1ሳሙኤልም፡ሞተ፤እስራኤልም፡ዅሉ፡ተሰብስበው፡አለቀሱለት፥በአርማቴምም፡በቤቱ፡ቀበሩት።ዳዊትም፡ ተነሥቶ፡ወደፋራን፡ምድረ፡በዳ፡ወረደ።
2በማዖንም፡የተቀመጠ፡አንድ፡ሰው፡ነበረ፥ከብቱም፡በቀርሜሎስ፡ነበረ፤እጅግም፡ታላቅ፡ሰው፡ ነበረ፥ለርሱም፡ሦስት፡ሺሕ፡በጎችና፡አንድ፡ሺሕ፡ፍየሎች፡ነበሩት፤በቀርሜሎስም፡በጎቹን፡ይሸልት፡ነበር።
3የሰውዮውም፡ስም፡ናባል፥የሚስቱም፡ስም፡አቢግያ ፡ነበረ፤የሴቲቱም፡አእምሮ፡ታላቅ፥መልኳም፡ የተዋበ፡ነበረ፤ሰውዮው፡ግን፡ባለጌ፡ነበረ፥ግብሩም፡ክፉ፡ነበረ፤ከካሌብም፡ወገን፡ነበረ።
4ዳዊትም፡በምድረ፡በዳ፡ሳለ፦ናባል፡በጎቹን፡ይሸልታል፡የሚል፡ወሬ፡ሰማ።
5ዳዊትም፡ዐሥር፡ጕልማሳዎች፡ላከ፡ለጕልማሳዎችም፡አለ፦ወደ፡ቀርሜሎስ፡ወጥታችኹ፡ወደ፡ናባል፡ ኺዱ፥በስሜም፡ስለ፡ሰላም፡ጠይቁት፤
6እንዲህም፡በሉት፦በደኅንነት፡ኑር፥ለአንተና፡ለቤትኽም፡ለአንተም፡ላሉት፡ዅሉ፡ሰላም፡ይኹን።
7አኹንም፡በጎችኽን፡እንድትሸልት፡ሰምቻለኹ፤እረኛዎችኽም፡ከእኛ፡ጋራ፡ነበሩ፥ከቶ፡ አልበደልናቸውም፤በቀርሜሎስም፡በተቀመጡበት፡ዘመን፡ዅሉ፡ከመንጋው፡አንዳች፡አልጐደለባቸውም።
8ጕልማሳዎችኽን፡ጠይቃቸው፥እነርሱም፡ይነግሩኻል፤አኹንም፡እንግዲህ፡በመልካም፡ቀን፡ 142 ዕብ.፥አቢጋይል። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org መጥተንብኻልና፥ጕልማሳዎች፡በፊትኽ፡ሞገስ፡ያግኙ፤በእጅኽም፡ከተገኘው፡ለባሪያዎችኽና፡ለልጅኽ፡ ለዳዊት፥እባክኽ፥ስጥ።
9የዳዊትም፡ጕልማሳዎች፡መጡ፥ይህንም፡ቃል፡ዅሉ፡በዳዊት፡ስም፡ለናባል፡ነግረው፡ዝም፡አሉ።
10ናባልም፡ለዳዊት፡ባሪያዎች።ዳዊት፡ማን፡ነው፧የእሴይስ፡ልጅ፡ማን፡ነው፧እያንዳንዳቸው፡ ከጌታዎቻቸው፡የኰበለሉ፡ባሪያዎች፡ዛሬ፡ብዙዎች፡ናቸው።
11እንጀራዬንና፡የወይን፡ጠጄን፡ለሸላቾቼም፡ያረድኹትን፡ሥጋ፡ወስጄ፡ከወዴት፡እንደ፡ኾኑ፡ ለማላውቃቸው፡ሰዎች፡እሰጣለኹን፧ብሎ፡መለሰላቸው።
12የዳዊትም፡ጕልማሳዎች፡ዞረው፡በመጡበት፡መንገድ፡ተመለሱ፥መጥተውም፡ይህን፡ነገር፡ዅሉ፡ለዳዊት፡ ነገሩት።
