Skip to content
← 1 Samuel

Chapter 15 · Amharic

1 Samuel

1ሳሙኤልም፡ሳኦልን፡አለው፦በሕዝቡ፡በእስራኤል፡ላይ፡ንጉሥ፡እንድትኾን፡እቀባኽ፡ዘንድ፡እግዚአብሔር፡ ላከኝ፥አኹንም፡የእግዚአብሔርን፡ድምፅ፡ስማ።

2የሰራዊት፡ጌታ፡እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦እስራኤል፡ከግብጽ፡በወጣ፡ጊዜ፡ዐማሌቅ፡በመንገድ፡ እየተቃወመ፡ያደረገበትን፡እበቀላለኹ።

3አኹንም፡ኼደኽ፡ዐማሌቅን፡ምታ፥ያላቸውንም፡ዅሉ፡ፈጽመኽ፡አጥፋ፥አትማራቸውም፤ወንዱንና፡ሴቱን፡ ብላቴናውንና፡ሕፃኑን፡በሬውንና፡በጉን፡ግመሉንና፡አህያውን፡ግደል።

4ሳኦልም፡ሕዝቡን፡ጠርቶ፡በገልገላ፡ቈጠራቸው፤ኹለት፡መቶ፡ሺሕ፡እግረኛዎች፥ከይሁዳም፡ዐሥር፡ ሺሕ፡ሰዎች፡ነበሩ።

5ሳኦልም፡ወደዐማሌቅ፡ከተማ፡ወጣ፥በሸለቆውም፡ውስጥ፡ተደበቀ።

6ሳኦል፡ቄናውያንን፦ተነሥታችኹ፡ኺዱ፤ከግብጽ፡በወጡ፡ጊዜ፡ለእስራኤል፡ልጆች፡ቸርነት፡ አድርጋችዃልና፥ከዐማሌቅ፡ጋራ፡እንዳላጠፋችኹ፡ከመካከላቸው፡ውረዱ፡አላቸው፤ቄናውያንም፡ ከዐማሌቃውያን፡መካከል፡ኼዱ።

7ሳኦልም፡ዐማሌቃውያንን፡ከኤውላጥ፡ዠምሮ፡በግብጽ፡ፊት፡እስካለችው፡እስከ፡ሱር፡ድረስ፡መታቸው።

8የዐማሌቅንም፡ንጉሥ፡አጋግን፡በሕይወቱ፡ማረከው፥ሕዝቡንም፡ዅሉ፡በሰይፍ፡ስለት፡ፈጽሞ፡አጠፋቸው።

9ነገር፡ግን፥ሳኦልና፡ሕዝቡ፡ለአጋግ፥ለተመረጡትም፡በጎችና፡በሬዎች፡ለሰቡትም፡ጥጃዎችና፡ ጠቦቶች፥ለመልካሞቹም፡ዅሉ፡ራሩላቸው፥ፈጽሞ፡ሊያጠፏቸውም፡አልወደዱም፤ነገር፡ግን፥ምናምንቴንና፡ የተናቀውን፡ዅሉ፡ፈጽመው፡አጠፉት።

11የእግዚአብሔርም፡ቃል።ሳኦል፡እኔ፡ከመከተል፡ተመልሷልና፥ትእዛዜንም፡አልፈጸመምና፡ ስላነገሥኹት፡ተጸጸትኹ፡ብሎ፡ወደ፡ሳሙኤል፡መጣ።ሳሙኤልም፡ተቈጣ፤ሌሊቱንም፡ዅሉ፡ወደ፡ እግዚአብሔር፡ጮኸ።

12ሳሙኤልም፡በነጋው፡ሳኦልን፡ለመገናኘት፡ማለደ።ሳኦልም፡ወደ፡ቀርሜሎስ፡ መጣ፤እንሆም፥የመታሰቢያ፡ዐምድ፡ባቆመ፡ጊዜ፡ዞሮ፡ዐለፈ፥ወደ፡ገልገላም፡ወረደ፡የሚል፡ወሬ፡ ለሳሙኤል፡ደረሰለት።

13ሳሙኤልም፡ወደ፡ሳኦል፡መጣ፤ሳኦልም፦አንተ፡ለእግዚአብሔር፡የተባረክኽ፡ኹን፡የእግዚአብሔርን፡ ትእዛዝ፡ፈጽሜያለኹ፡አለው።

14ሳሙኤልም፦ይህ፡በዦሮዬ፡የምሰማው፡የበጎች፡ጩኸትና፡የበሬዎች፡ግሣት፡ምንድር፡ነው፧አለ።

15ሳኦልም፦ሕዝቡ፡ለአምላክኽ፡ለእግዚአብሔር፡ይሠዉአቸው፡ዘንድ፡መልካሞቹን፡በጎችና፡በሬዎች፡ አድነዋቸዋልና፥ከዐማሌቃውያን፡አምጥተዋቸዋል፤የቀሩትንም፡ፈጽመን፡አጠፋን፡አለው።

16ሳሙኤልም፡ሳኦልን፦ቈይ፥እግዚአብሔር፡ዛሬ፡ሌሊት፡የነገረኝን፡ልንገርኽ፡አለው፤ርሱም፦ተናገር፡ አለው።

17ሳሙኤልም፡አለ፦በዐይንኽ፡ምንም፡ታናሽ፡ብትኾን፡ለእስራኤል፡ነገዶች፡አለቃ፡ አልኾንኽምን፧እግዚአብሔርም፡በእስራኤል፡ላይ፡ንጉሥ፡ትኾን፡ዘንድ፡ቀባኽ።

