1ለዳዊትም፦እንሆ፥ፍልስጥኤማውያን፡ቅዒላን፡ይወጋሉ፥ዐውድማውንም፡ይዘርፋሉ፡የሚል፡ወሬ፡ደረሰው። 141 ዕብ.፥አቢያታር፡(አበ፡ተረፍ፥የትርፍ፡አባት)። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
2ዳዊትም፦ልኺድን፧እነዚህንስ፡ፍልስጥኤማውያን፡ልምታን፧ብሎ፡እግዚአብሔርን፡ ጠየቀ፤እግዚአብሔርም፡ዳዊትን፦ኺድ፥ፍልስጥኤማውያንን፡ምታ፡ቅዒላንም፡አድን፡አለው።
3የዳዊትም፡ሰዎች፦እንሆ፥በዚህ፡በይሁዳ፡መቀመጥ፡እንፈራለን፥ይልቁንስ፡በፍልስጥኤማውያን፡ ጭፍራዎች፡ላይ፡ወደ፡ቅዒላ፡ብንኼድ፡እንዴት፡ነው፧አሉት።
4ዳዊትም፡ደግሞ፡እግዚአብሔርን፡ጠየቀ፤እግዚአብሔርም፡መልሶ፦ፍልስጥኤማውያንን፡በእጅኽ፡አሳልፌ፡ እሰጣለኹና፡ተነሥተኽ፡ወደ፡ቅዒላ፡ውረድ፡አለው።
5ዳዊትና፡ሰዎቹም፡ወደ፡ቅዒላ፡ኼዱ፥ከፍልስጥኤማውያንም፡ጋራ፡ተዋጉ፤እንስሳዎቻቸውንም፡ ማረኩ፥በታላቅም፡አገዳደል፡ገደሏቸው።ዳዊትም፡በቅዒላ፡የሚኖሩትን፡አዳነ።
6እንዲህም፡ኾነ፤የአቢሜሌክ፡ልጅ፡አብያታር፡ወደ፡ዳዊት፡ወደ፡ቅዒላ፡በኰበለለ፡ጊዜ፡ኤፉዱን፡ይዞ፡ ወርዶ፡ነበር።
7ሳኦልም፡ዳዊት፡ወደ፡ቅዒላ፡እንደ፡መጣ፡ሰማ፤ሳኦልም፦መዝጊያና፡መወርወሪያ፡ወዳለባት፡ከተማ፡ ገብቶ፡ተገኝቷልና፥እግዚአብሔር፡በእጄ፡አሳልፎ፡ሰጥቶታል፡አለ።
8ሳኦልም፡ወደ፡ቅዒላ፡ወርደው፡ይዋጉ፡ዘንድ፥ዳዊትንና፡ሰዎቹንም፡ይከቡ፟፡ዘንድ፡ሕዝቡን፡ዅሉ፡አዘዘ።
9ዳዊትም፡ሳኦል፡ክፉን፡እንዳሰበበት፡ዐወቀ፤ካህኑን፡አብያታርንም፦ኤፉዱን፡ወደዚህ፡አምጣ፡አለው።
10ዳዊትም፦የእስራኤል፡አምላክ፡አቤቱ፥በእኔ፡ምክንያት፡ከተማዪቱን፡ያጠፋ፡ዘንድ፡ሳኦል፡ወደ፡ቅዒላ፡ ሊመጣ፡እንደሚፈልግ፡እኔ፡ባሪያኽ፡ፈጽሜ፡ሰምቻለኹ።
11የቅዒላ፡ሰዎች፡በእጁ፡አሳልፈው፡ይሰጡኛልን፧ባሪያኽስ፡እንደ፡ሰማ፡ሳኦል፡በእውኑ፡ ይወርዳልን፧የእስራኤል፡አምላክ፡አቤቱ፥እንድትነግረኝ፡እለምንኻለኹ፡አለ።እግዚአብሔርም፦ይወርዳል፡አለ።
12ዳዊትም፦የቅዒላ፡ሰዎች፡እኔንና፡ሰዎቼን፡በሳኦል፡እጅ፡አሳልፈው፡ ይሰጡናልን፧አለ።እግዚአብሔርም፦አሳልፈው፡ይሰጧችዃል፡ብሎ፡ተናገረ።
13ዳዊትና፡ስድስት፡መቶ፡የሚኾኑ፡ሰዎችም፡ተነሥተው፡ከቅዒላ፡ወጡ፥መኼድም፡ወደሚችሉበት፡ ኼዱ።ሳኦልም፡ዳዊት፡ከቅዒላ፡እንደ፡ሸሸ፡ሰማ፤ስለዚህም፡ከመውጣት፡ቀረ።
14ዳዊትም፡በምድረ፡በዳ፡በዐምባ፡ውስጥ፡ይኖር፡ነበር፥ከዚፍ፡ምድረ፡በዳም፡ባለው፡በተራራማው፡አገር፡ ተቀመጠ፤ሳኦልም፡ዅል፡ጊዜ፡ይፈልገው፡ነበር፥እግዚአብሔር፡ግን፡በእጁ፡አሳልፎ፡አልሰጠውም።