13ዳዊትም፡ሰዎቹን፦ዅላችኹ፡ሰይፋችኹን፡ታጠቁ፡አላቸው።ዅሉም፡ሰይፋቸውን፡ታጠቁ፥ዳዊትም፡ ሰይፉን፡ታጠቀ፤አራት፡መቶ፡ሰዎችም፡ዳዊትን፡ተከትለው፡ወጡ፥ኹለት፡መቶውም፡በዕቃው፡ዘንድ፡ ተቀመጡ።
14ከብላቴናዎቹ፡አንዱ፡ለናባል፡ሚስት፡ለአቢግያ፡እንዲህ፡ብሎ፡ነገራት፦እንሆ፥ዳዊት፡በምድረ፡በዳ፡ ሳለ፡ጌታችንን፡ሊባርኩ፡መልእክተኛዎች፡ላከ፤ርሱ፡ግን፡ሰደባቸው።
15እነዚህ፡ሰዎች፡ግን፡በእኛ፡ዘንድ፡እጅግ፡መልካም፡ነበሩ፤አልበደሉንምም፥ከነርሱም፡በኼድንበት፡ ዘመን፡ዅሉ፡በምድረ፡በዳ፡ሳለን፡አንዳች፡አልጠፋብንም፤
16ከነርሱ፡ጋራ፡ኾነን፡መንጋውን፡በጠበቅንበት፡ዘመን፡ዅሉ፡ሌሊትና፡ቀን፡ዐጥር፡ኾነውን፡ነበር።
17ስለዚህም፡በጌታችንና፡በቤቱ፡ዅሉ፡ላይ፡ክፉ፡ነገር፡እንዲመጣ፡ተቈርጧልና፥ርሱ፡ምናምንቴ፡ሰው፡ስለ፡ ኾነ፡ማንም፡ሊናገረው፡አይችልምና፡የምታደርጊውን፡ተመልከቺና፡ዕወቂ።
18አቢግያም፡ፈጥና፡ኹለት፡መቶ፡እንጀራ፥ኹለት፡አቍማዳ፡የወይን፡ጠጅ፥ዐምስትም፡የተዘጋጁ፡ በጎች፥ዐምስትም፡መስፈሪያ፡ጥብስ፡እሸት፥አንድ፡መቶ፡ዘለላ፡ዘቢብ፥ኹለት፡መቶም፡የበለስ፡ጥፍጥፍ፡ ወሰደች፥በአህያዎችም፡ላይ፡አስጫነች።
19ለብላቴናዎቿም፦አስቀድማችኹ፡በፊቴ፡ኺዱ፥እንሆም፥እከተላችዃለኹ፡አለች።ይህንም፡ለባሏ፡ለናባል፡ አልነገረችውም።
20ርሷም፡በአህያው፡ላይ፡ተቀምጣ፡በተራራው፡ላይ፡በተሰወረ፡ስፍራ፡በወረደች፡ጊዜ፥እንሆ፥ዳዊትና፡ ሰዎቹ፡ወደ፡ርሷ፡ወረዱ፤ርሷም፡ተገናኘቻቸው።
21ዳዊትም፦ለዚህ፡ሰው፡ከኾነው፡ዅሉ፡አንድ፡ነገር፡እንዳይጠፋበት፡በእውነት፡ከብቱን፡ዅሉ፡በምድረ፡ በዳ፡በከንቱ፡ጠበቅኹ፥ርሱም፡ስለ፡በጎነቴ፡ክፋት፡መለሰልኝ።
22ለርሱም፡ከኾነው፡ዅሉ፡እስከ፡ነገ፡ጧት፡ድረስ፡አንድ፡ወንድ፡ስንኳ፡ብተው፥እግዚአብሔር፡በዳዊት፡ ላይ፡እንዲህ፡ያድርግ፡እንዲህም፡ይጨምር፡ብሎ፡ነበር።
23አቢግያም፡ዳዊትን፡ባየች፡ጊዜ፡ከአህያዋ፡ላይ፡ፈጥና፡ወረደች፥በዳዊትም፡ፊት፡በግንባሯ፡ ወደቀች፥በምድርም፡ላይ፡እጅ፡ነሣች።
