Skip to content
← 1 Samuel

Chapter 5 · Amharic

1 Samuel

1ፍልስጥኤማውያንም፡የእግዚአብሔርን፡ታቦት፡ወሰዱ፤ከአቤንዔዘርም፡ወደ፡አዛጦን፡ይዘውት፡መጡ።

2ፍልስጥኤማውያንም፡የእግዚአብሔርን፡ታቦት፡ወስደው፡ወደዳጎን፡ቤት፡አገቡት፥በዳጎንም፡አጠገብ፡ አኖሩት።

3በነጋውም፡የአዛጦን፡ሰዎች፡ማለዱ፥እንሆም፥ዳጎን፡በእግዚአብሔር፡ታቦት፡ፊት፡በምድር፡ላይ፡በግንባሩ፡ ወድቆ፡ነበር፤ዳጎንንም፡አንሥተው፡ወደ፡ስፍራው፡መለሱት።

4በነጋውም፡ማለዱ፥እንሆም፥ዳጎን፡በእግዚአብሔር፡ታቦት፡ፊት፡በምድር፡ላይ፡በግንባሩ፡ወድቆ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ነበር፤የዳጎንም፡ራስ፡እጆቹም፡ተቈርጠው፡በመድረኩ፡ላይ፡ወድቀው፡ነበር፤የዳጎንም፡ደረት፡ብቻውን፡ ቀርቶ፡ነበር።

5ስለዚህም፡የዳጎን፡ካህናት፡ወደዳጎንም፡ቤት፡የሚገቡት፡ዅሉ፡በአዛጦን፡ያለውን፡የዳጎንን፡መድረክ፡እስከ፡ ዛሬ፡ድረስ፡አይረግጡም።

6የእግዚአብሔርም፡እጅ፡በአዛጦን፡ሰዎች፡ላይ፡ከበደች፥አጠፋቸውም፥አዛጦንንና፡ድንበራቸውንም፡በዕባጭ፡ መታቸው።

7የአዛጦንም፡ሰዎች፡እንዲህ፡እንደ፡ኾነ፡ባዩ፡ጊዜ፦እጁ፡በእኛና፡በአምላካችን፡በዳጎን፡ላይ፡ ጠንክራለችና፡የእስራኤል፡አምላክ፡ታቦት፡ከእኛ፡ዘንድ፡አይቀመጥ፡አሉ።

8ልከውም፡የፍልስጥኤማውያንን፡አለቃዎች፡ዅሉ፡ወደ፡እነርሱ፡ሰበሰቡና፦በእስራኤል፡አምላክ፡ታቦት፡ምን፡ እናድርግ፧አሉ፤እነርሱም፦የእስራኤል፡አምላክ፡ታቦት፡ወደ፡ጌት፡ይዙር፡ብለው፡መለሱ።የእስራኤልንም፡ አምላክ፡ታቦት፡ወደዚያ፡ተሸከሙት።

9ከተሸከሙትም፡በዃላ፡የእግዚአብሔር፡እጅ፡በታላቅ፡ድንጋጤ፡በከተማዪቱ፡ላይ፡ኾነች፤ከታናሹም፡እስከ፡ ታላቁ፡ድረስ፡የከተማዪቱን፡ሰዎች፡መታ፥ዕባጭም፡መጣባቸው።

10የእግዚአብሔርንም፡ታቦት፡ወደ፡አስቀሎና፡ሰደዱት።የእግዚአብሔር፡ታቦት፡ወደ፡አስቀሎና፡በመጣ፡ጊዜ፡ አስቀሎናውያን፦እኛንና፡ሕዝባችንን፡ሊገድሉ፡የእስራኤልን፡አምላክ፡ታቦት፡አመጡብን፡ብለው፡ጮኹ።

11በከተማዪቱ፡ዅሉ፡የሞት፡ድንጋጤ፡ነበርና፥የእግዚአብሔርም፡እጅ፡በዚያ፡እጅግ፡ከብዳ፡ነበርና፥ልከው፡ የፍልስጥኤማውያንን፡አለቃዎች፡ዅሉ፡ሰብስበው፦የእስራኤልን፡አምላክ፡ታቦት፡ስደዱ፥እኛንና፡ሕዝባችንን፡ እንዳይገድል፡ወደ፡ስፍራው፡ይመለስ፡አሉ።

12ያልሞቱትም፡ሰዎች፡በዕባጭ፡ተመቱ፤የከተማዪቱም፡ዋይታ፡እስከ፡ሰማይ፡ወጣ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source