Skip to content
← 1 Samuel

Chapter 4 · Amharic

1 Samuel

1እስራኤልም፡ከፍልስጥኤማውያን፡ጋራ፡ሊዋጋ፡ወጡ፥በአቤንዔዘር ፡አጠገብ፡ሰፈሩ፤ፍልስጥኤማውያን፡ በአፌቅ፡ሰፈሩ።

2ፍልስጥኤማውያንም፡በእስራኤል፡ላይ፡ተሰለፉ፤ሰልፉም፡በተመደበ፡ጊዜ፡እስራኤል፡በፍልስጥኤማውያን፡ ፊት፡ተመቱ፤ጦርነት፡በተደረገበትም፡ስፍራ፡ከእስራኤል፡አራት፡ሺሕ፡የሚያኽሉ፡ሰዎችን፡ገደሉ።

3ሕዝቡም፡ወደ፡ሰፈር፡በመጡ፡ጊዜ፡የእስራኤል፡ሽማግሌዎች።ዛሬ፡እግዚአብሔር፡በፍልስጥኤማውያን፡ ፊት፡ስለ፡ምን፡መታን፧በመካከላችን፡እንዲኼዱ፥ከጠላቶቻችንም፡እጅ፡እንዲያድነን፥የእግዚአብሔርን፡ የቃል፡ኪዳኑን፡ታቦት፡ከሴሎ፡እናምጣ፡አሉ።

4ሕዝቡም፡ወደ፡ሴሎ፡ላኩ፥በኪሩቤልም፡ላይ፡የሚቀመጠውን፡የሰራዊት፡ጌታ፡የእግዚአብሔርን፡የቃል፡ ኪዳኑን፡ታቦት፡ከዚያ፡አመጡ፤ኹለቱም፡የዔሊ፡ልጆች፡አፍኒንና፡ፊንሐስ፡ከእግዚአብሔር፡ቃል፡ኪዳን፡ ታቦት፡ጋራ፡በዚያ፡ነበሩ።

5የእግዚአብሔር፡የቃል፡ኪዳን፡ታቦት፡ወደ፡ሰፈር፡በገባ፡ጊዜ፡እስራኤል፡ዅሉ፡ታላቅ፡እልልታ፡ አደረጉ፥ምድሪቱም፡አስተጋባች።

6ፍልስጥኤማውያንም፡የእልልታውን፡ድምፅ፡በሰሙ፡ጊዜ፦በዕብራውያን፡ሰፈር፡ያለው፡ይህ፡ታላቅ፡ የእልልታ፡ድምፅ፡ምንድር፡ነው፧አሉ።የእግዚአብሔርም፡ታቦት፡ወደ፡ሰፈሩ፡እንደ፡ገባ፡አስተዋሉ። 134 ዕብ.፥ኤቤንዔዜር፡(እብን፡ዐዘር፥ረዳት፡ድንጋይ)። http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org

7ፍልስጥኤማውያንም፡ፈርተው፦እግዚአብሔር፡ወደ፡ሰፈር፡መጥቷል፡አሉ።ደግሞም፡እንዲህ፡ አሉ፦ወዮልን፤ከዚህ፡አስቀድሞ፡እንዲህ፡ያለ፡ነገር፡አልኾነም።

8ወዮልን፤ከነዚህ፡ከኀያላን፡አማልክት፡እጅ፡ማን፡ያድነናል፧እነዚህ፡አማልክት፡ግብጻውያንን፡በምድረ፡ በዳ፡በልዩ፡በልዩ፡መቅሠፍት፡የመቱ፡ናቸው።

9እናንተ፡ፍልስጥኤማውያን፡ሆይ፥አይዟችኹ፥ጐብዙ፤እናንተ፡ባሪያዎች፡እንዳደረጋችዃቸው፡ዕብራውያን፡ ባሪያዎች፡እንዳያደርጓችኹ፡ጐብዙ፥ተዋጉ።

10ፍልስጥኤማውያንም፡ተዋጉ፤እስራኤልም፡ተመቱ፥ዅሉም፡እያንዳንዱ፡ወደ፡ድንኳናቸው፡ሸሹ፤እጅግም፡ ታላቅ፡ግድያ፡ኾነ፥ከእስራኤልም፡ሠላሳ፡ሺሕ፡እግረኛዎች፡ወደቁ።