24በእግሩም፡ላይ፡ወደቀች፥እንዲህም፡አለች፦ጌታዬ፡ሆይ፥ይህ፡ኀጢአት፡በእኔ፡ላይ፡ይኹን፤እኔ፡ ባሪያኽ፡በዦሮኽ፡ልናገር፥የባሪያኽንም፡ቃል፡አድምጥ።
25በዚህ፡ምናምንቴ፡ሰው፡በናባል፡ላይ፡ጌታዬ፡ልቡን፡እንዳይጣል፡እለምናለኹ፤እንደ፡ስሙ፡እንዲሁ፡ ርሱ፡ነው፤ስሙ፡ናባል፡ነው፥ስንፍናም፡ዐድሮበታል፤እኔ፡ባሪያኽ፡ግን፡ከአንተ፡የተላኩትን፡የጌታዬን፡ ጕልማሳዎች፡አላየኹም።
26አኹንም፥ጌታዬ፡ሆይ፥ሕያው፡እግዚአብሔርን! በሕያው፡ነፍስኽም፡እምላለኹ! ወደ፡ደም፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org እንዳትገባ፥እጅኽም፡ራስኽን፡እንዳታድን፡የከለከለኽ፡እግዚአብሔር፡ነው፤አኹንም፡ጠላቶችኽና፡በጌታዬ፡ ላይ፡ክፉ፡የሚሹ፡ዅሉ፡እንደ፡ናባል፡ይኹኑ።
27አኹንም፡ባሪያኽ፡ወደ፡ጌታዬ፡ያመጣችው፡ይህ፡መተያያ፡ጌታዬን፡ለሚከተሉ፡ጕልማሳዎች፡ይሰጥ።
28የእግዚአብሔርን፡ጦርነት፡ስለምትዋጋ፡እግዚአብሔር፡በእውነት፡ለጌታዬ፡የታመነ፡ቤት፡ ይሠራልና፥የእኔን፡የባሪያኽን፡ኀጢአት፥እባክኽ፥ይቅር፡በል፤በዘመንኽም፡ዅሉ፡ክፋት፡አይገኝብኽም።
29ያሳድድኽ፡ዘንድ፡ነፍስኽንም፡ይሻ፡ዘንድ፡ሰው፡ቢነሣ፥የጌታዬ፡ነፍስ፡በሕያዋን፡ወገን፡በአምላክኽ፡ በእግዚአብሔር፡ዘንድ፡የታሰረች፡ትኾናለች፤የጠላቶችኽንም፡ነፋስ፡ከወንጭፍ፡እንደሚጣል፡እንዲሁ፡ ይጥላታል።
30እግዚአብሔርም፡ለጌታዬ፡የተናገረውን፡ቸርነት፡ዅሉ፡ባደረገልኽ፡ጊዜ፥በእስራኤልም፡ላይ፡አለቃ፡ አድርጎ፡ባስነሣኽ፡ጊዜ፥
31አንተ፡በከንቱ፡ደም፡እንዳላፈሰስኽ፥በገዛ፡እጅኽም፡እንዳልተካስኽ፡ይህ፡ዕንቅፋትና፡የኅሊና፡ጸጸት፡ በጌታዬ፡አይኾንልኽም፤እግዚአብሔርም፡ለጌታዬ፡በጎ፡ባደረገልኽ፡ጊዜ፥ባሪያኽን፡ዐስብ።
32ዳዊትም፡አቢግያን፡አላት፦ዛሬ፡እኔን፡ለመገናኘት፡አንቺን፡የሰደደ፡የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡ ይመስገን።
