1የዚፍ፡ሰዎችም፡ወደ፡ጊብዓ፡ወደ፡ሳኦል፡መጥተው፦እንሆ፥ዳዊት፡በየሴሞን፡ፊት፡ለፊት፡ባለው፡ በኤኬላ፡ኰረብታ፡ላይ፡ተሸሽጓል፡አሉት።
2ሳኦልም፡ተነሥቶ፡ዳዊትን፡በዚፍ፡ምድረ፡በዳ፡ይሻ፡ዘንድ፡ከእስራኤል፡የተመረጡ፡ሦስት፡ሺሕ፡ሰዎች፡ ይዞ፡ወደዚፍ፡ምድረ፡በዳ፡ወረደ።
3ሳኦልም፡በየሴሞን፡ፊት፡ለፊት፡ባለው፡በኤኬላ፡ኰረብታ፡ላይ፡በመንገዱ፡አጠገብ፡ሰፈረ።ዳዊትም፡ በምድረ፡በዳ፡ውስጥ፡ተቀምጦ፡ነበር፥ሳኦልም፡በስተዃላው፡ወደ፡ምድረ፡በዳ፡እንደ፡መጣ፡አየ።
4ዳዊትም፡ሰላዮች፡ሰደደ፥ሳኦልም፡ወደዚህ፡እንደ፡መጣ፡በርግጥ፡ዐወቀ።
5ዳዊትም፡ተነሥቶ፡ሳኦል፡ወደሰፈረበት፡ቦታ፡መጣ፤ሳኦልና፡የሰራዊቱ፡አለቃ፡የኔር፡ልጅ፡አበኔርም፡ የተኙበትን፡ስፍራ፡አየ፤ሳኦልም፡በሰፈሩ፡ውስጥ፡ተኝቶ፡ነበር፤ሕዝቡም፡በዙሪያው፡ሰፍሮ፡ነበር።
6ዳዊትም፡ኬጢያዊውን፡አቢሜሌክ ንና፡የጽሩያን፡ልጅ፡የኢዮአብ ን፡ወንድም፡አቢሳን፦ወደ፡ሳኦል፡ ወደ፡ሰፈሩ፡ከእኔ፡ጋራ፡የሚወርድ፡ማን፡ነው፧ብሎ፡ጠየቃቸው፤አቢሳም፦እኔ፡ከአንተ፡ጋራ፡እወርዳለኹ፡ አለ።
7ዳዊትና፡አቢሳም፡ወደ፡ሕዝቡ፡በሌሊት፡መጡ፤እንሆም፥ሳኦል፡ጦሩ፡በራሱ፡አጠገብ፡በምድር፡ተተክሎ፡ በሰፈሩ፡ውስጥ፡ተኝቶ፡ነበር፤አበኔርና፡ሕዝቡም፡በዙሪያው፡ተኝተው፡ነበር።
8አቢሳም፡ዳዊትን፦ዛሬ፡እግዚአብሔር፡ጠላትኽን፡በእጅኽ፡አሳልፎ፡ሰጥቶታል፤አኹንም፡እኔ፡በጦር፡ አንድ፡ጊዜ፡ከምድር፡ጋራ፡ላጣብቀው፥ኹለተኛም፡አያዳግምም፡አለው።
9ዳዊትም፡አቢሳን፦እግዚአብሔር፡በቀባው፡ላይ፡እጁን፡የሚዘረጋ፡ንጹሕ፡አይኾንምና፡አትግደለው፡አለው።
10ደግሞም፡ዳዊት፦ሕያው፡እግዚአብሔርን! እግዚአብሔር፡ይመታዋል፥ወይም፡ቀኑ፡ደርሶ፡ ይሞታል፥ወይም፡ወደ፡ሰልፍ፡ወርዶ፡ይገደላል፤
11እኔ፡ግን፡እግዚአብሔር፡በቀባው፡ላይ፡እጄን፡እዘረጋ፡ዘንድ፡እግዚአብሔር፡ከእኔ፡ያርቀው፤አኹንም፡ በራሱ፡አጠገብ፡ያለውን፡ጦርና፡የውሃውን፡መንቀል፡ይዘኽ፡እንኺድ፡አለ።
12ዳዊትም፡በሳኦል፡ራስ፡አጠገብ፡የነበረውን፡ጦርና፡የውሃውን፡መንቀል፡ወሰደ፤ማንም፡ሳያይ፡ሳያውቅም፡ ኼዱ፤ከእግዚአብሔርም፡ዘንድ፡ከባድ፡እንቅልፍ፡ወድቆባቸው፡ነበርና፥ዅሉ፡ተኝተው፡ነበር፡እንጂ፡የነቃ፡ አልነበረም።
13ዳዊትም፡ወደዚያ፡ተሻገረ፤በተራራውም፡ራስ፡ላይ፡ርቆ፡ቆመ፤በመካከላቸውም፡ሰፊ፡ስፍራ፡ነበረ።
14ዳዊትም፡ለሕዝቡና፡ለኔር፡ልጅ፡ለአበኔር፦አበኔር፡ሆይ፥አትመልስምን፧ብሎ፡ጮኸ።አበኔርም፡መልሶ፡ ለንጉሡ፦የምትጮኸው፡አንተ፡ማን፡ነኽ፧አለ።
