Skip to content
← 1 Samuel

Chapter 18 · Amharic

1 Samuel

1ዳዊትም፡ለሳኦል፡መናገሩን፡በፈጸመ፡ጊዜ፡የዮናታን፡ነፍስ፡በዳዊት፡ነፍስ፡ታሰረች፥ዮናታንም፡እንደ፡ ነፍሱ፡ወደደው።

2በዚያም፡ቀን፡ሳኦል፡ወሰደው፥ወዳባቱም፡ቤት፡ይመልሰው፡ዘንድ፡አልተወውም።

3ዮናታንም፡እንደ፡ነፍሱ፡ስለ፡ወደደው፡ከዳዊት፡ጋራ፡ቃል፡ኪዳን፡አደረገ።

4ዮናታንም፡የለበሰውን፡ካባ፡አውልቆ፡ርሱንና፡ልብሱን፡ሰይፉንም፡ሸለመው።ዮናታንም፡የለበሰውን፡ካባ፡ አውልቆ፡ርሱንና፡ልብሱን፡ሰይፉንም፡ቀስቱንም፡መታጠቂያውንም፡ለዳዊት፡ሸለመው።

5ዳዊትም፡ሳኦል፡ወደሰደደው፡ዅሉ፡ይኼድ፡ነበር፥አስተውሎም፡ያደርግ፡ነበር፤ሳኦልም፡በጦረኛዎች፡ላይ፡ ሾመው፤ይህም፡በሕዝብ፡ዅሉ፡ዐይን፡እና፡በሳኦል፡ባሪያዎች፡ዐይን፡መልካም፡ነበረ።

6እንዲህም፡ኾነ፤ዳዊት፡ፍልስጥኤማዊውን፡ገድሎ፡በተመለሰ፡ጊዜ፥እየዘመሩና፡እየዘፈኑ፡እልልም፡እያሉ፡ ከበሮና፡አታሞ፡ይዘው፡ንጉሡን፡ሳኦልን፡ሊቀበሉ፡ሴቶች፡ከእስራኤል፡ከተማዎች፡ዅሉ፡ወጡ።

7ሴቶችም፦ሳኦል፡ሺሕ፥ዳዊትም፡እልፍ፡ገደለ፡እያሉ፡እየተቀባበሉ፡ይዘፍኑ፡ነበር።

8ሳኦልም፡እጅግ፡ተቈጣ፥ይህም፡ነገር፡አስከፋው፤ርሱም፦ለዳዊት፡እልፍ፡ሰጡት፥ለእኔ፡ግን፡ሺሕ፡ ብቻ፡ሰጡኝ፤ከመንግሥት፡በቀር፡ምን፡ቀረበት፧አለ።

9ከዚያም፡ቀን፡ዠምሮ፡ሳኦል፡ዳዊትን፡ተመቅኝቶ፡ተመለከተው።

10በነጋውም፡ሳኦልን፡ክፉ፡መንፈስ፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ያዘው፥በቤቱም፡ውስጥ፡ትንቢት፡ ተናገረ።ዳዊትም፡በየቀኑ፡ያደርግ፡እንደ፡ነበረ፡በእጁ፡በገና፡ይመታ፡ነበር።ሳኦልም፡ጦሩን፡በእጁ፡ይዞ፡ ነበር።

11ሳኦልም፦ዳዊትን፡ከግንቡ፡ጋራ፡አጣብቄ፡እመታዋለኹ፡ብሎ፡ጦሩን፡ወረወረ።ዳዊትም፡ኹለት፡ጊዜ፡ ከፊቱ፡ዘወር፡አለ።

12እግዚአብሔርም፡ከርሱ፡ጋራ፡ስለ፡ነበረ፡ከሳኦልም፡ስለ፡ተለየ፡ሳኦል፡ዳዊትን፡ፈራው።

13ስለዚህም፡ሳኦል፡ከርሱ፡አራቀው፥የሺሕ፡አለቃም፡አደረገው፤በሕዝቡም፡ፊት፡ይወጣና፡ይገባ፡ነበር።

14ዳዊትም፡በአካኼዱ፡ዅሉ፡አስተውሎ፡ያደርግ፡ነበር፤እግዚአብሔርም፡ከርሱ፡ጋራ፡ነበረ።

15ሳኦልም፡እጅግ፡ብልኅ፡እንደ፡ኾነ፡አይቶ፡እጅግ፡ፈራው።

16ነገር፡ግን፥በፊታቸው፡ይወጣና፡ይገባ፡ስለ፡ነበር፥እስራኤልና፡ይሁዳ፡ዅሉ፡ዳዊትን፡ወደዱ።

17ሳኦልም፡ዳዊትን፦ታላቂቱ፡ልጄ፡ሜሮብ፡እንሇት፤ርሷን፡እድርልኻለኹ፤ብቻ፡ቀልጣፋ፡ልጅ፡ ኹንልኝ፥ስለእግዚአብሔርም፡ጦርነት፡ተጋደል፡አለው።ሳኦልም፦የፍልስጥኤማውያን፡እጅ፡በርሱ፡ላይ፡ ትኹን፡እንጂ፡የእኔ፡እጅ፡በርሱ፡ላይ፡አትኹን፡ይል፡ነበር።

