Skip to content
← 2 Chronicles

Chapter 14 · Amharic

2 Chronicles

1አብያም፡ከአባቶቹ፡ጋራ፡አንቀላፋ፥በዳዊትም፡ከተማ፡ቀበሩት፤ልጁም፡አሣ፡በርሱ፡ፋንታ፡ ነገሠ።በርሱም፡ዘመን፡ምድሪቱ፡ዐሥር፡ዓመት፡ያኽል፡ዐረፈች።

2አሣም፡በአምላኩ፡በእግዚአብሔር፡ፊት፡መልካምና፡ቅን፡ነገር፡አደረገ፤

3የእንግዳዎቹንም፡አማልክት፡መሠዊያ፡የኰረብታውንም፡መስገጃዎች፡አፈረሰ፥ሐውልቶቹንም፡ ሰበረ፥የማምለኪያ፡ዐጸዶቹንም፡ቈረጠ፤

4የአባቶቻቸውን፡አምላክ፡እግዚአብሔርን፡ይሹ፡ዘንድ፥ሕጉንና፡ትእዛዙንም፡ያደርጉ፡ዘንድ፡ይሁዳን፡አዘዘ።

5ከይሁዳም፡ከተማዎች፡ዅሉ፡የኰረብታውን፡መስገጃዎችና፡የፀሓይ፡ምስሎችን፡አስወገደ፤መንግሥቱም፡ በርሱ፡ሥር፡በሰላም፡ተቀመጠች።

6በይሁዳም፡ምሽጎች፡ከተማዎችን፡ሠራ፤እግዚአብሔርም፡ዕረፍት፡ስለ፡ሰጠው፡ምድሪቱ፡ጸጥ፡ብላ፡ ነበር፥በዚያም፡ዘመን፡ሰልፍ፡አልነበረም።

7ይሁዳንም፦እነዚህን፡ከተማዎች፡እንሥራ፥ቅጥርም፡ግንብም፡መዝጊያም፡መወርወሪያም፡ እናድርግባቸው፤አምላካችንን፡እግዚአብሔርን፡ስለ፡ፈለግነው፡ምድሪቱ፡ገና፡በፊታችን፡ናት፤እኛ፡ ፈልገነዋል፥ርሱም፡በዙሪያችን፡ዕረፍት፡ሰጥቶናል፡አለ።እነርሱም፡ሠሩ፡አከናወኑም።

8ለአሣም፡አላባሽ፡አግሬ፡ጋሻና፡ጦር፡የሚሸከሙ፡ሦስት፡መቶ፡ሺሕ፡የይሁዳ፡ሰራዊት፥ጋሻም፡ የሚሸከሙ፡ቀስትም፡የሚገትሩ፡ኹለት፡መቶ፡ሰማንያ፡ሺሕ፡የብንያም፡ሰዎች፡ነበሩት፤እነዚህም፡ዅሉ፡ ጽኑዓን፡ኀያላን፡ሰዎች፡ነበሩ።

9ኢትዮጵያዊውም፡ዝሪ፡አንድ፡ሚልዮን፡ሰዎችና፡ሦስት፡መቶ፡ሠረገላዎች፡ይዞ፡ወጣባቸው፤ወደ፡ መሪሳም፡መጣ።

10አሣም፡ሊጋጠመው፡ወጣ፥በመሪሳም፡አጠገብ፡ባለው፡በጽፋታ፡ሸለቆ፡ውስጥ፡ተሰለፉ።

11አሣም፦አቤቱ፥በብዙም፡ኾነ፡በጥቂቱ፡ማዳን፡አይሳንኽም፤አቤቱ፡አምላካችን፡ሆይ፥ባንተ፡ ታምነናልና፥በስምኽም፡በዚህ፡ታላቅ፡ወገን፡ላይ፡መጥተናልና፥ርዳን፤አቤቱ፥አምላካችን፡አንተ፡ ነኽ፤ሰውም፡አያሸንፍኽ፡ብሎ፡ወደ፡አምላኩ፡ወደ፡እግዚአብሔር፡ጮኸ።

12እግዚአብሔርም፡በአሣና፡በይሁዳ፡ፊት፡ኢትዮጵያውያንን፡መታ፤ኢትዮጵያውያንም፡ሸሹ።

13አሣም፡ከርሱም፡ጋራ፡ያለው፡ሕዝብ፡እስከ፡ጌራራ፡ድረስ፡አሳደዷቸው፤ኢትዮጵያውያንም፡ፈጽመው፡ እስኪጠፉ፡ድረስ፡ወደቁ፥በእግዚአብሔርና፡በሰራዊቱ፡ፊት፡ተሰባብረዋልና፤እጅግም፡ብዙ፡ምርኮ፡ወሰዱ።

14ከእግዚአብሔርም፡ዘንድ፡ታላቅ፡ድንጋጤ፡ስለ፡ወደቀባቸው፡በጌራራ፡ዙሪያ፡የነበሩትን፡ከተማዎች፡ዅሉ፡ መቱ፤በከተማዎቹም፡ውስጥ፡እጅግ፡ብዝበዛ፡ነበረና፡ከተማዎቹን፡ዅሉ፡በዘበዙ።

15የከብቶቹንም፡በረት፡አፈረሱ፤እጅግም፡ብዙ፡በጎችንና፡ግመሎችንም፡ማረኩ፥ወደ፡ኢየሩሳሌምም፡ http://www.gzamargna.net www.ethiopianorthodox.org ተመለሱ።

Amharic — extracted from the Ethiopian Orthodox typeset edition (Desta Unicode), lossless; verify symbols against the source