11የእግዚአብሔርም፡ታቦት፡ተማረከች፥ኹለቱም፡የዔሊ፡ልጆች፡አፍኒንና፡ፊንሐስ፡ሞቱ።

12በዚያም፡ቀን፡አንድ፡የብንያም፡ሰው፡ከሰልፍ፡እየበረረ፡ልብሱን፡ቀዶ፟፡በራሱም፡ላይ፡ትቢያ፡ነስንሶ፡ ወደ፡ሴሎ፡መጣ።

13በመጣም፡ጊዜ፡ዔሊ፡ስለእግዚአብሔር፡ታቦት፡ልቡ፡ተናውጦ፡ነበርና፥በመንገድ፡ዳር፡በወንበሩ፡ላይ፡ ተቀምጦ፡ይጠባበቅ፡ነበር፤ሰውዮውም፡ወደ፡ከተማዪቱ፡ገብቶ፡ባወራ፡ጊዜ፡ከተማዪቱ፡ዅሉ፡ተጯጯኸች።

14ዔሊም፡የጩኸቱን፡ድምፅ፡በሰማ፡ጊዜ፦ይህ፡ጫጫታ፡ምንድር፡ነው፧አለ።ሰውዮውም፡ፈጥኖ፡ መጣና፡ለዔሊ፡ነገረው።

15ዔሊም፡የዘጠና፡ስምንት፡ዓመት፡ሽማግሌ፡ነበረ፤ዐይኖቹም፡ማየት፡እስኪሳናቸው፡ድረስ፡ፈዘ፟ው፡ነበር።

16ሰውዮውም፡ዔሊን፦ከሰልፍ፡የመጣኹ፡እኔ፡ነኝ፥ዛሬም፡ከሰልፍ፡ኰበለልኹ፡አለ።ርሱም፦ልጄ፡ ሆይ፥ነገሩሳ፡እንዴት፡ኾነ፧አለው።

17ወሬኛውም፡መልሶ፦እስራኤል፡ከፍልስጥኤማውያን፡ፊት፡ሸሹ፤ደግሞ፡በሕዝቡ፡ዘንድ፡ታላቅ፡ግድያ፡ ኾኗል፥ኹለቱም፡ልጆችኽ፡አፍኒንና፡ፊንሐስ፡ሞተዋል፤የእግዚአብሔርም፡ታቦት፡ተማርካለች፡አለ።

18ሰውዮውም፡ስለእግዚአብሔር፡ታቦት፡በተናገረ፡ጊዜ፡ዔሊ፡በበሩ፡አጠገብ፡ካለው፡ከወንበሩ፡ወደቀ፤ርሱ፡ ሸምግሎ፡ደንግዞም፡ነበርና፥ዐንገቱ፡ተሰብሮ፡ሞተ።ርሱም፡በእስራኤል፡ላይ፡አርባ፡ዓመት፡ፈራጅ፡ነበረ።

19ምራቱም፡የፊንሐስ፡ሚስት፡አርግዛ፡ልትወልድ፡ተቃርባ፡ነበር፤የእግዚአብሔርም፡ታቦት፡እንደ፡ ተማረከች፥አማቷና፡ባሏም፡እንደ፡ሞቱ፡በሰማች፡ጊዜ፡ምጥ፡ደርሶባት፡ነበርና፥ተንበርክካ፡ወለደች።

20ወደ፡ሞትም፡በቀረበች፡ጊዜ፡በዙሪያዋ፡ያሉት፡ሴቶች፦ወንድ፡ልጅ፡ወልደሻልና፥አትፍሪ፡አሏት።ርሷ፡ ግን፡አልመለሰችላቸውም፥በልቧም፡አላኖረችውም።

21ርሷም፡የእግዚአብሔር፡ታቦት፡ስለ፡ተማረከች፡ስለ፡አማቷና፡ስለ፡ባሏም፦ክብር፡ከእስራኤል፡ለቀቀ፡ ስትል፡የሕፃኑን፡ስም፦ኢካቦድ፡ብላ፡ጠራችው።

22ርሷም፦የእግዚአብሔር፡ታቦት፡ተማርካለችና፡ክብር፡ከእስራኤል፡ለቀቀ፡አለች።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source