1አንድ፡ቀንም፡እንዲህ፡ኾነ፤የሳኦል፡ልጅ፡ዮናታን፡ጋሻ፡ዣግሬውን፦ና፥በዚያ፡በኩል፡ወዳለው፡ ወደፍልስጥኤማውያን፡ጭፍራ፡እንለፍ፡አለው፤ለአባቱም፡አልነገረውም።
2ሳኦልም፡በመጌዶን፡ባለው፡በሮማኑ፡ዛፍ፡በታች፡በጊብዓ፡ዳርቻ፡ተቀምጦ፡ነበረ፤ከርሱም፡ጋራ፡የነበረው፡ ሕዝብ፡ስድስት፡መቶ፡የሚያኽል፡ሰው፡ነበረ።
3የኢካቦድ፡ወንድም፡የአኪጦብ ፡ልጅ፡የፊንሐስ፡ልጅ፡የዔሊ፡ልጅ፡በሴሎ፡ለእግዚአብሔር፡ካህን፡የኾነ፡ ኤፉድም፡የለበሰ፡አኪያ፡ዐብሮ፡ነበር፤ሕዝቡ፡ዮናታን፡እንደ፡ኼደ፡አላወቁም።
4ዮናታንም፡ወደፍልስጥኤማውያን፡ጭፍራ፡ሊሻገርበት፡በወደደው፡መተላለፊያ፡መካከል፡በወዲህ፡አንድ፡ ሾጣጣ፡በወዲህ፡አንድ፡ሾጣጣ፡ድንጋዮች፡ነበሩ፤የአንዱም፡ስም፡ቦጼጽ፡የኹለተኛውም፡ስም፡ሴኔ፡ነበረ።
5አንዱም፡ሾጣጣ፡በማክማስ፡አንጻር፡በሰሜን፡በኩል፥ኹለተኛውም፡በጊብዓ፡አንጻር፡በደቡብ፡በኩል፡ የቆሙ፡ነበሩ።
6ዮናታንም፡ጋሻ፡ዣግሬውን፦ና፥ወደ፡እነዚህ፡ቈላፋን፡ጭፍራ፡እንለፍ፤በብዙ፡ወይም፡በጥቂት፡ማዳን፡ እግዚአብሔርን፡አያስቸግረውምና፡ምናልባት፡እግዚአብሔር፡ይሠራልን፡ይኾናል፡አለው።
7ጋሻ፡ዣግሬውም፦ልብኽ፡ያሠኘኽን፡ዅሉ፡አድርግ፤እንሆ፥ከአንተ፡ጋራ፡ነኝ፤እንደ፡አንተ፡ልብ፡ ዅሉ፡የእኔም፡ልብ፡እንዲሁ፡ነው፡አለው።
8ዮናታንም፡አለ፦እንሆ፥ወደ፡ሰዎቹ፡እናልፋለን፡እንገለጥላቸውማለን፤
9እነርሱም፦ወደ፡እናንተ፡እስክንመጣ፡ድረስ፡ቈዩ፡ቢሉን፡በስፍራችን፡እንቆማለን፥ወደ፡እነርሱም፡ አንወጣም።
10ነገር፡ግን፦ወደ፡እኛ፡ውጡ፡ቢሉን፡እግዚአብሔር፡በእጃችን፡አሳልፎ፡ ሰጥቷቸዋልና፥እንወጣለን፤ምልክታችንም፡ይህ፡ይኾናል።
11ኹለታቸውም፡ለፍልስጥኤማውያን፡ጭፍራ፡ተገለጡ፤ፍልስጥኤማውያንም፦እንሆ፥ዕብራውያን፡ ከተሸሸጉበት፡ጕድጓድ፡ይወጣሉ፡አሉ።
12የጭፍራው፡ሰዎችም፡ዮናታንንና፡ጋሻ፡ዣግሬውን፦ወደ፡እኛ፡ውጡ፥አንድ፡ነገርም፡እናሳያችዃለን፡ 137 ዕብ.፥አኂጦብ፡(አኅወ፡ጦቢያ፥የመልካም፡የበጎ፡ወንድም)። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org አሉ።ዮናታንም፡ጋሻ፡ዣግሬውን፦እግዚአብሔር፡በእስራኤል፡እጅ፡አሳልፎ፡ሰጥቷቸዋልና፥ተከተለኝ፡አለው።
13ዮናታንም፡በእጁና፡በእግሩ፡ወጣ፥ጋሻ፡ዣግሬውም፡ተከተለው፤ፍልስጥኤማውያንም፡በዮናታን፡እጅ፡ ወደቁ፥ጋሻ፡ዣግሬውም፡ተከትሎ፡ገደላቸው።
