Skip to content
← 1 Samuel

Chapter 27 · Amharic

1 Samuel

1ዳዊትም፡በልቡ።አንድ፡ቀን፡በሳኦል፡እጅ፡እጠፋለኹ፤ወደፍልስጥኤማውያንም፡ምድር፡ከመሸሽ፡በቀር፡ የሚሻለኝ፡የለም፤ሳኦልም፡በእስራኤል፡አውራጃ፡ዅሉ፡እኔን፡መሻት፡ይተዋል፥እንዲሁም፡ከእጁ፡እድናለኹ፡ አለ።

2ዳዊትም፡ከርሱም፡ጋራ፡የነበሩት፡ስድስቱ፡መቶ፡ሰዎች፡ተነሥተው፡ወደጌት፡ንጉሥ፡ወደአሜኽ፡ (ወደማዖክ)፡ልጅ፡ወደ፡አንኩስ፡ዐለፉ።

3ዳዊትና፡ሰዎቹም፡እያንዳንዳቸው፡ከነ፡ቤተ፡ሰቡ፡ከአንኩስ፡ጋራ፡በጌት፡ውስጥ፡ተቀመጡ፤ከዳዊትም፡ ጋራ፡ኢይዝራኤላዊቱ፡አኪናሖምና፡የቀርሜሎሳዊው፡የናባል፡ሚስት፡አቢግያ፡ኹለቱ፡ሚስቶቹ፡ነበሩ።

4ሳኦልም፡ዳዊት፡ወደ፡ጌት፡እንደ፡ኰበለለ፡ሰማ፤ከዚያም፡በዃላ፡ደግሞ፡አልፈለገውም።

5ዳዊትም፡አንኩስን፦በዐይንኽ፡ፊት፡ሞገስ፡አግኝቼ፡እንደ፡ኾነ፡በዚህ፡አገር፡በአንዲቱ፡ከተማ፡ የምቀመጥበት፡ስፍራ፡ስጠኝ፤ስለ፡ምን፡እኔ፡ባሪያኽ፡ከአንተ፡ጋራ፡በንጉሥ፡ከተማ፡እቀመጣለኹ፧አለው።

6በዚያም፡ቀን፡አንኩስ፡ጺቅላግን፡ሰጠው፤ስለዚህም፡ጺቅላግ፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡ለይሁዳ፡ነገሥታት፡ ኾነች።

7ዳዊትም፡በፍልስጥኤማውያን፡አገር፡የተቀመጠበት፡የዘመን፡ቍጥር፡አንድ፡ዓመት፡ከአራት፡ወር፡ነበረ።

8ዳዊትና፡ሰዎቹም፡ወጥተው፡በጌሹራውያንና፡በጌርዛውያን፡በዐማሌቃውያንም፡ላይ፡ዘመቱ፤እነዚህም፡እስከ፡ ሱር፡እስከ፡ግብጽ፡ምድር፡ድረስ፡ባለው፡አገር፡ድሮውኑ፡ተቀምጠው፡ነበር።

9ዳዊትም፡ምድሪቱን፡መታ፤ወንድ፡ኾነ፡ሴትም፡ኾነ፡ማንንም፡በሕይወት፡አልተወም፤በጎችንና፡ላሞችን፡ አህያዎችንና፡ግመሎችን፡ልብስንም፡ማረከ፥ተመልሶም፡ወደ፡አንኩስ፡መጣ።

10አንኩስም፦ዛሬ፡በማን፡ላይ፡ዘመታችኹ፧አለ፤ዳዊትም፦በይሁዳ፡ደቡብ፥በይረሕምኤላውያንም፡ ደቡብ፥በቄናውያንም፡ደቡብ፡ላይ፡ዘመትን፡አለ። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

11ዳዊት፡እንዲህ፡አደረገ፡በፍልስጥኤማውያንም፡አገር፡በሚቀመጥበት፡ዘመን፡ዅሉ፡ልማዱ፡ይህ፡ነበረ፡ ብለው፡እንዳይናገሩብን፡ብሎ፡ዳዊት፡ወደ፡ጌት፡ያመጣቸው፡ዘንድ፡ወንድም፡ኾነ፡ሴትም፡ኾነ፡ማንንም፡ በሕይወት፡አልተወም።

12አንኩስም፦በሕዝቡ፡በእስራኤል፡ዘንድ፡እጅግ፡የተጠላ፡ኾኗል፤ስለዚህም፡ለዘለዓለም፡ባሪያ፡ይኾነኛል፡ ብሎ፡ዳዊትን፡አመነው።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source