33ወደ፡ደም፡እንዳልኼድ፥በእጄም፡በቀል፡እንዳላደርግ፡ዛሬ፡የከለከለኝ፡አእምሮሽ፡የተመሰገነ፡ ይኹን፥አንቺም፡የተመሰገንሽ፡ኹኚ።
34ነገር፡ግን፥ክፉ፡እንዳላደርግብሽ፡የከለከለኝ፡የእስራኤል፡አምላክ፡ሕያው፡እግዚአብሔርን! እኔን፡ ለመገናኘት፡ፈጥነሽ፡ባልመጣሽ፡ኖሮ፡እስኪነጋ፡ድረስ፡ለናባል፡አንድ፡ወንድ፡ስንኳ፡ባልቀረውም፡ነበር።
35ዳዊትም፡ያመጣችውን፡ከእጇ፡ተቀብሎ፦በደኅና፡ወደ፡ቤትሽ፡ኺጂ፤እንሆ፥ቃልሽን፡ ሰማኹ፥ፊትሽንም፡አከበርኹ፡አላት።
36አቢግያም፡ወደ፡ናባል፡መጣች፤እንሆም፥በቤቱ፡እንደ፡ንጉሥ፡ግብዣ፡ያለ፡ግብዣ፡ያደርግ፡ ነበር፤ናባልም፡እጅግ፡ሰክሮ፡ነበርና፥ልቡ፡ደስ፡ብሎት፡ነበር፤ስለዚህም፡እስኪነጋ፡ድረስ፡ታናሽ፡ነገር፡ ወይም፡ታላቅ፡ነገር፡አልነገረችውም፡ነበር።
37በነጋውም፡የጠጁ፡ስካር፡ከናባል፡ባለፈ፡ጊዜ፡ሚስቱ፡ይህን፡ነገር፡ነገረችው፤ልቡም፡በውስጡ፡ሞተ፥
38እንደ፡ድንጋይም፡ኾነ፤ከዐሥር፡ቀንም፡በዃላ፡እግዚአብሔር፡ናባልን፡ቀሠፈው፥ርሱም፡ሞተ።
39ዳዊትም፡ናባል፡እንደ፡ሞተ፡በሰማ፡ጊዜ፦ከናባል፡እጅ፡የስድቤን፡ፍርድ፡የፈረደልኝ፥ባሪያውንም፡ ከክፋት፡የጠበቀ፡እግዚአብሔር፡ይመስገን፤እግዚአብሔርም፡የናባልን፡ክፋት፡በራሱ፡ላይ፡መለሰ፡ አለ።ዳዊትም፡ልኮ፡ያገባት፡ዘንድ፡አቢግያን፡ተነጋገራት።
40የዳዊትም፡ባሪያዎች፡ወደ፡ቀርሜሎስ፡ወደ፡አቢግያ፡በመጡ፡ጊዜ፦ዳዊት፡ያገባሽ፡ዘንድ፡ወደ፡አንቺ፡ ልኮናል፡ብለው፡ነገሯት።
41ተነሥታም፡በግንባሯ፡ወድቃ፡እጅ፡ነሣችና፦እንሆ፥እኔ፡ገረድኽ፡የጌታዬን፡ሎሌዎች፡እግር፡ዐጥብ፡ ዘንድ፡አገልጋይ፡ነኝ፡አለች።
42አቢግያም፡ፈጥና፡ተነሣች፤በአህያም፡ላይ፡ተቀመጠች፥ዐምስቱም፡ገረዶቿ፡ተከተሏት፤የዳዊትንም፡ መልእክተኛዎች፡ተከትላ፡ኼደች፥ሚስትም፡ኾነችው።
43ዳዊትም፡ደግሞ፡ኢይዝራኤላዊቱን፡አኪናሖምን፡ወሰደ፤ኹለቱም፡ሚስቶች፡ኾኑለት።
44ሳኦል፡ግን፡የዳዊትን፡ሚስት፡ልጁን፡ሜልኮልን፡አገሩ፡ጋሊም፡ለነበረው፡ለሌሳ፡ልጅ፡ለፈልጢ፡ሰጥቶ፡ ነበር። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org