14የዮናታንና፡የጋሻ፡ዣግሬውም፡የመዠመሪያ፡ግዳያቸው፡ባንድ፡ትልም፡ዕርሻ፡መካከል፡ኻያ፡ያኽል፡ ሰው፡ነበረ።
15በሰፈሩም፡በዕርሻውና፡በሕዝቡም፡ዅሉ፡መካከል፡ሽብር፡ነበረ፤በሰፈሩ፡የተቀመጡና፡ለምርኮ፡የወጡት፡ ተሸበሩ፤ምድሪቱም፡ተናወጠች፤ከእግዚአብሔርም፡ዘንድ፡ታላቅ፡ሽብር፡ኾነ።
16በብንያም፡ጊብዓ፡ያሉ፡የሳኦል፡ዘበኛዎችም፡ተመለከቱ፤እንሆም፥ሰራዊቱ፡ወዲህና፡ወዲያ፡እየተራወጡ፡ ተበታተኑ።
17ሳኦልም፡ከርሱ፡ጋራ፡የነበሩትን፡ሕዝብ።እስኪ፡ተቋጠሩ፥ከእኛ፡ዘንድ፡የኼደ፡ማን፡እንደ፡ኾነ፡ ተመልከቱ፡አላቸው።በተቋጠሩም፡ጊዜ፥እንሆ፥ዮናታንና፡ጋሻ፡ዣግሬው፡በዚያ፡አልነበሩም።
18በዚያም፡ቀን፡አኪያ፡በእስራኤል፡ልጆች፡ፊት፡ኤፉድ፡ለብሶ፡ነበርና፥ሳኦል፦ኤፉድን፡አምጣ፡አለው።
19ሳኦል፡ከካህኑ፡ጋራ፡ሲነጋገር፡በፍልስጥኤማውያን፡ሰፈር፡ግርግርታ፡እየበዛና፡እየጠነከረ፡ኼደ፤ሳኦልም፡ ካህኑን፦እጅኽን፡መልስ፡አለው።
20ሳኦልና፡ከርሱም፡ጋራ፡የነበሩት፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ተሰብስበው፡ወደ፡ውጊያው፡መጡ፤እንሆም፥የያንዳንዱ፡ ሰው፡ሰይፍ፡በባልንጀራው፡ላይ፡ነበረ፥እጅግም፡ታላቅ፡ድንጋጤ፡ኾነ።
21ቀድሞ፡ከፍልስጥኤማውያን፡ጋራ፡የነበሩት፡ከነርሱም፡ጋራ፡ከሰፈሩ፡ዙሪያ፡የወጡት፡ዕብራውያን፡ደግሞ፡ ከሳኦልና፡ከዮናታን፡ጋራ፡ወደነበሩት፡እስራኤላውያን፡ለመኾን፡ዞሩ።
22ከእስራኤልም፡ሰዎች፡በተራራማው፡በኤፍሬም፡አገር፡የተሸሸጉት፡ዅሉ፡ፍልስጥኤማውያን፡እንደ፡ ኰበለሉ፡በሰሙ፡ጊዜ፡እነርሱ፡ደግሞ፡ሊዋጓቸው፡ተከትለው፡ገሠገሡ።
23እግዚአብሔርም፡በዚያ፡ቀን፡እስራኤልን፡አዳነ፤ውጊያውም፡በቤትአዌን፡በኩል፡ዐለፈ።ከሳኦልም፡ጋራ፡ የነበሩ፡ሕዝብ፡ዅሉ፡ዐሥር፡ሺሕ፡የሚያኽሉ፡ሰዎች፡ነበሩ፤ውጊያውም፡በተራራማው፡በኤፍሬም፡አገር፡ ዅሉ፡ተበታትኖ፡ነበር።
24የእስራኤልም፡ሰዎች፡በዚያ፡ቀን፡ተጨነቁ፤ሳኦል።ጠላቶቼን፡እስክበቀል፡እስከ፡ማታ፡ድረስ፡መብል፡ የሚበላ፡ሰው፡ርጉም፡ይኹን፡ብሎ፡ሕዝቡን፡አምሏቸው፡ነበርና።ሕዝቡም፡ዅሉ፡መብል፡አልቀመሱም።
25ሕዝቡም፡ዅሉ፡ወደ፡ዱር፡ገባ፤ማርም፡በምድር፡ላይ፡ነበረ።
26ሕዝቡም፡ወደ፡ዱር፡በገባ፡ጊዜ፥እንሆ፥የሚፈስ፟፡ማር፡ነበረ፤ሕዝቡ፡መሐላውን፡ፈርቶ፡ ነበርና፥ማንም፡እጁን፡ወደ፡አፉ፡አላደረገም።
