Skip to content
← 2 Chronicles

Chapter 13 · Amharic

2 Chronicles

1ንጉሡም፡ኢዮርብዓም፡በነገሠ፡በዐሥራ፡ስምንተኛው፡ዓመት፡አብያ፡በይሁዳ፡ላይ፡ንጉሥ፡ኾነ።

2ሦስት፡ዓመት፡በኢየሩሳሌም፡ነገሠ፤የእናቱም፡ስም፡ሚካያ፡ነበረ፥የገብዓ፡ሰው፡የኡርኤል፡ልጅ፡ነበረች።

3በአብያና፡በኢዮርብዓም፡መካከልም፡ሰልፍ፡ነበረ።አብያም፡የተመረጡትን፡አራት፡መቶ፡ሺሕ፡ኀያላን፡ ሰልፈኛዎች፡ይዞ፡ወደ፡ሰልፍ፡ወጣ፤ኢዮርብዓምም፡የተመረጡትን፡ስምንት፡መቶ፡ሺሕ፡ጽኑዓን፡ኀያላን፡ ሰዎች፡ይዞ፡በርሱ፡ላይ፡ተሰለፈ።

4አብያም፡በተራራማው፡በኤፍሬም፡አገር፡ባለው፡በጽማራይም፡ተራራ፡ላይ፡ቆሞ፡እንዲህ፡ አለ፦ኢዮርብዓምና፡እስራኤል፡ዅሉ፡ሆይ፥ስሙኝ፤

5የእስራኤል፡አምላክ፡እግዚአብሔር፡በእስራኤል፡ላይ፡መንግሥትን፡ለዳዊትና፡ለልጆቹ፡በጨው፡ቃል፡ ኪዳን፡ለዘለዓለም፡እንደ፡ሰጠ፡በእውኑ፡አታውቁምን፧

6የዳዊት፡ልጅ፡የሰሎሞን፡ባሪያ፡የናባጥ፡ልጅ፡ኢዮርብዓም፡ግን፡ተነሥቶ፡በጌታው፡ላይ፡ዐመፀ።

7ክፉዎች፡ሰዎችና፡ምናምንቴዎችም፡ወደ፡ርሱ፡ተሰበሰቡ፤ሮብዓም፡ሕፃንና፡ለጋ፡በነበረበት፡ ጊዜ፥ሊቋቋማቸውም፡ባልቻለበት፡ጊዜ፥በሰሎሞን፡ልጅ፡በሮብዓም፡ላይ፡በረቱበት።

8አኹንም፡በዳዊት፡ልጆች፡እጅ፡የሚኾነውን፡የእግዚአብሔርን፡መንግሥት፡ልትቋቋሙ፡ ታስባላችኹ።እናንተም፡እጅግ፡ታላቅ፡ሕዝብ፡ናችኹ፥ኢዮርብዓምም፡አማልክት፡አድርጎ፡የሠራላችኹ፡ የወርቅ፡እንቦሶች፡ከእናንተ፡ጋራ፡ናቸው።

9የአሮንን፡ልጆች፡የእግዚአብሔርን፡ካህናትና፡ሌዋውያን፡አላሳደዳችኹምን፧እንደ፡ሌላዎችም፡አሕዛብ፡ ልማድ፡ካህናትን፡አላደረጋችኹምን፧አንድ፡ወይፈንና፡ሰባት፡አውራ፡በጎች፡ይዞ፡ይቀድስ፡ዘንድ፡የሚመጣ፡ ዅሉ፡አማልክት፡ላልኾኑት፡ለእነዚያ፡ካህን፡ይኾናል።

10ለእኛ፡ግን፡አምላካችን፡እግዚአብሔር፡ነው፥አልተውነውም፤የእግዚአብሔርም፡አገልጋዮች፡የአሮን፡ ልጆች፡ካህናቱ፡ሌዋውያኑም፡በሥራቸው፡ከእኛ፡ጋራ፡ናቸው።