15ዳዊትም፡አበኔርን፦አንተ፡ጕልማሳ፡አይደለኽምን፧በእስራኤል፡ዘንድ፡አንተን፡የሚመስል፡ማን፡ ነው፧ጌታኽን፡ንጉሡን፡ለመግደል፡አንድ፡ሰው፡ገብቶ፡ነበርና፥ጌታኽን፡ንጉሡን፡የማትጠብቅ፡ስለ፡ምን፡ ነው፧
16ይህ፡ያደረግኸው፡ነገር፡መልካም፡አይደለም፤ሕያው፡እግዚአብሔርን! እናንተ፡እግዚአብሔር፡የቀባውን፡ ጌታችኹን፡አልጠበቃችኹምና፥ሞት፡ይገ፟ባ፟ችዃል፤አኹንም፡የንጉሡ፡ጦርና፡በራሱ፡አጠገብ፡የነበረው፡ የውሃው፡መንቀል፡የት፡እንደ፡ኾነ፡ተመልከት፡አለው።
17ሳኦልም፡የዳዊት፡ድምፅ፡እንደ፡ኾነ፡ዐውቆ፦ልጄ፡ዳዊት፡ሆይ፥ይህ፡ድምፅኽ፡ ነውን፧አለው።ዳዊትም፦ጌታዬ፡ንጉሥ፡ሆይ፥ድምፄ፡ነው፡አለው። 143 ዕብ.፥አኂመለክ፡(የንጉሥ፡ወንድም)። 144 ዕብ.፥የውአብ፡(አምላክ፡አባቱ)። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org
18ደግሞ፡አለ፦ጌታዬ፡ባሪያውን፡ስለ፡ምን፡ያሳድዳል፧ምን፡አደረግኹ፧ምንስ፡ክፋት፡በእጄ፡ላይ፡ ተገኘብኝ፧
19አኹንም፡ጌታዬ፡ንጉሥ፡ሆይ፥የእኔን፡የባሪያኽን፡ቃል፡ትሰማ፡ዘንድ፡እለምንኻለኹ፤እግዚአብሔር፡ በእኔ፡ላይ፡አስነሥቶኽ፡እንደ፡ኾነ፥ቍርባንን፡ይቀበል፤የሰው፡ልጆች፡ግን፡ቢኾኑ፦ኺድ፡ሌላዎችን፡ አማልክት፡አምልክ፡ብለው፡በእግዚአብሔር፡ርስት፡ላይ፡እንዳልቀመጥ፡ዛሬ፡ጥለውኛልና፥በእግዚአብሔር፡ ፊት፡ርጉማን፡ይኹኑ።
20አኹንም፡በተራራው፡ላይ፡ሰው፡ቆቅን፡እንደሚሻ፡የእስራኤል፡ንጉሥ፡ነፍሴን፡ለመሻት፡ ወጥቷልና፥ደሜ፡ከእግዚአብሔር፡ፊት፡ርቆ፡በምድር፡ላይ፡አይፍሰስ።
21ሳኦልም፦በድያለኹ፤ልጄ፡ሆይ፡ዳዊት፥ተመለስ፤ዛሬ፡ነፍሴ፡በዐይንኽ፡ፊት፡ከብራለችና፡ከዚህ፡ በዃላ፡ክፉ፡አላደርግብኽም፥እንሆ፥ስንፍና፡አድርጌያለኹ፥እጅግ፡ብዙም፡ስቻለኹ፡አለ።
22ዳዊትም፡መልሶ፡አለ፦የንጉሥ፡ጦር፥እንሆ፥ከብላቴናዎችም፡አንድ፡ይምጣና፡ይውሰዳት።
23ዛሬም፡እግዚአብሔር፡በእጄ፡አሳልፎ፡ሰጥቶኽ፡ሳለ፡እግዚአብሔር፡በቀባው፡ላይ፡እጄን፡እዘረጋ፡ዘንድ፡ አልወደድኹምና፡ለዅሉ፡እያንዳንዱ፡እግዚአብሔር፡እንደ፡ጽድቁና፡እንደ፡እምነቱ፡ፍዳውን፡ይክፈለው።
24ነፍስኽም፡ዛሬ፡በዐይኔ፡ፊት፡እንደ፡ከበረች፡እንዲሁ፡ነፍሴ፡በእግዚአብሔር፡ዐይን፡ፊት፡ ትክበር፥ከመከራም፡ዅሉ፡ያድነኝ።
25ሳኦል፡ዳዊትን፦ልጄ፡ዳዊት፡ሆይ፥ቡሩክ፡ኹን፤ማድረግን፡ታደርጋለኽ፥መቻልንም፡ትችላለኽ፡ አለው።ዳዊትም፡መንገዱን፡ኼደ፥ሳኦልም፡ወደ፡ስፍራው፡ተመለሰ።