27ዮናታን፡ግን፡አባቱ፡ሕዝቡን፡ባማለ፡ጊዜ፡አልሰማም፡ነበር፤ርሱም፡በእጁ፡ያለችውን፡በትር፡ጫፏን፡ ወደ፡ወለላው፡ነከረ፥እጁንም፡ወደ፡አፉ፡አደረገ፤ዐይኑም፡በራ።
28ከሕዝቡም፡አንድ፡ሰው፡መልሶ፦አባትኽ።ዛሬ፡መብል፡የሚበላ፡ሰው፡ርጉም፡ይኹን፡ብሎ፡ሕዝቡን፡ መሐላ፡አምሏቸዋል፡አለው፤ሕዝቡም፡ደከሙ።
29ዮናታንም፦አባቴ፡ምድሪቱን፡አስቸገረ፤ከዚህ፡ማር፡ጥቂት፡ብቀምስ፡ዐይኔ፡እንደ፡በራ፡እዩ።
30ይልቅስ፡ሕዝቡ፡ካገኙት፡ከጠላቶቻቸው፡ምርኮ፡በልተው፡ቢኾኑ፡የፍልስጥኤማውያን፡መመታት፡ይበልጥ፡ አልነበረምን፧አለ።
31በዚያም፡ቀን፡ፍልስጥኤማውያንን፡ከማክማስ፡እስከ፡ኤሎን፡ድረስ፡መቷቸው፤ሕዝቡም፡እጅግ፡ደከሙ።
32ሕዝቡም፡ለምርኮ፡ሣሡ፤በጎችን፡በሬዎችንም፡ጥጃዎችንም፡ወስደው፡በምድር፡ላይ፡ዐረዱ፤ሕዝቡም፡ ከደሙ፡ጋራ፡በሉ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
33ለሳኦልም፦እንሆ፥ሕዝቡ፡ከደሙ፡ጋራ፡በመብላታቸው፡እግዚአብሔርን፡በደሉ፡ብለው፡ ነገሩት።ሳኦልም፦እጅግ፡ተላለፋችኹ፤አኹንም፡ትልቅ፡ድንጋይ፡አንከባላ፟ችኹ፡አቅርቡልኝ፡አላቸው።
34ሳኦልም፦በሕዝቡ፡መካከል፡እየዞራችኹ።እያንዳንዱ፡ሰው፡በሬውንና፡በጉን፡ወደ፡እኔ፡ ያቅርብ፥በዚህም፡ዕረዱና፡ብሉ፤ከደሙም፡ጋራ፡በመብላታችኹ፡እግዚአብሔርን፡አትበድሉ፡በሏቸው፡ አለው።እያንዳንዱም፡ሰው፡ዅሉ፡በእጁ፡ያለውን፡በሬውን፡በዚያች፡ሌሊት፡አቀረበ፥በዚያም፡ዐረደው።
35ሳኦልም፡ለእግዚአብሔር፡መሠዊያን፡ሠራ፤ይኸውም፡ለእግዚአብሔር፡የሠራው፡መዠመሪያ፡መሠዊያ፡ ነው።
36ሳኦልም፦ፍልስጥኤማውያንን፡በሌሊት፡ተከትለን፡እስኪነጋ፡ድረስ፡እንበዝብዛቸው፤አንድ፡ሰው፡እንኳ፡ አናስቀርላቸው፡አለ።እነርሱም፦ደስ፡የሚያሠኝኽን፡ዅሉ፡አድርግ፡አሉት።ካህኑም፦ወደ፡እግዚአብሔር፡ እንቅረብ፡አለ።
37ሳኦልም፦ፍልስጥኤማውያንን፡ልከተልን፧በእስራኤልስ፡እጅ፡አሳልፈኽ፡ትሰጣቸዋለኽን፧ብሎ፡ እግዚአብሔርን፡ጠየቀው።በዚያ፡ቀን፡ግን፡አልመለሰለትም።
38ሳኦልም፦እናንተ፡የሕዝቡ፡አለቃዎች፡ዅሉ፥ወደዚህ፡ቅረቡ፤ዛሬ፡ይህ፡ኀጢአት፡በምን፡እንደ፡ኾነ፡ ዕወቁ፥ተመልከቱም፤
39እስራኤልን፡የሚያድን፡ሕያው፡እግዚአብሔርን! ኀጢአቱ፡በልጄ፡በዮናታን፡ቢኾን፡ፈጽሞ፡ይሞታል፡ አለ።ከሕዝቡም፡ዅሉ፡አንድ፡የመለሰለት፡ሰው፡አልነበረም።