11በየጧቱና፡በየማታውም፡ለእግዚአብሔር፡የሚቃጠለውን፡መሥዋዕትና፡ጣፋጩን፡ዕጣን፡ ያሳርጋሉ፤የገጹንም፡ኅብስት፡በንጹሕ፡ገበታ፡ላይ፥የወርቁን፡መቅረዝና፡ቀንዲሎቹንም፡ማታ፡ማታ፡ እንዲያበሩ፡ያዘጋጃሉ፤እኛም፡የአምላካችንን፡የእግዚአብሔርን፡ትእዛዝ፡እንጠብቃለን፥እናንተ፡ግን፡ ትታችኹታል።

12እንሆም፥እግዚአብሔር፡በእኛ፡ላይ፡አለቃ፡ነው፥መለከቱንም፡የሚነፉ፡ካህናቱ፡ከእኛ፡ጋራ፡ ናቸው፥በእናንተም፡ላይ፡ይጮኻሉ።የእስራኤል፡ልጆች፡ሆይ፥አይበጃችኹምና፡ከአባቶቻችኹ፡አምላክ፡ ከእግዚአብሔር፡ጋራ፡አትዋጉ።

13ኢዮርብዓም፡ግን፡ድብቅ፡ጦር፡በስተዃላቸው፡አዞረ፤እነርሱ፡በይሁዳ፡ፊት፡ኾነው፡ድብቅ፡ጦሩ፡ በስተዃላቸው፡ነበረ።

14ይሁዳም፡ወደ፡ዃላው፡በተመለከተ፡ጊዜ፥እንሆ፥ሰልፉ፡በፊቱና፡በዃላው፡ነበረ፤ወደ፡እግዚአብሔርም፡ ጮኹ፥ካህናቱም፡መለከቱን፡ነፉ።

15የይሁዳም፡ሰዎች፡ጮኹ፤የይሁዳም፡ሰዎች፡በጮኹ፡ጊዜ፡እግዚአብሔር፡ኢዮርብዓምንና፡እስራኤልን፡ ዅሉ፡በአብያና፡በይሁዳ፡ፊት፡መታቸው።

16የእስራኤልም፡ልጆች፡ከይሁዳ፡ፊት፡ሸሹ፥እግዚአብሔርም፡በእጃቸው፡አሳልፎ፡ሰጣቸው።

17አብያና፡ሕዝቡ፡ታላቅ፡አመታት፡መቷቸው፤ከእስራኤልም፡ዐምስት፡መቶ፡ሺሕ፡የተመረጡ፡ሰዎች፡ ተገድለው፡ወደቁ።

18በዚያም፡ጊዜ፡የእስራኤል፡ልጆች፡ተዋረዱ፥የይሁዳም፡ልጆች፡በአባቶቻቸው፡አምላክ፡በእግዚአብሔር፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ታምነው፡ነበርና፥አሸነፉ።

19አብያም፡ኢዮርብዓምን፡አሳደደው፥ከርሱም፡ከተማዎቹን፥ቤቴልንና፡መንደሮቿን፥ይሻናንና፡ መንደሮቿን፥ዔፍሮንንና፡መንደሮቿን፡ወሰደ።

20ኢዮርብዓምም፡ከዚያ፡በዃላ፡በአብያ፡ዘመን፡አልበረታም፤እግዚአብሔርም፡ቀሠፈው፥ሞተም።

21አብያም፡ጸና፥ዐሥራ፡አራትም፡ሚስቶች፡አገባ፥ኻያ፡ኹለትም፡ወንዶች፡ልጆችንና፡ዐሥራ፡ስድስት፡ ሴቶች፡ልጆችን፡ወለደ።

22የአብያም፡የቀረው፡ነገርና፡አካኼዱ፡የተናገራቸውም፡ቃሎች፡በነቢዩ፡በአዶ፡መጽሐፍ፡ተጽፈዋል።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source