Skip to content
← 1 Samuel

Chapter 24 · Amharic

1 Samuel

1እንዲህም፡ኾነ፤ሳኦል፡ፍልስጥኤማውያንን፡ከማሳደድ፡ከተመለሰ፡በዃላ፦እንሆ፥ዳዊት፡በዐይንጋዲ፡ ምድረ፡በዳ፡አለ፡የሚል፡ወሬ፡ደረሰለት።

2ሳኦልም፡ከእስራኤል፡ዅሉ፡የተመረጡትን፡ሦስት፡ሺሕ፡ሰዎች፡ወሰደ፥ዳዊትንና፡ሰዎቹንም፡ለመፈለግ፡ የበረሓ፡ፍየሎች፡ወደነበሩባቸው፡አለቶች፡ኼደ።

3በመንገድም፡አጠገብ፡ወዳሉት፡የበጎች፡ማደሪያዎች፡መጣ፥በዚያም፡ዋሻ፡ነበረ፤ሳኦልም፡ወገቡን፡ ይሞክር፡ዘንድ፡ከዚያ፡ገባ፤ዳዊትና፡ሰዎቹም፡ከዋሻው፡በውስጠኛው፡ቦታ፡ተቀምጠው፡ነበር።

4የዳዊትም፡ሰዎች፦እንሆ፥ጠላትኽን፡በእጅኽ፡አሳልፌ፡እሰጠዋለኹ፥በዐይንኽም፡ደስ፡የሚያሠኝኽን፡ ታደርግበታለኽ፡ብሎ፡እግዚአብሔር፡የነገረኽ፡ቀን፥እንሆ፥ዛሬ፡ነው፡አሉት።ዳዊትም፡ተነሥቶ፡የሳኦልን፡ መጐናጸፊያ፡ዘርፍ፡በቀስታ፡ቈረጠ።

5ከዚያም፡በዃላ፡እንዲህ፡ኾነ፤የሳኦልን፡የልብሱን፡ዘርፍ፡ስለ፡ቈረጠ፡የዳዊት፡ልብ፡በሐዘን፡ተመታ።

6ሰዎቹንም፦እግዚአብሔር፡የቀባው፡ነውና፥እግዚአብሔር፡በቀባው፡በጌታዬ፡ላይ፡እንዲህ፡ያለውን፡ነገር፡ ኣደርግ፡ዘንድ፡እጄንም፡እጥልበት፡ዘንድ፡እግዚአብሔር፡ከእኔ፡ያርቀው፡አላቸው።

7ዳዊትም፡በዚህ፡ቃል፡ሰዎቹን፡ከለከላቸው፥በሳኦልም፡ላይ፡ይነሡ፡ዘንድ፡አልተዋቸውም፤ሳኦልም፡ ከዋሻው፡ተነሥቶ፡መንገዱን፡ኼደ።

8ከርሱም፡በዃላ፡ዳዊት፡ደግሞ፡ተነሣ፥ከዋሻውም፡ወጣ፥ከሳኦልም፡በዃላ፦ጌታዬ፡ንጉሥ፡ሆይ፥ብሎ፡ ጮኸ፤ሳኦልም፡ወደ፡ዃላው፡ተመለከተ፥ዳዊትም፡ወደ፡ምድር፡ተጐንብሶ፡እጅ፡ነሣ።

9ዳዊትም፡ሳኦልን፡አለው፦እንሆ፥ዳዊት፡ክፉ፡ነገር፡ይሻብኻል፡የሚሉኽን፡ሰዎች፡ቃል፡ለምን፡ ትሰማለኽ፧

10እንሆ፥ዛሬ፡በዋሻው፡ውስጥ፡እግዚአብሔር፡በእጄ፡አሳልፎ፡እንደ፡ሰጠኽ፡ዐይንኽ፡አይታለች፤አንተንም፡ እንድገድልኽ፡ሰዎች፡ተናገሩኝ፤እኔ፡ግን፦በእግዚአብሔር፡የተቀባ፡ነውና፥እጄን፡በጌታዬ፡ላይ፡አልዘረጋም፡ ብዬ፡ራራኹልኽ።