15ዳዊትም፡ሳኦል፡ነፍሱን፡ሊፈልግ፡እንደ፡ወጣ፡አየ፤ዳዊትም፡በዚፍ፡ምድረ፡በዳ፡በጥሻው፡ውስጥ፡ ይኖር፡ነበር።
16የሳኦልም፡ልጅ፡ዮናታን፡ተነሥቶ፡ወደ፡ዳዊት፡ወደ፡ጥሻው፡ስጥ፡ኼደ፤እጁንም፡በእግዚአብሔር፡ አጽንቶ፦
17የአባቴ፡የሳኦል፡እጅ፡አታገኝኽምና፡አትፍራ፤አንተም፡በእስራኤል፡ላይ፡ንጉሥ፡ትኾናለኽ፥እኔም፡ ከአንተ፡በታች፡ኹለተኛ፡እኾናለኹ፤ይህን፡ደግሞ፡አባቴ፡ሳኦል፡ያውቃል፡አለው።
18ኹለቱም፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡ቃል፡ኪዳን፡አደረጉ፤ዳዊትም፡በጥሻው፡ውስጥ፡ተቀመጠ፥ዮናታንም፡ ወደ፡ቤቱ፡ኼደ።
19የዚፍ፡ሰዎችም፡ወደ፡ሳኦል፡ወደ፡ጊብዓ፡መጥተው፦እንሆ፥ዳዊት፡በየሴሞን፡ደቡብ፡በኩል፡በኤኬላ፡ ኰረብታ፡ላይ፡በጥሻ፡ውስጥ፡ባሉት፡ዐምባዎች፡በእኛ፡ዘንድ፡ተሸሽጎ፡የለምን፧
20አኹንም፥ንጉሥ፡ሆይ፥ትወርድ፡ዘንድ፡ነፍስኽ፡እንደ፡ወደደች፡ውረድ፤በንጉሡም፡እጅ፡ርሱን፡ አሳልፎ፡ለመስጠት፡እኛ፡አለን፡አሉት።
21ሳኦልም፡አለ፦እናንተ፡ስለ፡እኔ፡ዐዝናችዃልና፥ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡የተባረካችኹ፡ኹኑ፤
22አኹንም፡ደግሞ፡ኺዱ፤ርሱም፡እጅግ፡ተንኰለኛ፡እንደ፡ኾነ፡ሰምቻለኹና፡አጥብቃችኹ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ፈልጉት፥እግሩም፡የሚኼድበትን፡ስፍራ፡እዩና፡ዕወቁ፥በዚያ፡ያየውንም፡ሰው፡አግኙ።
23ርሱ፡የሚደበቅበትንና፡የሚሸሸግበትን፡ስፍራ፡እዩና፡ዕወቁ፥በርግጥም፡ወደ፡እኔ፡ተመለሱ፥እኔም፡ ከእናንተ፡ጋራ፡እኼዳለኹ፤በምድርም፡ውስጥ፡ቢሸሸግ፡በይሁዳ፡አእላፋት፡ዅሉ፡መካከል፡እፈልገዋለኹ።
24እነዚያም፡ተነሥተው፡ከሳኦል፡በፊት፡ወደ፡ዚፍ፡ኼዱ፤ዳዊትና፡ሰዎቹ፡ግን፡በየሴሞን፡ደቡብ፡በኩል፡ በዐረባ፡በማዖን፡ምድረ፡በዳ፡ነበሩ።
25ሳኦልና፡ሰዎቹም፡ሊፈልጉት፡ኼዱ፤ዳዊትም፡በሰማ፡ጊዜ፡ወደ፡አለቱ፡ወርዶ፡በማዖን፡ምድረ፡በዳ፡ ተቀመጠ፤ሳኦልም፡ያንን፡በሰማ፡ጊዜ፡ዳዊትን፡በማዖን፡ምድረ፡በዳ፡አሳደደው።
26ሳኦልም፡በተራራው፡ባንድ፡ወገን፡ኼደ፥ዳዊትና፡ሰዎቹም፡በተራራው፡በሌላው፡ወገን፡ኼዱ።ሳኦልና፡ ሰዎቹም፡ዳዊትንና፡ሰዎቹን፡ለመያዝ፡ከበ፟ዋቸው፡ነበርና፥ዳዊት፡ከሳኦል፡ፊት፡ያመልጥ፡ዘንድ፡ፈጠነ።
27ወደ፡ሳኦልም፡መልእክተኛ፡መጥቶ፦ፍልስጥኤማውያን፡አገሩን፡ወረ፟ውታልና፥ፈጥነኽ፡ና፡አለው።
28ሳኦልም፡ዳዊትን፡ማሳደድ፡ትቶ፡ተመለሰ፥ከፍልስጥኤማውያንም፡ጋራ፡ሊዋጋ፡ኼደ።ስለዚህ፡የዚህ፡ ስፍራ፡ስም፡የማምለጥ፡አለት፡ተባለ።
29ዳዊትም፡ከዚያ፡ወጥቶ፡በዐይንጋዲ፡ዐምባዎች፡ተቀመጠ።