18ዳዊትም፡ሳኦልን፦ለንጉሥ፡ዐማች፡እኾን፡ዘንድ፡እኔ፡ማን፡ነኝ፧ሰውነቴስ፡ምንድር፡ናት፧የአባቴስ፡ ወገን፡በእስራኤል፡ዘንድ፡ምንድር፡ነው፧አለው።

19ነገር፡ግን፥የሳኦል፡ልጅ፡ሜሮብ፡ዳዊትን፡የምታገባበት፡ጊዜ፡ሲደርስ፡ለመሐላታዊው፡ለኤስድሪኤል፡ ተዳረች።

20የሳኦልም፡ልጅ፡ሜልኮል፡ዳዊትን፡ወደደች፤ይህም፡ወሬ፡ለሳኦል፡ደረሰለት፥ነገሩም፡ደስ፡አሠኘው።

21ሳኦልም፦ወጥመድ፡ትኾነው፡ዘንድ፥የፍልስጥኤማውያንም፡እጅ፡በርሱ፡ላይ፡ትኾን፡ዘንድ፡ርሷን፡ እድርለታለኹ፡አለ፤ሳኦልም፡ዳዊትን፦ዛሬ፡ኹለተኛ፡ዐማች፡ትኾነኛለኽ፡አለው። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

22ሳኦልም፡ባሪያዎቹን፦እንሆ፥ንጉሥ፡እጅግ፡ወዶ፟ኻል፥ባሪያዎቹም፡ዅሉ፡ወደ፟ውኻል፥አኹንም፡ለንጉሥ፡ ዐማች፡ኹን፡ብላችኹ፡በስውር፡ለዳዊት፡ንገሩት፡ብሎ፡አዘዛቸው።

23የሳኦልም፡ባሪያዎች፡ይህን፡ቃል፡በዳዊት፡ዦሮ፡ተናገሩ፤ዳዊትም፦እኔ፡ድኻ፡የተጠቃኹም፡ሰው፡ ስኾን፡ለንጉሥ፡ዐማች፡እኾን፡ዘንድ፡ለእናንተ፡ትንሽ፡ነገር፡ይመስላችዃልን፧አለ።

24የሳኦልም፡ባሪያዎች።ዳዊት፡እንዲህ፡ብሎ፡ተናገረ፡ብለው፡ነገሩት።

25ሳኦልም፡ዳዊትን፡በፍልስጥኤማውያን፡እጅ፡ይጥለው፡ዘንድ፡ዐስቦ።የንጉሥን፡ጠላቶች፡ይበቀል፡ዘንድ፡ ከመቶ፡ፍልስጥኤማውያን፡ሸለፈት፡በቀር፡ንጉሥ፡ማጫ፡አይሻም፡ብላችኹ፡ለዳዊት፡ንገሩት፡አላቸው።

26የሳኦልም፡ባሪያዎች፡ይህን፡ቃል፡ለዳዊት፡ነገሩት፥ለንጉሥም፡ዐማች፡ይኾን፡ዘንድ፡ዳዊትን፡ደስ፡ አሠኘው።

27ዳዊትና፡ሰዎቹም፡ተነሥተው፡ኼዱ፥ከፍልስጥኤማውያንም፡መቶ፡ሰዎች፡ገደሉ፤ዳዊትም፡ለንጉሥ፡ ዐማች፡ይኾን፡ዘንድ፡ሰለባቸውን፡አምጥቶ፡በቍጥራቸው፡ልክ፡ለንጉሡ፡ሰጠ።ሳኦልም፡ልጁን፡ሜልኮልን፡ ዳረለት።

28ሳኦልም፡እግዚአብሔር፡ከዳዊት፡ጋራ፡እንደ፡ኾነ፡አየ፤እስራኤልም፡ዅሉ፡ወደዱት።

29ሳኦልም፡ዳዊትን፡አጥብቆ፡ፈራው፤ሳኦልም፡ዕድሜውን፡ዅሉ፡ለዳዊት፡ጠላት፡ኾነ።

30የፍልስጥኤማውያንም፡አለቃዎች፡ይወጡ፡ነበር፤በወጡም፡ጊዜ፡ዅሉ፡ከሳኦል፡ባሪያዎች፡ዅሉ፡ይልቅ፡ ዳዊት፡አስተውሎ፡ያደርግ፡ነበርና፥ስሙ፡እጅግ፡ተጠርቶ፡ነበር።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source