11ደግሞም፥አባቴ፡ሆይ፥የልብስኽ፡ዘርፍ፡በእጄ፡እንዳለ፡ተመልክተኽ፡ዕወቅ፤የልብስኽንም፡ዘርፍ፡ በቈረጥኹ፡ጊዜ፡አልገደልኹኽም፤ስለዚህም፡በእጄ፡ክፋትና፡በደል፡እንደሌለ፥አንተም፡ነፍሴን፡ልትወስድ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ምንም፡ብታሳድደኝ፡እንዳልበደልኹኽ፡ተመልክተኽ፡ዕወቅ።

12እግዚአብሔር፡በእኔና፡በአንተ፡መካከል፡ይፍረድ፥እግዚአብሔርም፡አንተን፡ይበቀልልኝ፤እጄ፡ግን፡ባንተ፡ ላይ፡አትኾንም።

13በጥንት፡ምሳሌ፦ከኀጢአተኛዎች፡ኀጢአት፡ይወጣል፡እንደ፡ተባለ፤እጄ፡ግን፡ባንተ፡ላይ፡አትኾንም።

14የእስራኤል፡ንጉሥ፡ማንን፡ለማሳደድ፡መጥቷል፧አንተስ፡ማንን፡ታሳድዳለኽ፧የሞተ፡ውሻን፡ወይስ፡ ቍንጫን፡ታሳድዳለኽን፧

15እንግዲህ፡እግዚአብሔር፡ዳኛ፡ይኹን፥በእኔና፡በአንተም፡መካከል፡ይፍረድ፥አይቶም፡ ይሟገትልኝ፥ከእጅኽም፡ያድነኝ።

16እንዲህም፡ኾነ፤ዳዊት፡ይህን፡ቃል፡ለሳኦል፡መናገር፡በፈጸመ፡ጊዜ፥ሳኦል፦ልጄ፡ሆይ፡ዳዊት፥ይህ፡ ድምፅኽ፡ነውን፧አለ፤ሳኦልም፡ድምፁን፡ከፍ፡አድርጎ፡አለቀሰ።

17ዳዊትን፡አለው፦እኔ፡ክፉ፡በመለስኹልኽ፡ፋንታ፡በጎ፡መልሰኽልኛልና፥አንተ፡ከእኔ፡ይልቅ፡ጻድቅ፡ ነኽ።

18እግዚአብሔርም፡በእጅኽ፡አሳልፎ፡ሰጥቶኝ፡ሳለ፡አልገደልኸኝምና፥ለእኔ፡መልካም፡እንዳደረግኽልኝ፡ አንተ፡ዛሬ፡አሳየኸኝ።

19ጠላቱን፡አግኝቶ፡በመልካም፡መንገድ፡ሸኝቶ፡የሚሰድ፟፡ማን፡ነው፧ስለዚህ፡ለእኔ፡ስላደረግኸው፡ ቸርነት፡እግዚአብሔር፡ይመልስልኽ።

20አኹንም፥እንሆ፥አንተ፡በርግጥ፡ንጉሥ፡እንድትኾን፡የእስራኤልም፡መንግሥት፡በእጅኽ፡እንድትጸና፡እኔ፡ ዐውቃለኹ።

21አኹን፡እንግዲህ፡ከእኔ፡በዃላ፡ዘሬን፡እንዳትቈርጥ፡ከአባቴም፡ቤት፡ስሜን፡እንዳታጠፋው፡ በእግዚአብሔር፡ማልልኝ።

22ዳዊትም፡ለሳኦል፡ማለለት፤ሳኦልም፡ወደ፡ቤቱ፡ኼደ፥ዳዊትና፡ሰዎቹም፡ወደ፡ዐምባው፡ወጡ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source