40እስራኤልንም፡ዅሉ፦እናንተ፡ባንድ፡ወገን፡ኹኑ፥እኔና፡ልጄ፡ዮናታንም፡በሌላ፡ወገን፡እንኾናለን፡ አለ።ሕዝቡም፡ሳኦልን፡ደስ፡የሚያሠኝኽን፡አድርግ፡አሉት።
41ሳኦልም፡የእስራኤልን፡አምላክ፡እግዚአብሔርን፦እውነትን፡ግለጥ፡አለው።ሳኦልና፡ዮናታንም፡ ተያዙ፤ሕዝቡም፡ነጻ፡ኾነ።
42ሳኦልም፦በእኔና፡በልጄ፡በዮናታን፡መካከል፡ዕጣ፡ጣሉ፡አለ።ዮናታንም፡ተያዘ።
43ሳኦልም፡ዮናታንን፦ያደረግኸውን፡ንገረኝ፡አለው፤ዮናታንም፦በእጄ፡ባለው፡በበትሬ፡ጫፍ፡ጥቂት፡ ማር፡በርግጥ፡ቀምሻለኹ፤እንሆኝ፥እሞታለኹ፡ብሎ፡ነገረው።
44ሳኦልም፦እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ያድርግብኝ፡እንዲህም፡ይጨምርብኝ፤ዮናታን፡ሆይ፥ፈጽመኽ፡ ትሞታለኽ፡አለ።
45ሕዝቡም፡ሳኦልን፦በእውኑ፡በእስራኤል፡ዘንድ፡ታላቅ፡መድኀኒት፡ያደረገ፡ዮናታን፡ይሞታልን፧ይህ፡ አይኹን፤ዛሬ፡ከእግዚአብሔር፡ጋራ፡አድርጓልና፥ሕያው፡እግዚአብሔርን! ከራሱ፡ጠጕር፡አንዲት፡በምድር፡ ላይ፡አትወድቅም፡አሉት።ሕዝቡም፡እንዳይሞት፡ዮናታንን፡አዳነው።
46ሳኦልም፡ፍልስጥኤማውያንን፡ከመከተል፡ተመለሰ፤ፍልስጥኤማውያንም፡ወደ፡ስፍራቸው፡ኼዱ።
47ሳኦልም፡መንግሥቱን፡በእስራኤል፡ላይ፡አጸና፤በዙሪያውም፡ካሉት፡ከጠላቶቹ፡ዅሉ፡ ጋራ፥ከሞዐብም፥ከዐሞንም፡ልጆች፥ከኤዶምያስም፥ከሱባም፡ነገሥታት፥ከፍልስጥኤማውያንም፡ጋራ፡ይዋጋ፡ ነበር፤በየኼደበትም፡ዅሉ፡ድል፡ይነሣ፡ነበር።
48ርሱም፡ዠግና፡ነበረ፥ዐማሌቃውያንንም፡መታ፥እስራኤልንም፡ከዘራፊዎቹ፡እጅ፡አዳነ።
49የሳኦልም፡ወንዶች፡ልጆች፡ዮናታን፥የሱዊ፥ሜልኪሳ፡ነበሩ፤የኹለቱም፡ሴቶች፡ልጆቹ፡ስም፡ይህ፡ ነበረ፤የታላቂቱ፡ስም፡ሜሮብ፥የታናሺቱም፡ስም፡ሜልኮል፡ነበረ።
50የሳኦልም፡ሚስት፡ስም፡የአኪማዐስ ፡ልጅ፡አኪናሖም ፡ነበረ፤የሰራዊቱም፡አለቃ፡ስም፡የሳኦል፡አጎት፡ የኔር፡ልጅ፡አበኔር፡ነበረ። 138 ዕብ.፥አኂይማጽ፡(እኅወ፡መዓት፥የመዓት፡የቍጣ፡ወንድም)። 139 ዕብ.፥አኂኖዐም፡(በጎ፡ወንድም)። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
51የሳኦልም፡አባት፡ቂስ፡ነበረ፤የአበኔርም፡አባት፡ኔር፡የአቢኤል፡ልጅ፡ነበረ።
52በሳኦልም፡ዕድሜ፡ዅሉ፡ከፍልስጥኤማውያን፡ጋራ፡ጽኑ፡ውጊያ፡ነበረ፤ሳኦልም፡ጽኑ፡ወይም፡ኀያል፡ ሰው፡ባየ፡ጊዜ፡ወደ፡ርሱ፡ይሰበስብ፡ነበር።