18እግዚአብሔርም፦ኼደኽ፡ኀጢአተኛዎቹን፡ዐማሌቃውያንን፡ፈጽመኽ፡አጥፋቸው፥እስኪጠፉም፡ድረስ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ውጋቸው፡ብሎ፡በመንገድ፡ላከኽ።

19ለምርኮ፡ሳስተኽ፡ለምን፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡አልሰማኽም፧ለምንስ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ክፉ፡ አደረግኽ፧

20ሳኦልም፡ሳሙኤልን፦የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ሰምቻለኹ፥እግዚአብሔርም፡በላከኝ፡መንገድ፡ ኼጃለኹ፤የዐማሌቅን፡ንጉሥ፡አጋግን፡አምጥቻለኹ፥ዐማሌቃውያንንም፡ፈጽሜ፡አጥፍቻለኹ።

21ሕዝቡ፡ግን፥ለአምላክኽ፣ለእግዚአብሔር፡በገልገላ፡ይሠዉ፡ዘንድ፥ከዕርሙ፡የተመረጡትን፡በጎችንና፡ በሬዎችን፡ከምርኮው፡ወሰዱ፥አለው።

22ሳሙኤልም፦በእውኑ፡የእግዚአብሔርን፡ቃል፡በመስማት፡ደስ፡እንደሚለው፡እግዚአብሔር፡በሚቃጠልና፡ በሚታረድ፡መሥዋዕት፡ደስ፡ይለዋልን፧እንሆ፥መታዘዝ፡ከመሥዋዕት፥ማዳመጥም፡የአውራ፡በግ፡ስብ፡ ከማቅረብ፡ይበልጣል።

23ዐመፀኝነት፡እንደ፡ሟርተኛ፡ኀጢአት፥እልከኝነትም፡ጣዖትንና፡ተራፊምን፡እንደ፡ማምለክ፡ ነው፤የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ንቀኻልና፥እግዚአብሔር፡ንጉሥ፡እንዳትኾን፡ናቀኽ፡አለ።

24ሳኦልም፡ሳሙኤልን፦ሕዝቡን፡ስለ፡ፈራኹ፥ቃላቸውንም፡ስለ፡ሰማኹ፡የእግዚአብሔርን፡ትእዛዝና፡ የአንተን፡ቃል፡በመተላለፍ፡በድያለኹ።

25አኹንም፥እባክኽ፥ኀጢአቴን፡ይቅር፡በለኝ፥ለእግዚአብሔርም፡እሰግድ፡ዘንድ፡ከእኔ፡ጋራ፡ተመለስ፡ አለው።

26ሳሙኤልም፡ሳኦልን፦የእግዚአብሔርን፡ቃል፡ንቀኻልና፥እግዚአብሔርም፡በእስራኤል፡ላይ፡ንጉሥ፡ እንዳትኾን፡ንቆኻልና፥ከአንተ፡ጋራ፡አልመለስም፡አለው።

27ሳሙኤልም፡ሊኼድ፡ዘወር፡ባለ፡ጊዜ፡ሳኦል፡የልብሱን፡ጫፍ፡ያዘ፥ተቀደደም።

28ሳሙኤልም፦እግዚአብሔር፡የእስራኤልን፡መንግሥት፡ዛሬ፡ከአንተ፡ቀደዳት፥ከአንተም፡ለሚሻል፡ ለጎረቤትኽ፡አሳልፎ፡ሰጣት፤

29የእስራኤል፡ኀይል፡እንደ፡ሰው፡የሚጸጸት፡አይደለምና፡አይዋሽም፡አይጸጸትምም፡አለው።

30ርሱም፦በድያለኹ፤አኹን፡ግን፡በሕዝቤ፡ሽማግሌዎች፡ፊትና፡በእስራኤል፡ ፊት፥እባክኽ፥አክብረኝ፤ለአምላክኽም፡ለእግዚአብሔር፡እሰግድ፡ዘንድ፡ከእኔ፡ጋራ፡ተመለስ፡አለው።

31ሳሙኤልም፡ከሳኦል፡በዃላ፡ተመለሰ፤ሳኦልም፡ለእግዚአብሔር፡ሰገደ።

32ሳሙኤልም፦የዐማሌቅን፡ንጉሥ፡አጋግን፡አምጡልኝ፡አለ።አጋግም፡እየተንቀጠቀጠ፡ወደ፡ርሱ፡ መጣ።አጋግም፦በእውኑ፡ሞት፡እንደዚህ፡መራራ፡ነውን፧አለ።

33ሳሙኤልም፦ሰይፍኽ፡ሴቶችን፡ልጆች፡አልባ፡እንዳደረገቻቸው፡እንዲሁ፡እናትኽ፡በሴቶች፡መካከል፡ ልጅ፡አልባ፡ትኾናለች፡አለ፤ሳሙኤልም፡አጋግን፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡በገልገላ፡ቈራረጠው።

34ሳሙኤልም፡ወደ፡አርማቴም፡ኼደ፤

35ሳኦልም፡ወደ፡ቤቱ፡ወደ፡ጊብዓ፡ወጣ።ሳሙኤልም፡እስከ፡ሞተበት፡ቀን፡ድረስ፡ሳኦልን፡ለማየት፡ ዳግመኛ፡አልኼደም፥ሳሙኤልም፡ለሳኦል፡አለቀሰ፤እግዚአብሔርም፡በእስራኤል፡ላይ፡ሳኦልን፡ስላነገሠ፡ ተጸጸተ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source