1ሮብዓምም፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡በመጣ፡ጊዜ፡እስራኤልን፡ወግተው፡መንግሥቱን፡ወደ፡ሮብዓም፡ይመልሱ፡ ዘንድ፡ከይሁዳና፡ከብንያም፡ቤት፡የተመረጡትን፡አንድ፡መቶ፡ሰማንያ፡ሺሕ፡ሰልፈኛዎች፡ሰዎች፡ሰበሰበ።
2የእግዚአብሔርም፡ቃል፡ወደእግዚአብሔር፡ሰው፡ወደሸማያ፡እንዲህ፡ሲል፡መጣ፦
3ለይሁዳ፡ንጉሥ፡ለሰሎሞን፡ልጅ፡ለሮብዓም፥በይሁዳና፡በብንያምም፡ላሉት፡ለእስራኤል፡ዅሉ፦
4እግዚአብሔር፡እንዲህ፡ይላል፦ይህ፡ነገር፡ከእኔ፡ዘንድ፡ነውና፥አትውጡ፥ወንድሞቻችኹንም፡ አትውጉ፤እያንዳንዱም፡ወደ፡ቤቱ፡ይመለስ፡ብለኽ፡ንገራቸው።የእግዚአብሔርንም፡ቃል፡ ሰሙ፥በኢዮርብዓምም፡ላይ፡ከመኼድ፡ተመለሱ።
5ሮብዓምም፡በኢየሩሳሌም፡ተቀመጠ፥በይሁዳም፡የተመሸጉትን፡ከተማዎች፡ሠራ።
6በይሁዳና፡በብንያም፡ያሉትንም፡የተመሸጉትን፡ከተማዎች፥ቤተ፡ልሔም፥ኤጣምን፥ቴቁሔን፥
8ቤትጹርን፥ሦኮን፥ዓዶላምን፥ጌትን፥መሪሳን፥
9ዚፍን፥አዶራይምን፥ለኪሶን፥ዓዜቃን፥
10ጾርዓን፥ኤሎንን፥ኬብሮንን፥ሠራ።
11ምሽጎቹንም፡አጠነከረ፥አለቃዎችንም፡አኖረባቸው፥ምግቡንም፡ዘይቱንም፡የወይን፡ጠጁንም፡አከማቸባቸው።
12በከተማዎቹ፡ዅሉ፡ጋሻና፡ጦርን፡አኖረ።ከተማዎቹንም፡እጅግ፡አጠነከራቸው፤ይሁዳና፡ብንያምም፡የርሱ፡ ወገን፡ነበሩ።
13በእስራኤልም፡ዅሉ፡ዘንድ፡የነበሩ፡ካህናትና፡ሌዋውያን፡ከየአገራቸው፡ዅሉ፡ወደ፡ርሱ፡መጡ።
14የእግዚአብሔርም፡ካህናት፡እንዳይኾኑ፡ኢዮርብዓምና፡ልጆቹ፡አስለቅቀዋቸው፡ነበርና፥ሌዋውያን፡ መሰመሪያቸውንና፡ቦታቸውን፡ትተው፡ወደ፡ይሁዳና፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡መጡ።
15ርሱ፡ግን፡ለኰረብታው፡መስገጃዎች፡ለአጋንንቱም፡ለሠራቸውም፡እንቦሶች፡ካህናትን፡አቆመ።
16ደግሞም፡ለአባቶቻቸው፡አምላክ፡ለእግዚአብሔር፡ይሠዉ፡ዘንድ፡ከእስራኤል፡ነገድ፡ዅሉ፡የእስራኤልን፡ አምላክ፡እግዚአብሔርን፡ለመፈለግ፡ልባቸውን፡የሰጡ፡ዅሉ፡እነርሱን፡ተከትለው፡ወደ፡ኢየሩሳሌም፡መጡ።
17ሦስት፡ዓመት፡በዳዊትና፡በሰሎሞን፡መንገድ፡ይኼዱ፡ነበርና፥ሦስት፡ዓመት፡የይሁዳን፡መንግሥት፡ አበረቱ፥የሰሎሞንንም፡ልጅ፡ሮብዓምን፡አጸኑ።
18ሮብዓምም፡መሐላትን፡አገባ፤አባቷ፡የዳዊት፡ልጅ፡ኢያሪሙት፡ነበረ፤እናቷም፡የእሴይ፡ልጅ፡የኤልያብ፡ ልጅ፡አቢካኢል፡ነበረች።
19ርሷም፡የዑስን፥ሰማራያን፥ዘሃምን፡ወንዶች፡ልጆች፡ወለደችለት።
20ከርሷም፡በዃላ፡የአቤሴሎምን፡ልጅ፡መዓካን፡አገባ፤ርሷም፡አብያን፥ዐታይን፥ዚዛን፥ሰሎሚትን፡ ወለደችለት።
21ሮብዓምም፡ከሚስቶቹና፡ከቁባቶቹ፡ዅሉ፡ይልቅ፡የአቤሴሎምን፡ልጅ፡መዓካን፡ወደደ፤ዐሥራ፡ስምንትም፡ ሚስቶችና፡ስድሳ፡ቁባቶች፡ነበሩት፥ኻያ፡ስምንት፡ወንዶችና፡ስድሳ፡ሴቶች፡ልጆች፡ወለደ።
22ሮብዓምም፡ንጉሥ፡ያደርገው፡ዘንድ፡ዐስቧልና፥የመዓካን፡ልጅ፡አብያን፡በወንድሞቹ፡ላይ፡አለቃ፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org አድርጎ፡ሾመው።
23ተጠበበም፥ልጆቹንም፡ዅሉ፡በይሁዳና፡በብንያም፡አገር፡ዅሉ፡በምሽጉ፡ከተማዎች፡ዅሉ፡ ከፋፈላቸው፤ብዙም፡ምግብ፡ሰጣቸው፤ብዙም፡ሚስቶች፡ፈለገላቸው።