1የእግዚአብሔር፡ታቦት፡በፍልስጥኤማውያን፡አገር፡ሰባት፡ወር፡ተቀመጠ።
2ፍልስጥኤማውያንም፡ካህናትንና፡ሟርተኛዎችን፡ጠርተው፦በእግዚአብሔር፡ታቦት፡ላይ፡ምን፡ እናድርግ፧ወደ፡ስፍራውስ፡በምን፡እንስደደው፧አስታውቁን፡አሉ።
3እነርሱም፦የእስራኤልን፡አምላክ፡ታቦት፡ብትሰዱ፟፡የበደል፡መሥዋዕት፡መልሱለት፡እንጂ፡ባዶውን፡ አትስደዱት፥የዚያን፡ጊዜም፡ትፈወሳላችኹ፤እጁም፡ከእናንተ፡አለመራቁ፡ስለ፡ምን፡እንደ፡ኾነ፡ታውቃላችኹ፡ አሉ።
4እነርሱም፦ስለ፡በደል፡መሥዋዕት፡የምንመልስለት፡ምንድር፡ነው፧አሉ።እነርሱም፡እንዲህ፡ አሉ፦እናንተንና፡አለቃዎቻችኹን፡ያገኘች፡መቅሠፍት፡አንዲት፡ናትና፥እንደ፡ፍልስጥኤማውያን፡አለቃዎች፡ ቍጥር፡ዐምስት፡የወርቅ፡ዕባጮች፡ዐምስትም፡የወርቅ፡ዐይጦች፡አቅርቡ።
5የዕባጫችኹንም፡ምሳሌ፥ምድራችኹንም፡የሚያጠፉትን፡የዐይጦችን፡ምሳሌ፡አድርጋችኹ፡ለእስራኤል፡ አምላክ፡ክብርን፡ስጡ፤እጁን፡ከእናንተና፡ከአማልክታችኹ፡ከምድራችኹም፡ምናልባት፡ያቀል፟፡ይኾናል።
6ግብጻውያንና፡ፈርዖንም፡ልባቸውን፡እንዳጸኑ፡ልባችኹን፡ለምን፡ታጸናላችኹ፧እግዚአብሔር፡ኀይሉን፡ ካደረገባቸው፡በዃላ፡ያወጧቸው፡አይደሉምን፧
7እነርሱም፡አልኼዱምን፧አኹንም፡ወስዳችኹ፡አንዲት፡ሠረገላ፡ሥሩ፤የሚያጠቡም፥ቀንበር፡ ያልተጫነባቸውን፡ኹለት፡ላሞች፡በሠረገላ፡ጥመዷቸው፥እንቦሶቻቸውንም፡ለይታችኹ፡ወደ፡ቤት፡መልሷቸው።
8የእግዚአብሔርንም፡ታቦት፡ወስዳችኹ፡በሠረገላው፡ላይ፡አኑሩት፤ስለ፡በደልም፡መሥዋዕት፡ ያቀረባችኹትን፡የወርቁን፡ዕቃ፡በሣጥን፡ውስጥ፡አድርጋችኹ፡በታቦቱ፡አጠገብ፡አኑሩት፤ይኼድም፡ዘንድ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ስደዱት።
9ተመልከቱም፡በድንበሩም፡መንገድ፡ወደ፡ቤትሳሚስ፡ቢወጣ፡ይህን፡እጅግ፡ክፉ፡ነገር፡ያደረገብን፡ እግዚአብሔር፡ነው፤አለዚያም፡እንዲያው፡መጥቶብናል፡እንጂ፡የመታን፡የርሱ፡እጅ፡እንዳልኾነ፡እናውቃለን።
10ሰዎቹም፡እንዲሁ፡አደረጉ፤የሚያጠቡትን፡ኹለቱን፡ላሞች፡ወሰዱ፥በሠረገላም፡ ጠመዷቸው፥እንቦሶቻቸውንም፡በቤት፡ዘጉባቸው፤
11የእግዚአብሔርም፡ታቦት፥የወርቁ፡ዐይጦችና፡የዕባጮቻቸው፡ምሳሌ፡ያሉበትንም፡ሣጥን፡በሠረገላው፡ላይ፡ ጫኑ።
