክፍል፡ወደቤት፡ሖሮን፡መንገድ፡ዞረ፤ሦስተኛውም፡ክፍል፡በበረሓው፡አጠገብ፡ባለው፡ ወደስቦይም፡ሸለቆ፡በሚመለከተው፡በዳርቻ፡መንገድ፡ዞረ።
19ፍልስጥኤማውያንም፦ዕብራውያን፡ሰይፍና፡ጦር፡እንዳይሠሩ፡ብለው፡ነበርና፥በእስራኤል፡ምድር፡ዅሉ፡ ብረተ፡ሠሪ፡አልተገኘም።
20እስራኤልም፡ዅሉ፡የማረሻውን፡ጫፍና፡ማጭዱን፡መጥረቢያውንና፡መቈፈሪያውን፡ይስል፡ዘንድ፡ወደ፡ ፍልስጥኤማውያን፡ይወርድ፡ነበር።
21ለማረሻው፡ጫፍና፡ለመቈፈሪያው፡ዋጋው፡የሰቅል፡ከ፫፡እጅ፡፪ቱ፡እጅ፡ነበረ።መጥረቢያውንም፡ ለማሳል፡መውጊያውንም፡ለማበጀት፡ዋጋው፡የሰቅል፡ከ
22ስለዚህም፡በሰልፍ፡ቀን፡ሰይፍና፡ጦር፡ከሳኦልና፡ከዮናታን፡ጋራ፡በነበሩ፡ሕዝብ፡ዅሉ፡እጅ፡ አልተገኘም፤ብቻ፡በሳኦልና፡በልጁ፡በዮናታን፡ዘንድ፡ተገኘ።የፍልስጥኤማውያንም፡ጭፍራ፡ወደማክማስ፡ መተላለፊያ፡ወጡ።