Skip to content
← 1 Samuel

Chapter 19 · Amharic

1 Samuel

1ሳኦልም፡ለልጁ፡ለዮናታንና፡ለባሪያዎቹ፡ዅሉ፡ዳዊትን፡ይገድሉ፡ዘንድ፡ነገራቸው።የሳኦል፡ልጅ፡ዮናታን፡ ግን፡ዳዊትን፡እጅግ፡ይወድ፟፡ነበር።

2ዮናታንም፦አባቴ፡ሳኦል፡ሊገድልኽ፡ፈልጓል፤አኹን፡እንግዲህ፡ለነገው፡ተጠንቅቀኽ፡ተሸሸግ፥በስውርም፡ ተቀመጥ፤

3እኔም፡እወጣለኹ፡አንተም፡ባለኽበት፡ዕርሻ፡በአባቴ፡አጠገብ፡እቆማለኹ፥ስለ፡አንተም፡ከአባቴ፡ጋራ፡ እነጋገራለኹ፤የኾነውንም፡አይቼ፡እነግርኻለኹ፡ብሎ፡ለዳዊት፡ነገረው።

4ዮናታንም፡ለአባቱ፡ለሳኦል፦ርሱ፡አልበደለኽምና፥ሥራውም፡ለአንተ፡እጅግ፡መልካም፡ኾኗልና፥ንጉሡ፡ ባሪያውን፡ዳዊትን፡አይበድለው፤

5ነፍሱንም፡በእጁ፡ጥሎ፡ፍልስጥኤማዊውን፡ገደለ፥እግዚአብሔርም፡ለእስራኤል፡ዅሉ፡ታላቅ፡መድኀኒት፡ አደረገ፤አንተም፡አይተኽ፡ደስ፡አለኽ፤በከንቱ፡ዳዊትን፡በመግደልኽ፡ስለ፡ምን፡በንጹሕ፡ደም፡ላይ፡ ትበድላለኽ፧ብሎ፡ስለ፡ዳዊት፡መልካም፡ተናገረ።

6ሳኦልም፡የዮናታንን፡ቃል፡ሰማ፤ሳኦልም፦ሕያው፡እግዚአብሔርን! ዳዊት፡አይገደልም፡ብሎ፡ማለ።

7ዮናታንም፡ዳዊትን፡ጠርቶ፡ይህን፡ነገር፡ዅሉ፡ነገረው፤ዮናታንም፡ዳዊትን፡ወደ፡ሳኦል፡አመጣው፥እንደ፡ ቀድሞውም፡በፊቱ፡ነበረ።

8ደግሞም፡ጦርነት፡ኾነ፤ዳዊትም፡ወጥቶ፡ከፍልስጥኤማውያን፡ጋራ፡ተዋጋ፥ታላቅ፡ግዳይም፡ ገደላቸው፥ከፊቱም፡ሸሹ።

9ሳኦልም፡ጦሩን፡ይዞ፡በቤቱ፡ተቀምጦ፡ሳለ፡ክፉ፡መንፈስ፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ያዘው።ዳዊትም፡በእጁ፡ በገና፡ይመታ፡ነበር።

10ሳኦልም፡ዳዊትን፡ከግንብ፡ጋራ፡ያጣብቀው፡ዘንድ፡ጦሩን፡ወረወረ፤ዳዊትም፡ከሳኦል፡ፊት፡ዘወር፡ አለ፥ጦሩም፡በግንቡ፡ውስጥ፡ተተከለ፤በዚያም፡ሌሊት፡ዳዊት፡ሸሽቶ፡አመለጠ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

11ሳኦልም፡ዳዊትን፡ጠብቀው፡በነጋው፡እንዲገድሉት፡መልእክተኛዎቹን፡ወደዳዊት፡ቤት፡ላከ፤ሚስቱም፡ ሜልኮል፦በዚች፡ሌሊት፡ነፍስኽን፡ካላዳንኽ፡ነገ፡ትገደላለኽ፡ብላ፡ነገረችው።