12ላሞችም፡ወደ፡ቤትሳሚስ፡ወደሚወስደው፡መንገድ፡አቅንተው፡እምቧ፡እያሉ፡በጐዳናው፡ላይ፡ ኼዱ፥ወደ፡ቀኝም፡ወደ፡ግራም፡አላሉም፤የፍልስጥኤማውያንም፡አለቃዎች፡እስከ፡ቤትሳሚስ፡ዳርቻ፡ድረስ፡ በዃላ፡በዃላቸው፡ይኼዱ፡ነበር።
13የቤትሳሚስ፡ሰዎችም፡በሸለቆው፡ውስጥ፡ስንዴ፡ያጭዱ፡ነበር፤ዐይናቸውንም፡ከፍ፡አድርገው፡ታቦቱን፡ አዩ፥በማየታቸውም፡ደስ፡አላቸው።
14ሠረገላውም፡ወደ፡ቤትሳሚሳዊው፡ወደኢያሱ፡ዕርሻ፡መጣ፥ታላቅም፡ድንጋይ፡በነበረበት፡በዚያ፡ ቆመ፤የሠረገላውንም፡ዕንጨት፡ፈልጠው፡ላሞቹን፡ለእግዚአብሔር፡ለሚቃጠል፡መሥዋዕት፡አቀረቡ።
15ሌዋውያንም፡የእግዚአብሔርን፡ታቦት፥ከርሱ፡ጋራ፡የነበረውንም፡የወርቅ፡ዕቃ፡ያለበትን፡ሣጥን፡ አወረዱ፥በታላቁም፡ድንጋይ፡ላይ፡አኖሩት፤በዚያም፡ቀን፡የቤትሳሚስ፡ሰዎች፡ለእግዚአብሔር፡የሚቃጠለውን፡ መሥዋዕት፡አቀረቡ፥መሥዋዕትንም፡ሠዉ።
16ፍልስጥኤማውያንም፡ዐምስቱ፡አለቃዎች፡ባዩት፡ጊዜ፡በዚያው፡ቀን፡ወደ፡አስቀሎና፡ተመለሱ።
17ፍልስጥኤማውያን፡ስለ፡በደል፡መሥዋዕት፡ለእግዚአብሔር፡ያቀረቧቸው፡የወርቅ፡ዕባጮች፡እነዚህ፡ ናቸው፤አንዲቱ፡ለአዛጦን፥አንዲቱም፡ለጋዛ፥አንዲቱም፡ለአስቀሎና፥አንዲቱ፡ለጌት፥
18አንዲቱ፡ለዐቃሮን፡የወርቁም፡ዐይጦች፡ቍጥር፡ለዐምስቱ፡የፍልስጥኤማውያን፡አለቃዎች፡እንደ፡ነበሩት፡ ከተማዎች፡ዅሉ፡ቍጥር፡እንዲሁ፡ነበረ፤እነርሱም፡እስከ፡ታላቁ፡ድንጋይ፡የሚደርሱ፡ከተማዎችና፡መንደሮች፡ ናቸው።በዚህም፡ድንጋይ፡ላይ፡የእግዚአብሔርን፡ታቦት፡አስቀመጡ፥ድንጋዩም፡እስከ፡ዛሬ፡ድረስ፡ በቤትሳሚሳዊው፡በኢያሱ፡ዕርሻ፡አለ።
19ወደእግዚአብሔርም፡ታቦት፡ውስጥ፡ተመልክተዋልና፥የቤትሳሚስን፡ሰዎች፡መታ፤በሕዝቡም፡ከዐምስት፡ ሺሕ፡ሰው፡ሰባ፡ሰዎችን፡መታ፤እግዚአብሔርም፡ሕዝቡን፡በታላቅ፡ግዳይ፡ስለ፡መታ፡ሕዝቡ፡አለቀሰ።
20የቤትሳሚስም፡ሰዎች፦በዚህ፡በቅዱስ፡አምላክ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡መቆም፡ማን፡ይችላል፧ከእኛስ፡ ወጥቶ፡ወደ፡ማን፡ይኼዳል፧አሉ።
21በቂርያትይዓሪምም፡ወደተቀመጡት፡ሰዎች፡መልክተኛዎች፡ልከው፦ፍልስጥኤማውያን፡የእግዚአብሔርን፡ ታቦት፡መልሰዋል፤ወርዳችኹም፡ወደ፡እናንተ፡አውጡት፡አሉ።