12ሜልኮልም፡ዳዊትን፡በመስኮት፡አወረደችው፤ኼደም፥ሸሽቶም፡አመለጠ።

13ሜልኮልም፡ተራፊምን፡ወስዳ፡በዐልጋ፡ላይ፡አኖረችው፥በራስጌውም፡ጕንጕን፡የፍየል፡ጠጕር፡ አደረገች፥በልብስም፡ከደነችው።

14ሳኦልም፡ዳዊትን፡እንዲያመጡት፡መልእክተኛዎችን፡ላከ፥ርሷም፦ታሟ፟ል፡አለቻቸው።

15ሳኦልም፦እገድለው፡ዘንድ፡ዳዊትን፡ከነ፡ዐልጋው፡አምጡልኝ፡ብሎ፡መልእክተኛዎቹን፡ወደ፡ዳዊት፡ ሰደደ።

16መልእክተኛዎቹም፡በገቡ፡ጊዜ፥እንሆ፥ተራፊሙን፡በዐልጋው፡ላይ፡አገኙ፥በራስጌውም፡ጕንጕን፡ የፍየል፡ጠጕር፡ነበረ።

17ሳኦልም፡ሜልኮልን፦ስለ፡ምን፡እንዲህ፡አድርገሽ፡አታለልሽኝ፧ጠላቴን፡አስኰበለልሽው፡ አላት።ሜልኮልም፡ለሳኦል፦ርሱ፦አውጥተሽ፡ስደጂኝ፥አለዚያም፡እገድልሻለኹ፡አለኝ፡ብላ፡መለሰችለት።

18ዳዊትም፡ሸሽቶ፡አመለጠ፥ወደ፡አርማቴምም፡ወደ፡ሳሙኤል፡መጣ፥ሳኦልም፡ያደረገበትን፡ዅሉ፡ ነገረው፤ርሱና፡ሳሙኤልም፡ኼዱ፡በነዋትዘራማም፡ተቀመጡ።

19ሳኦልም፦ዳዊት፥እንሆ፥በአርማቴም፡አገር፡በነዋትዘራማ፡ተቀምጧል፡የሚል፡ወሬ፡ሰማ።

20ሳኦልም፡ዳዊትን፡ያመጡት፡ዘንድ፡መልእክተኛዎችን፡ሰደደ፤የነቢያት፡ጉባኤ፡ትንቢት፡ ሲናገሩ፥ሳሙኤልም፡አለቃቸው፡ኾኖ፡ሲቆም፡ባዩ፡ጊዜ፡የእግዚአብሔር፡መንፈስ፡በሳኦል፡መልእክተኛዎች፡ ላይ፡ወረደ፥እነርሱም፡ትንቢት፡ይናገሩ፡ዠምር።

21ሳኦልም፡ያንን፡በሰማ፡ጊዜ፡ሌላዎች፡መልእክተኛዎችን፡ሰደደ፥እነርሱም፡ደግሞ፡ትንቢት፡ ተናገሩ።ሳኦልም፡እንደ፡ገና፡ሦስተኛ፡ጊዜ፡መልእክተኛዎችን፡ሰደደ፥እነርሱም፡ደግሞ፡ትንቢት፡ተናገሩ።

22የሳኦልም፡ቍጣ፡ነደደ፥ርሱም፡ደግሞ፡ወደ፡አርማቴም፡መጣ፥በሤኩም፡ወዳለው፡ወደ፡ታላቁ፡የውሃ፡ ጕድጓድ፡ደረሰ።ሳሙኤልና፡ዳዊት፡የት፡ናቸው፧ብሎ፡ጠየቀ፤አንድ፡ሰውም፦እንሆ፥በአርማቴም፡አገር፡ በነዋትዘራማ፡ናቸው፡አለው።

23ወደአርማቴምም፡አገር፡ወደ፡ነዋትዘራማ፡ኼደ፤የእግዚአብሔርም፡መንፈስ፡በርሱ፡ደግሞ፡ ወረደ፥ርሱም፡ኼደ፥ወደአርማቴምም፡አገር፡ወደ፡ነዋትዘራማ፡እስኪመጣ፡ድረስ፡ትንቢት፡ይናገር፡ነበር።

24ልብሱንም፡አወለቀ፥በሳሙኤልም፡ፊት፡ትንቢት፡ተናገረ፥ዕራቍቱንም፡ወድቆ፡በዚያ፡ቀን፡ዅሉ፡ በዚያም፡ሌሊት፡ዅሉ፡ተጋደመ።ስለዚህ፦ሳኦል፡ደግሞ፡ከነቢያት፡መካከል፡ነውን፧ይባባሉ፡ነበር።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source